Friday, May 24th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

በግንቦት 7 ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሃሳብ

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ኅዳር 4 ቀን 2002 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የቅጣት ማክበጃ ሃሳብ፣ በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ የተከሰሱ 38 ተከሳሾች በተመሰረተባቸው አምስት የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ በመባላቸው የመጨረሻውንና ለመሰሎቻቸው ማስጠንቀቂያ፣ መቀጣጫና ማስተማሪያ የሚሆነውን የሞት ቅጣት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡



በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሃይልና በትጥቅ አመፅ ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ በሚል ክስ ከተመሠረተባቸው 46 ተከሳሾች ውስጥ 14ቱ በሌሉበት፣ 32ቱ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸው ከታየ በኋላ የአንድ ተከሳሽ ክስ ሲቋረጥ፣ አምስቱ በነፃ ተሰናብተዋል፡፡ ሁለት ተከሳሾች ጥፋታቸውን በማመናቸው ዐቃቤ ሕግ "ቅጣቱ ቢቀልላቸው አልቃወምም" ብሏል፡፡ በማረሚያ ቤት በሚገኙት 25 ተከሳሾችና በሌሉበት ጥፋተኛ በተባሉት 13ቱ ተከሳሾች ላይ ግን የቅጣት ማክበጃ አቅርቧል፡፡ የማክበጃው ሃሳብ የሚከተለው ነው፡፡

የጥፋተኝነት ውሣኔ ለተላለፈባቸው ሁሉም ተከሳሾች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 149/3/ መሠረት የቀረበ የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ሃሳብ፣

ሁሉም ተከሳሾች በቀረቡባቸው አምስት የተለያዩ የወንጀል ክሶች ማለትም የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 38 እና 240/1/ሀ/፤ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 38፣27/1/ እና 238/1/ሀ/ለ/፤ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 38 እና 247/ሐ/፤ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 38 እና 256/ሀ/ሀ/፤ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 38 እና 257/ሀ/ለ/ሐ/ሠ/ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይልና በትጥቅ አመፅ ለመጣል የጋራ የወንጀል አድማ ስምምነት በመፍጠር የወንጀል ድርጊቱን አላማ ውጤትና ፍሬ ሙሉ በሙሉ በመቀበል፣ በመደራጀት በማደራጀት፣ በመምራት ስርዓቱን በሽብርና በዐመፅ ተግባር ለማፍረስ ተሳትፈዋል በሚል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የቅጣት አስተያየታችን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

ሀ. የግል ነፃነታቸውን በተመለከተ
የተከበረው ፍርድ ቤት

1.    24ኛ ተከሳሽ መላኩ ተፈራ፣ 38ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ነጋ፣ 39ኛ ተከሳሽ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ 40ኛ ተከሳሽ ሙሉነህ ኢዮኤል እና 44ኛ ተከሳሽ መስፍን አማን የቅንጅት ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ሆነው በሚሠሩበት ጊዜ ሕዝብን በተሳሳተ መንገድ በመምራት ለብጥብጥ ሁከት በማነሳሳት ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ፣ በሰው ሕይወት፣ በሰው አካል፣ በሕዝብና በመንግሥት ንብረት ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ በማድረጋቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 43246 እና 45990 ተከሰው እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት መላኩ ተፈራ በአስራ አምስት ዓመት መቀጣታቸውን ከላይ በተጠቀሱት የመዝገብ ቁጥሮች እንዲመለከትልንና በማክበጃነት እንዲመዘግቡልን በማክበር እንጠይቃለን፡፡

2.    ከቅጣት በኋላ ተከሣሾች በጥፋታችን ተጸጽተናል፣ ዳግመኛ በማናቸውም የወንጀል ተግባር አንሰለፍም ሲሉ ቃል ገብተው፣ መንግሥት ይቅርታ ያድርግልን ብለው በመጠየቃቸው ቅጣታቸው በይቅርታ የቀረላቸው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣

ለተከሳሾች ይቅርታ የተደረገላቸው ሕግና ሥርዓት አክብረው በሰላም እንዲኖሩ ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ በኤፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 1 ላይ እንደተመለከተው የቅጣት ዓላማው ላለፈው ጥፋት መማሪያ ወደፊትም ድጋሚ ጥፋት እንዳይሠራ ማስጠንቀቂያ መሆኑ በግልጽ ሠፍሯል፡፡

ይሁን እንጂ ተከሳሾች ካለፈው ስህተታቸው የማይታረሙ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ ቆርጠው የተነሱ ብጥብጥና ሁከት በማስነሳት ሕዝብን በማጋጨት በዜጎችና በመንግሥት ላይ ጉዳት ማድረስን ሙያ አድርገው የያዙ ደጋጋሚ አጥፊዎች በመሆናቸው በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 67/1/፣188/1/ መሠረት ቅጣት ከብዶ እንዲወሰንባቸው ስለሚያስገድድ፡፡

3.    ከዚህ በኋላም ሊታረሙ እንደማይችሉ፣ የከሸፈባቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊት ማሳያ ከመሆኑ ባለፈ ተመሳሳይ ህገወጥ ድርገት ለማስፈፀምና ለመፈፀም አሁንም በሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ሀገር በመሥራት ላይ በመሆናቸውና በሀገራዊ ሕገ-
መንግሥቱና አጠቃላይ ሕዝብ ላይ አደጋ ለማድረስ አረመኔያዊነት በተላበሰ ሁኔታ በግላጭ እየሠሩ በመሆናቸውና ይህ ዓይነት ድርጊት ማክበጃ በመሆኑ፡፡

4.    ሁሉም ተከሣሾች የፈጸሙት ወንጀል ፍጻሜ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ብቻ የሚቆም ሳይሆን በሕዝቦች እኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ በተመሠረተ አንድነት የተዋቀረውን ፌዴራላዊ ሥርዓት የሚያፈርስ፣ የአገሪቱን አንድነት የሚበታትን፣ በአገር ህልውና ያነጣጠረ፣ የአንድ ወገን ፍላጎት በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ላይ የሚጭን፣ አገሪቱን ማብቂያ ወደሌለው ትርምስና የእርስ በርስ ጦርነት የሚከት፣ አደገኛ አድራጎት ከመሆኑም በላይ የአገሪቱን ውድቀት በመመኘትና ብርቱ ፍላጎት የተፈፀመው ወንጀል ከአድማ የተነሳና በግብረ-አበርነት በህቡዕ በተደራጀ ቡድን በጦር መሣሪያ በታገዘ መልኩ የተፈፀመ ወንጀል በመሆኑ በኤፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 258 /ለ/ መሠረት ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰን የሚደነግግ በመሆኑ፡፡

5.    ሁሉም ተከሳሾች በተለያዩ ሀሳቦች፣ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች እና የመብት ጥሰቶች የተቋቋሙ ተደራራቢ አምስት ግዙፍ ወንጀሎች በመፈፀማቸው የሚጣለው ቅጣት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 85 እና 184 መሠረት ቅጣቱ መክበድ እንዳለበት ሕጉ በግልፅ የደነገገ ስለሆነ፡፡

6.    ሁሉም ተከሳሾች የትምህርት ደረጃቸው ከመካከለኛ በላይና ከፍተኛ ሲሆን ይህም ሕጋዊ አካሄድን ከሕገ-ወጥ መንገድ በቀላሉ ለመለየት እንደሚችል ለማረጋገጥ የሚችል፣ ብሎም አገሪቷ እና ሕዝቦቿ ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር በተደላደለ መልኩ እንዲቀጥል ደፋ ቀና በሚሉበት፣ ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ተቀርጾለት በሰላማዊ የትግልና የሥልጣን ሽግግር በተዘረጋበት ወቅት የፈፀሙት ተደራራቢ ወንጀል እና አጠቃላይ አድራጎታቸው ሊያስከትል የሚችለውን ከፍተኛ አደጋ ከምንም ባለመቁጠር ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በትጥቅ ዓመፅ ለማፍረስ መሞከራቸው ብቻውን ቅጣቱ ከመነሻው ይልቅ ከባዱ እና ከፍተኛ ሊሆን ስለሚገባው፤

7.    የሁሉም ተከሳሾች የወንጀል አድራጎት የወንጀሉ አፈፃፀምና ዘዴ ሲታይ ወንጀል ለመፈፀም በተደረገ ስምምነት፣ ከሌሎች ጋር በመሆን በጦር መሣሪያ የተደገፈ አደገኛ የሽብር ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 84 ንዑስ አንቀፅ 1/ሐ/ እና መ እና 183 መሠረት ከባዱ ቅጣት መወሰን እንዳለበት ስለሚያስገድድ፤

8.    ከ11ኛ ተከሳሽ አዱኛ አለማየሁ እና 17ኛ ተከሳሽ አደፍርስ አሳምነው ውጪ የተቀሩት ተከሳሾች በወንጀል ሕግ አንቀፅ 82 እና 179 መሠረት ሊነሱ የሚችሉ በማስረጃ የተደገፉ የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ጠቅላላና ልዩ ማቅለያ ፈፅሞ እንደሌሉ በክርክሩ ወቅት የታወቀ በመሆኑ በተቃራኒው አላስፈላጊ የዘረኝነት ቅስቀሳ እና ጉዳዩ የማንዛዛት ድርጊታቸው አደገኝነታቸው ያሳያል ለአጥፊዎቹ ሌላ ወንጀል እንዳይፈፅሙ ለመግታት፣ ለመሰሎቻቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያና መቀጣጫ ለተቀረው ማስተማሪያ የሚሆን ጥፋተኛ በተሰኙበት የሕግ አንቀፅ የተቀመጠው ቅጣት ጣሪያ (ከፍተኛና የመጨረሻው) የሆነው የሞት ቅጣት እንዲወሰንባቸው እንጠይቃለን፡፡

11ኛ ተከሳሽ አዱኛ አለማየሁ እና 17ኛ ተከሳሽ አደፍርስ አሳምነው ምንም እንኳ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት የጋራ ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆነው ዘግይተው ቢያምኑም ማመናቸው መፀፀታቸውን ስለሚያሳይ ቅጣቱ ቢቀልላቸው ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

ለ. በወንጀል ህግ አንቀፅ 98፣ 99 እና 260 መሠረት በማድረግ በተከሳሾች ባለቤትነት የተመዘገበው የግል ንብረት እንዲወረስ መጠየቅ፤
የተከበረው ፍርድ ቤት

ሀ/ በወንጀል ህግ አንቀፅ 98/1/2/ መሠረት በማድረግ በህግ በግልፅ በተደነገገ ግዜ የወንጀለኛውን ንብረት በሙሉ ወይም በከፊል እንዲወረስ ሊፈርድ እንደሚችል በመደንገጉ፣ 
ለ/ በወንጀል ህግ አንቀፅ 99 መሰረት "ማንም ሰው በአገሪቱ ህገመንግስታዊ ስርአት ወይም በውስጥና በውጭ ደህንነት ላይ አድማ በማድረጉ ወይም ጉዳት የሚያደርስ ተግባር በመፈፀሙ ምክንያት በሌለበት በሚፈረድበት ጊዜ በሚወሰንበት ከማንኛውም ቅጣት ጋር አጣምሮ ንብረቱ እንዲያዝ ለማዘዝ እንደሚችል በመደንገጉ"፣
ሐ/ በወንጀል ህግ አንቀፅ 260 መሠረት "ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እንዲያስከብር በግልፅ አደራ የተጣለበት ሰው በወንጀል ህግ አንቀፅ 238፣ 240 እና 241፣ 246 እስከ 256 እና 252/2/ ከተመለከቱት ወንጀሎች አንዱን በመፈፀም ጥፋተኛ ሆኖ የተፈረደበት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ከሚፈርደው ከዋናው ቅጣት ጋር አጣምቶ የተፈረደበት ሰው ንብረት በህግ መሠረት እንዲወረስ ማድረግ እንደሚቻል በመደንገጉ"፣
መ/ ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደተሞከረው ሁሉም ተከሳሾች ተላልፈዋል በማለት ዐቃቤ ህግ እየተከራከረባቸው ያሉት አንቀፆች በወንጀል ህግ አንቀፅ 260 መሰረት የሚሸፈኑ በመሆናቸው፣
ሠ/ 38ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር፣ 39ኛ ተከሳሽ አንዳርጋቸወ ፅጌ ሀ/ማርያም፣ 5ኛ ተከሳሽ ኮ/ል አለህበል አማረ ዋሴ፣ 18ኛ ተከሳሽ ያረጋል ይማም (ሚኪ"፣ በሌሉበት ተከሰው በቀረበባቸው አምስቱም ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው እና በወንጀል ህግ አንቀፅ 99 እና 260 መሰረት ንብረታቸው እንዲወረስ በመደንገጉ፣
ረ/ 1ኛ ተከሳሽ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ጨርቆስ፣ 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሳምነው ፅጌ ተበጀ፣ 36ኛ ተከሳሽ አቶ ጌቱ ወርቁ ንዳው፣ 37ኛ ተከሳሽ አቶ ፅጌ ሀ/ማርያም ጨሜሶ፣ በቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በወንጀል ህግ አንቀፅ 260 መሰረት ንብረታቸው እንደሚወረስ በግልፅ በመደንገጉ፣
ሸ/ ተከሳሾች በስማቸው በባለቤትነት የያዟቸው የተለያዩ ንብረቶች ዝርዝር ያሉበት ቦታና ሁኔታ ዐቃቤ ህግ አጣርቶ በማቅረቡ እና ከዚሁ አቤቱታ ጋር አያይዞ በማቅረቡ፣
ቀ/ ተከሳሾቹ የክቡር ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ንብረታቸው እንዲወረስ በሚያስችል መልኩ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ክቡር ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹ የንብረት ድርሻ እንዲሁም በእነርሱ ባለቤትነት የተመዘገበ የግል ንብረት እንዲወረስ ትእዛዝ ይሰጥልን ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን፡፡

ሐ. ከህዝባዊ መብታቸው ስለ ማሻር በተመለከተ


በወንጀል ህግ አንቀፅ 123 እና 124 መሰረት የፅኑ እስራት እና ከዛ በላይ የሚፈረዱ ቅጣቶች ከህዝባዊ መብት የመሻርን ሁኔታ የግድ ማስከተል እንዳለበት በመደንገጉ እና ሁሉም ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉባቸው አንቀፆች መብት መሻርን የሚያስከትሉ በመሆናቸው የመብት መሻርን ትእዛዝ ይሰጥልን ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን፡፡