Friday, May 24th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

በገዳዩ ሮቦት ዙሪያ ክርክር ያስፈልጋል

E-mail Print PDF
User Rating: / 23
PoorBest 

ራሱን ችሎ በጦርነት መሳተፍ የሚችለውን ገዳይ ሮቦት በተመለከተ ዓለም አቀፍ ክርክር እንደሚያስፈልግ ሺፊልድ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ዩኒቨርሲቲውን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው የሮቦት ቴክኖሎጂን በጦርነት ውስጥ መጠቀም ሰላማዊውን ሕብረተሰብ አደጋ ውስጥ ሊጥል ይችላል፡፡

እንግሊዝ ላይ በተደረገው ስብሰባ የአሜሪካ ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ የስነምግባር ጥያቄዎችን የሚፈታ እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ "ሮቦቶች የት መግደል እንዳለባቸውና ማንን እንደሚገድሉ መቼ እንደሚገድሉ መወሰን ይችላሉ፡፡" ብለዋል፡፡

ከሺፊልድ ዩኒቨርሲቲ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ሻርኬይ በበኩላቸው የሮቦቶች ውሳኔ በሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሻርኬይ ሮቦቶችን በጦርነት መጠቀም ያልተለመደ እንደሆነ ጠቅሰው የጦርነትን ባህሪም እንደሚቀይር ተናግረዋል፡፡ "አንድ ወታደር ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ በሪሞት ኮንትሮል በመቆጣጠር ሰው አልባ የሆኑ በአየር የሚበሩ ተሸከርካሪዎችን በ100 ሺህ በሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ይቆጣጠራል፡፡ ይህም በአካል ተገኝቶ ከሚደረግ ውጊያ አንፃር የስነ ልቦና ጫና የለውም ቀን በጦርነት የተሳተፈው ወታደር ማታ ወደ ቤቱ ተመልሶ ራቱን ይመገባል፣ ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር የተለመደውን ሕይወት ይቀጥላል፡፡  ይህ ያተለመደ ነገር አይደለም" ብለዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሮቦቶችን ለጦርነት መጠቀም ፅንሰ ሃሳቡ ሰው አልባ ተሽከርካሪዎች በመላክ መዋጋት ብቻ አይደለም፡፡ በምድርም ከሰው እርዳታ ውጭ በራሳቸው የሚወስኑ ሮቦቶችንም በእግረኝነት መጠቀምን ይጨምራል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ የእንግሊዝ ወታደሮች ባለፈው ወር አፍጋኒስታን ላይ ሰው አልባ የአየር ላይ ተሸከርካሪዎችን ለማሰማራት፣ የአሜሪካ አየር ኃይል በበኩሉ "አንማንድ አርቲክራፍት ፍላይት ፕላን 2009-2047" በሚል በያዝነው ወር ሰው አልባ የሆኑ የጦርነት የአየር ላይ በረራዎችን በተመለከተ እቅዳቸውን አሳትመዋል፡፡ ራሳቸውን ችለው የሚዋጉ አውሮፕላኖችን የማሰማራት ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡ የታመው ዶክመንት እንደሚለው ለውጊያው የሚደረጉ ውሳኔዎችን ዋና ዋና ሚናዎች ሰዎች ይቆጣጠራሉ፡፡

ፕሮፌሰር ሻርኬይ ገዳይ ማሽኖችን በተመለከተ የሚከሰቱ አሉታዊ ገፅታዎችን ጠቅሰው፣ ስራ ላይ ከመዋላቸው በፊት ዓለም አቀፍ ክርክር እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡ በተለይ ውሳኔ ሰጭነቱ ለሮቦቶቹ ቢተው ይሻላል ወይስ ሰዎች መቆጣጠር አለባቸው የሚለው ሃሳብ ላይ ክርክር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡