Wednesday, May 22nd

English Version

Error
  • Error loading feed data.

ለ8ኛ ጊዜ የተካሄደው "ቅድሚያ ለሴቶች" የ5 ኪ.ሜ. የሴቶች ሩጫ

E-mail Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

ጠባቂው
ውሻ ጌታ ቢሆን ሰው የሱ ዘበኛ፣
ሌሊት ሲጮህ አድሮ ቀን ቀን የሚተኛ
ቤትን ለመጠበቅ ለውሻ ቢቀጠር፣ የሰው ልጅ በተራው በጩኸቱ ቢኖር
የግቢው ዘራፊ ጠባቂው በነበር፤
(ዮናስ ፈንታው፣ 2003)

*    *     *    *
ሲልቪያና ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ እንደ መንግሥት የመቀጠሏ ሁኔታ ጠፋ፤ መንበረ ሙሴው ከሥልጣን ተወግዶ ባዕዳን ኢጣሊያውያን በግራዚያ ፊትአውራሪነት ወንበሩ ለኛ ይገባል አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥት ፈረሰ፡፡ አሳዛኝ ለቅሶ፡፡ ንጉሡ አገር አልባ ሆኑ፡፡ በክብር ከነበሩባት የንግሥና መንበር ተነስተው እንደተራ ሰው ስደተኛው ባይተዋር ሆኑ፡፡

በምድረ እንግሊዝ ስደታቸው ስለአገራቸው ኢትዮጵያ መወረር አዕምሮዋ የቆሰለው ሲልቪያ ፓንክረስት እና ሌሎች 32 የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ጃንሆይ ከባቡር ሲወርዱ ንግግር አደረጉላቸው፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ መወረር እንዳሳዘናቸው እና ወረራውን ለመቀልበስ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ እነ ሲልቪያ ለጃንሆይ ተናገሩ፡፡ የጀመሩት የሰላም መንገድ ጥሩ ነው አሏቸው፡፡ በተለይም ሲልቪያ ፀረ ፋሽስት ትግሉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ድምጿን ስታሰማ ቆይታለች፡፡ እናም በስደት አንገታቸውን የደፉትን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትና ባለሟሎቻቸውን አይዟችሁ፤ ከጎናችሁ ነን፡፡ ባይተዋርነት አይሰማችሁ፡፡ ትግሉ የሁላችንም ነው ብላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ወደፊት እንዲቀጥል ትልቅ ደጀን የሆነችው ሲልቪያ ፓንክረስት ከወደ እንግሊዝ ትጠቀሳለች፡፡

New Times & Ethiopian News በተሰኘው የወቅቱ ጋዜጣ ስለ ወራሪዋ ኢጣሊያ የተለያዩ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው መጣጥፍ አቅርባለች፡፡ ሲልቪያ የምትጽፋቸውን ፀረ ፋሽታዊ መጣጥፎች በሙሉ ለእንግሊዝ መንግሥት የፓርላማ አባላት ታከፋፍል ነበር፡፡ ሁሉም በየዕለቱ ጉዳያቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲሆን ለማድረግ ያልማሰችው ጉድጓድ የለም፡፡

በምትጽፍበት New Times & Ethiopian News ጋዜጣ ላይ ስታስተጋባ የነበረው ፋሽዝም ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ እና ኢትዮጵያውያንም ነፃ እንዲወጡ የነፃነት አቀንቃኝ ሆና ነው ሲልቪያ የምትታየው፡፡

ከዚህም በመቀጠል የዓለም ሕዝብ ስለ ኢትዮጵያ የነፃነት እጦት እንዲገነዘብና ፀረ ፋሽስታዊ ትግሉ እንዲፋፋም እንግሊዝ ውስጥ ሠልፍ ጠራች፡፡ በተለይም የሴቶች እንቅስቃሴ የእንግሊዝን መንግሥት በወቅቱ ይነቀንቀው ስለነበር የሲልቪያን የሠልፍ ጥሪ በነዚሁ ሴቶች በኩል የሚደረግ ነበር፡፡ እናም እንግሊዛዊያን ፀረ ፋሽዝም የተጻፈባቸውን መፈክሮች በማንገብ ዓለም ኢትዮጵያን እንዲታደግ ሠልፍ ወጡ፡፡ አገሪቷ ከዳር እስከ ዳር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ውይይት ገባች፡፡

የሲልቪያ ትግል በመላው ሴቶች ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከመላው እንግሊዛዊ ጋር የኢትዮጵያን ጉዳይ ጉዳዩ እንዲያደርግ ከጨፍ እስከ ጫፍ የትግል መረቧን እየዘረጋች ነበር፡፡ ከቤተሰቧ ጀምሮ በወቅቱ ገና ጨቅላ የነበረው ልጅ ሪቻርድ ፓንክረስት (የዛሬው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት) ጭምር ፋሽስታዊ ተጋድሎ ውስጥ እንዲገቡ አድርጋለች፡፡
(መንደቅ መጽሔት፣2003)

*    *     *    *
ዕቁብ በመርካቶ
ዶ/ር ደጀኔ አረዶ እ.ኤ.አ በ1993 ዕቁብን በሚመለከት ባደረጉት ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ የመጀመሪያው ዕቁብ የተጀመረው ከዛሬ 62 ዓመት በፊት መምሬ ወልደ ማርያም በተባሉ የጉራጌ ተወላጅ የቤተ ክህነት ሰው አነሳሽነት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ሌሎች አጥኚዎች ደግሞ አመሠራረቱ ከዚህ ጊዜ ቀደም እንደሚል ይገልጻሉ፡፡

ያም ሆነ ይህ በመርካቶም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዕቁብ እንደ ባህላዊ የቁጠባ ተቋም ይቆጠራል፡፡ ሌቪን የተባለ ፀሐፊ እ.ኤ.አ በ1972 በታተመው መጽሐፉ ገጽ 278 ላይ እንደገለጸው ዕቁብ አባላት ሳምንታዊም ሆነ ወርሐዊ መዋጮ በመሰብሰብ በዕቁቡ ዕድሜ ውስጥ ጥቅል የሆነ ገንዘብ የሚያገኙበት ባህላዊ የቁጠባ ተቋም ነው፡፡ ሌላው ፀሐፊ ቤከር እ.ኤ.አ በ1986 በጻፈው መጽሐፍ ገጽ 163 ዕቁብን የባንክና የሎተሪ አሠራርን ያቀናጀ የቁጠባ ከለብ ነው በለት ይገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ማብራሪያዎች መገንዘብ እንደሚቻለው ዕቁብ በአጠቃላይ መልኩ ሲገለጽ አባላት በመሰባሰብ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰነ የገንዘብ መጠን በማዋጣት እያንዳንዱ አባል በየተራ የተሰበሰበውን ጥቅል ገንዘብ የሚያገኝበት የቁጠባ ማኅበር ነው፡፡ በሌላ መልኩ በመርካቶ አካባቢ የቀን ተቀን መዋጮ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ዕቁቦች ማካተቱ እየተለመደ መጥቷል፡፡

የመርካቶ ዕቁብን ከሌሎች የአዲስ አበባ ዕቁቦች ለየት የሚያደርገው አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የመዋጮ መጠን ያላቸው በርካታ ዕቁቦች መኖራቸው ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ዘመትር እሑድ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ መርካቶ ከዋናው መስጊድ ፊት ለፊት ያሉትን የሕንፃና የሱቅ በረንዳዎችን ቢቃኝ ብዙ ዕቁቦች ከአባላት መዋጮ ሲሰበስቡ ሊመለከት ይችላል፡፡ የእነዚህ ዕቁብ አባላትም ሁለቱን ፆታዎች ማለትም ወንድና ሴትን ያካተቱ ሲሆን፣ በአብዛኛው መዋጮአውም ከብር 100.00 እስከ ብር 200.00 ይደርሳል፡፡
(መርካቶ መጽሔት፣2002)

*    *     *    *
ጥቁር ሳጥን (ብላክ ቦክስ)
ብላክ ቦክስ የአውሮፕላን አደጋ ክስተትን መንስዔ ለመመርመር የሚያስችሉ ዲቫይሶች ሲሆኑ እነሱም በጋራ የበረራ ዳታ መቅረጫዎች (FDRS) እና የአውሮፕላን ጋቢና (ኮክፒት) ድምፅ መቅረጫዎች (VCR) ተብለው የሚጠሩ ክፍሎች ናቸው፡፡ በማይቀጣጠል ቁስ የተሸፈኑት፣ ከጭነት ርቀው የሚቀመጡትና ብርቱካናማ ቀለም የተቀቡት የበረራ ዳታ መመዝገቢያዎች (FDRS) እና የኮክፔት ድምፅ መቅረጫዎች ዋና ዋና የሚባሉ መረጃዎተን ማለትም አውሮፕላኑ ይበርበት የነበውን ፍጥነትና ከፍታ እንዲሁም በአብራሪዎችና በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መካከል የተደረጉ ንግግሮችን በሙሉ ቀርጸው ያስቀምጣሉ፡፡ በአየር በረራ ላይ አደጋ በማደርስበት ጊዜ የበረራ ደኅንነት መርማሪዎች ከበረራ ዳታ መቅረጫዎች (FDRS) ያገኙትን መረጃ በማሰባሰብ በኮምፒዩተር የአደጋውን ሁኔታ የሚያመላክት የሚመሰል የአውሮፕላን እንቅስቃሴ (Animation) ይሠራሉ፡፡