Sunday, May 19th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

ቬንገር በፈረንሳውያን፣ ፈርጉሰን በበረኛ ዝውውር ተጠምደዋል

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

የእንግሊዝ ክለቦች የፊታችን ቅዳሜን የሚጠብቋት በጉጉት ነው፡፡ በፈረንጆች አዲስ ዓመት የተጫዋቾች ዝውውር ከሚከናወንባቸው ወቅቶች አንዱ በመሆኑ ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ክለቦች ለፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ የሚጠበቁት ማንቼስተር ዩናይትድና አርሰናል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡

በዝውውር ገበያው ብዙም የማይታሙት ፈረንሳዊው አርሴን ቬንገር የዚህ ዓመት ቡድናቸው አቋም የጠበቁትን ያህል ወጥ አለመሆኑን ተከትሎ፣ ተቀናቃኞቻቸውን ለመምሰል እየተገደዱ ስለመሆኑ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡
ወትሮም ቢሆን በዝውውር ገበያው ተዋንያን ከመሆን ያልቦዘኑት የማንቼስተሩ ማናጀር ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በበኩላቸው፣ ቅዳሜን የሚጠብቁት ለዝውውሩ ዳጐስ ያለ ገንዘብ መድበው መሆኑ ትኩረትን ስቧል፡፡

ከውጤት ይልቅ ለኳስ ፍሰት ቅድሚያ እንደሚሰጡ የሚነገርላቸው ቬንገር፣ የውድድር ዓመቱን የጀመሩት በመልካም ውጤት ቢሆንም፣ ከፈረንሳይ ሞናኮ ያስፈረሙት ማርዋን ሻማክ፣ የአጥቂ መስመሩን የመምራት አቅም ቢኖረውም፣ የቡድኑ የኋላ ደጀን ግን የሚጠበቅበትን ሚና መወጣት አለመቻሉ ሥጋት ፈጥሮባቸዋል፡፡

ቬንገር ቡድናቸውን በተለይም ተከላካይ ክፍላቸውን በአብዛኛው ያዋቀሩት በፈረንሳውያን ተጫዋቾች ነው፡፡ እንደዚህም ሆኖ ሎሮ ኮሸየሊናና ስባስቲያን ስኩላቺ እስከ አሁን ጥምረት ሊፈጥሩ አለመቻላቸው ቬንገር ሊፈቱት ያልቻሉት ችግር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ቬርማሌን ከጉዳቱ ሊያገግም አለመቻሉ አሠልጣኙ የሚጠሉትን የዝውውር ገበያ እንዲቀላቀሉ እንዳስገደዳቸው ተጠቁሟል፡፡

ቬንገር ከትውልድ አገራቸው የሚወጡ ተጫዋቾችን ወደ አርሴናል በማስመጣት የቆዩ ሲሆን፣ በዚህ ወቅትም ሊያስፈርሟቸው ያሰቡት ተጫዋቾች በፈረንሳይ ሊግ እየተጫወቱ የሚገኙትን ያካትታል፡፡ ከእነዚህ ተጫዋቾች ከ10 እስከ 15 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚያወጡለት የሚጠበቀውና የሊል ክለብ ተጫዋች የሆነው አዲል ራሚ አንዱ ነው፡፡ ሌላው አሁንም ከሊል ክለብ መሆኑ የሚነገርለት የሀን ካባዩ ሲሆን፣ ለተጫዋቹ ከሰባት ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደመደቡም ተነግሯል፡፡ ሌሎችም ፈረንሳዊ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች በቬንገር የዝውውር እይታ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል፡፡ በዚያው መጠን አርሴናልን ይለቃሉ ተብሎ ከሚጠበቁት ውስጥ ደግሞ ቶማስ ሮዚስኪ፣ ዴልሰንና ቬንትነር ይጠቀሳሉ፡፡

ፕሪምየር ሊጉን የሚመሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በበኩላቸው፣ ክለቡን በባለቤትነት ከሚያስተዳድሩት ግለዜሮች 50 ሚሊዮን ፓውንድ ለዝውውር ተመድቦላቸዋል፡፡

የፈርጉሰን የመጀመርያው የዝውውር ኢላማም በአሁኑ ወቅት 38ኛ ዓመቱን እያስቆጠረ የሚገኘውን ኤዲዮን ቫን ደርሳርን መተካት ነው፡፡ በምትኩ የሊቨርፑሉን ፔፔ ሬይናን እንዳሰቡም ተመልክቷል፡፡ ቫን ደርሳርን የመተካቱ ሐሳብ የቆየ ቢሆንም፣ ነገር ግን በፈርጉሰን መስፈርት የሚመጥን ጠፍቶ ዛሬ ላይ መድረሳቸውም ይነገራል፡፡ ሬይናን የቀያዮቹ ባለቤቶች የማይለቁት ከሆነ በሚል በሁለተኛነት የባየር ሊቨርኩሰኑ ሬነን አድለርን እያነጋገሩ መሆኑንም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

እንደ መረጃው አሌክስ ፈርጉሰን ከበረኛ ውጪ ሊያስፈርሙት ያሰቡት ተጫዋች በማንቼስተር ቤት ምትክ ያልተገኘለት ‹‹የምንጊዜም የእኔ ምርጥ›› ሲሉ ፈርጉሰን የሚያወድሱት ሪያን ጊግስንን የሚተካ ተጫዋች ነው፡፡ ለዚህም አሠልጣኙ እስካሁን ሁነኛ ብለው የመረጡት እንዳላገኙ፣ ነገር ግን እያፈላለጉ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡