Thursday, May 23rd

English Version

Error
  • Error loading feed data.

መንፈሱ

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

 

መንፈሱ

ዕውቀት ከሰው ልጅ ርቃ የተደበቀች ስለመሆንዋ በዕብራውያንም ዘንድ አንድ ተመሳሳይ ንግርት እናገኛለን፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት እንደምናነበው የመጀመሪያው ሰው በገነት ሲኖር ማናቸውም ነገር ተፈቅዶለት “ከዕውቀት ዛፍ” ብቻ አንዲት ፍሬ እንዳይቀምስ ተከልክሎ ነበር፡፡ ግን በልቶ ተገኘ፡፡

ይህንን ሐሳብ በነፃ ሕሊና ለመረዳት ብንፈልግ ሰው በስጦታ ወይም በችሮታ በሚገኘው ድሎት የማይደሰት መሆኑንና ከገነት ለመውጣት የደፈረው ከዕውቀት በሚያገኘው ጉልበት ራሱን ለማስተዳደር የራሱ ባለሥልጣን ገዥ ለመሆን ነው እስከ ማለት እንደርሳለን፡፡ ይህንን ሐሳብ ለማስረዳት ከዘመናዊ የአማርኛ ግጥም አንድ እንጠቅሳለን፡፡ ገጣሚው በገነት ስለነበረው ሰው ሲናገር ቆይቶ በመካከል እንዲህ ይላል፡፡

በዙሪያው የነበር ሀብትና ንብረት
ሽልማት ነበረ የለተ ልደት፡፡
ስጦታ ለሰጭው እጅግ ያስደስታል፡፡
ለተቀባይው ግን ጸጸትን ያተርፋል፡፡
እጁን ሲዘረጋ ሲፈራ ሲቸር
ለማግኘት ለማጣት በመጠራጠር፡፡
ልቡ ይጨነቃል ይላል ትርትር
“እምቢኝ አሻፈረኝ በችሮት አልኖርም፡፡
ላቤን አንጠፍጥፌ ሠርቼ ደክሜም
“በነፃ እኖራለሁ ስሰግድ ለማንም፡፡”
ፎክሮ ማለና ቢነሣስ አንድለት
ራሱን በራሱ ነፃ ለማውጣት
ትቢት ሽፍተኝነት ተቆጠረበት
በቡራኬ ፈንታ እርግማን ሰጡት
ዓለም ተለወጠች ወደወህኒ ቤት
ብርሃኑ ጠፋና ጭለማ ዋጣት፡፡
በድሉ ሳያዝን ከቶ ሳያመር
በሌሊት ቁርና በመዓልት ሀሩር
የሚሰጠው ሳይኖር ጥዋ ማይ ቆሪር
ሀ ብሎ ጀመረ ዓለም ለመፍጠር፡፡
ወደላይ ተጓዘ ከጧት እስከ ማታ
መስቀል ተሸክሞ ትልቁ ከርታታ
ዓለምን ለማዳን በታሪክ ጎልጎታ፤
አማልክት መጡና እንርዳህ ቢሉት
ገነት እንዲያገቡት ተስፋ ቢሰጡት
ለቅጽበት ማረከው የስሜት ብርታት
ራሱን ነቅንቆ በኀዘን ትርዒት
በሐሳብ ብቻ እንጂ የለሽም በውነት
አስታውስሻለሁ በጋለ ምኞት
ገነት ገነት ሀገሬ ገነት፤

ምን ይሆናል ግና ዋግሽ ባርነት፤


በዚህ ሐሳብ መሠረት ሰው የሚመኘው የሚጥረውም በገዛ ራሱና በዙሪያው ባሉት ነገሮች ላይ ሁሉ ሥልጣን እንዲኖረው ነው፡፡ ከሥልጣኔ ዘይቤ አሁን የደረስን ይመስለኛል፡፡ ሥልጣኔ ማለት መጀመሪያ ሰው በሕሊናው ውሰጥ ያሉትን ሀብታት መርምሮ ተረድቶ መሪነቱን ካወቀ በኋላ ዝቅተኛውን የስሜት ወይም የፍትወት ዓለም አርቆ ገርቶ ለሕሊናው ያስገበረ እንደሆን በራሱ ላይ ሥልጣን ያለው የሆነ እንደሆነ  የሚሰጠው ቅጽል ነው፡፡ ሁለተኛ በዙሪያው ያሉትን ሥነ ፍጥረቶች ለራሱ እንዲያገለግሉ ለማስገበር የሚያደርገው ጥረትና ከዚያ ጥረትና ከዚያም የሚገኘው ውጤት ሥልጣኔ ይባላል፡፡ በመጀመሪያው በኩል ያደረገው እርምጃ ምንም እንኳ የሚያጠራጥር ቢሆን፣ በሁለተኛው በኩል በጣም ርቆ ሔዶአል፡፡ አየር ይታዘዘዋል፡፡ ከውሃ እሳት ለማውጣት ችሏል፡፡ ነገሩ ቁጥርም የለው፡፡

(እጓለ ገ/ዮሐንስ፤ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣ 1955)


ስለ ሲጋራ አንዳንድ እውነታዎች

ሲጋራ የሚያጨሱ ወጣቶች አይ ኪው፣ ከማያጨሱ የዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ብሎ መገኘቱ ቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ የሳይካትሪ ትምህርት ክፍል ተረጋግጧል፡፡

ዕድሜያቸው ከ18-21 በሚደርስ የእሰራኤል የጦር ሰራዊት አባላት በሆኑ ወጣቶች ላይ የተደረገው በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ጥናት ሲጋራ የማያጨሱ ወጣቶች አማካይ አይ ኪው 101 ሲሆን የሚያጨሱት ደግሞ 94 ሆኖ ተገኝቱል፡፡ እንደ ጥናቱ ገለፃ በቀን አንድ ፓኬት ሲጋራ የሚያጨቡ ወጣቶች አይ ኪው ከሌሎቹ በጣም ያነሰ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሲጋራ ውስጥ ከ 3,000 ያላነሱ በጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችና ኬሚካሎች ይገኛሉ፡፡ ሲጋራ ውስጥ የሚገኘውና ሱስ የሚያስይዘው ኬሚካል ኒኮቲን ይባላል፡፡ ኒኮቲን የማያቋርጥና እየጨመሪ የሚሄድ ጠንካራ የሲጋራ ፍላጎት ያሳድራል፡፡ በአንድ ሲጋራ ውስጥ 0.5 ሚሊ ግራም ኒኮቲን ይገኛል፡፡ ከ 60 ሚሊ ግራም በላይ ኒኮቲን ወደ ሰውነት ውስጥ ከገባ ሞት ያስከትላል፡፡ ከዚህ ባሻገርም የኒኮቲን በሰውነት ውሰጥ መብዛት ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ምራቅ መብዛት፣ መገርጣት፣ ድካም፣ የሆድ ህመም፣ የልብ ትርታ መፍጠን፣ መንቀጥቀጥ፣ የደም ግፊት መጨመር እና ማላብን ከማስከተሉም ሌላ ሃሳብን መሰብሰብ ያለመቻል፣ ግራ መጋባትንና ብዥታን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከኒኮቲን በተጨማሪ ሲጋራ ውስጥ ታር እና ካርቦንሞናክሳይድ የተባሉ ጎጂ ኬሚካሎች ይገኛሉ፡፡ ታር የሚያጣብቅ ቡናማ ንጠረነገር ሲሆን ሳንባ ላይ ካንሰር የሚያስከትል ኬሚካል ነው፡፡ ካርቦንሞኖኦክሳይድ በደም ውስጥ የሚተላለፈውን ኦክስጂን ቦታ በማስለቀቅ ጉዳት የሚያደርስ መርዝ ነው፡፡ የሲጋራ ጭስ የሳንባ ህዋሶችን እና አየር መሸከሚያ ክፍሎችን በመጉዳት በቂ ኦክስጂን ከሳንባ ወደ ደም ውስጥ እንዳይገባ ያደርጋል፡፡ ጉዳቱ እየበዛ ሲሄድ ኤምፊሴማ የሚባል የሳንባ በሽታና ስር የሰደደ የሳንባ ቱቦ (ብሮንካይትስ) በሽታ ይከተላል፡፡ ሰውነት በቂ ኦክስጂን ስለማያገኝ ትንፋሽ ማጠር ይከተላል፡፡

በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ የሳንባ፣ የአፍ፣ የምላስ፣ የጉሮሮ፣ የፓንክርያስ፣ የኩላሊት እና የፊኛ ካንሰር ያስከትላል፡፡ ይህም የሚሆነው የሰውነት ህዋሳት በሲጋራ ጭስ ውስጥ ባሉ ኬሚካሎች ምክንያት አደጋ ደርሶባቸው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ መራባት ሲጀምሩ ነው፡፡

(ሳይንስ ዴይሊ)


ከበር


በፓርላማ የጆሮ ጌጥ አድርጎ የገባ የሕዝብ ተወካይ ከፓርላማ ታገደ

በኬንያ ፓርላማ የሕዝብ ድምጽ አግኝቶ የገባው ሚ/ር ጌዲዮን እምቡቪ የጆሮ ጌጥ በማድረጉ ወይም ሁሌም ፓርላማ ሲገባ በመሽቀርቀሩ ከፓርላማ እታገዳለሁ ብሎ አልገመተም፡፡

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ግን ያልጠበቀው ተቃውሞ ከፓርላማ አባላቱ ገጥሞታል፡፡ በፓርላማ ውስጥ ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ፣ ፋሽን መከተል ብሎም የጆሮ ጌጥ አድርጎ መምጣት ያልተገባና ክብርን የሚያጎድፍ ነው በሚልም በፓርላማ እንዳይሳተፍ ተደርጓል፡

ወጣቱና በቅጽል ስሙ፣ በኪስዋህሊ ሶኖኮ ማትም (ሃብታሙ ሰው) በመባል የሚታወቀው ሚ/ር እምቡቪ “እኔ በፓርላማ የወከልኩት ወጣቱን ነው፡፡ በኔ ሕይወት ጣልቃ ከመግባት የመጣሁበትና የወከልኩት ወጣቱ ላይ ማተኮር ነበረባቸው፣”› ብሏል፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው፣ ሚ/ር እምቡቪ ውክልናው ከኬንያዋ መዲና ናይሮቢ  ነው፡፡


የመጨረሻዋ ቢራ ያስከሰሰቻቸው

አባትና ልጅ ቢራቸውን መጠጣታቸውን ተያይዘውት ነበር፡፡ የመጨረሻዋ ቢራ ስትቀራቸው ያልጠበቁት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡

እነሱ ወደሚጠጡበት ስፍራ የገባው የ46 ዓመቱ ጎልማሳ የቀረቻቸውን አንድ ቢራ አንሥቶ ይጠጣል፡፡ በድርጊቱ የተናደዱት አባትና ልጅ ጎልማሳውን ይደበድቡታል፡፡
ሰንሰንቲኔል ድረ ገጽ እንደዘገበው አባትና ልጅ በ46 ዓመቱ ጎልማሳ ላይ ባደረሱት ድብደባ ልጅ ሲታሰር አባት በነፃ ተሰናብቷል፡፡


በመቶዎች የሚቆጠሩ ሊያሳድጉት የቋመጡለት ቡችላ


በመቶዎች የሚቆጠሩ ካናዳውያንና አሜሪካውያን በአጋጣሚ ከሞት የተረፈውን ቡችላ ለማሳደግ እኔ እኔ እያሉ ነው፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ የኦክላህማ ከተማ ነዋሪ የሆነው የእንስሳት ሐኪም፣ አምሰት የሞቱ ውሾችን ካስቀመጠበት ማጠራቀሚያ አንዱ ቡችላ ቀና ብሎ ሲያየው በማየቱ ሕይወቱ እንዳለ ተገንዝቧል፡፡

የእንስሳት ሐኪሙ ከሙታን ውሾች አንዱን ማግኘቱን ጠቅሶ በድረ ገጽ ይለቃል፡፡ ድረ ገጹን ከጎበኙት በመቶዎች የሚቆጠሩትም ቡችላውን ለመውሰድ የሐኪሙን ስልክና ኢሜይል አጨናንቀውታል፡፡