Sunday, May 19th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

እንዲወረስ ጥያቄ የቀረበበት የዶ/ር ብርሃኑ ንብረት አወዛገበ

E-mail Print PDF
User Rating: / 31
PoorBest 

(በታምሩ ጽጌ)

በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው የመጨረሻ ቅጣት እየተጠባበቁ ካሉት 38

 የግንቦት 7 ተከሳሾች መካከል ዐቃቤ ሕግ ንብረታቸው እንዲወረስ ክሱን እየተመለከተው ላለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ጥያቄ ካቀረበባቸው ስምንት ተከሳሾች መካከል በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ንብረት ላይ አዲስ መቃወሚያ በመቅረቡ ውዝግብ ተፈጠረ፡፡

ትናንትና ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው ንብረታቸው እንዲወረስ ጥያቄ በቀረበባቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ጽጌ ሃ/ማርያም፣ ብ/ጄ/ተፈራ ማሞ፣ አሳምነው ጽጌ፣ ጌቱ ወርቁ፣ ኮ/ል አለሁበል አማረ እና ያረጋል ይማም (ሚኪ"፤ ዐቃቤ ሕግ የብቻ ንብረታቸው መሆኑን በሰነድ የተደገፈ ማጣራት አድርጐ እንዲያቀርብ፣ ሌላ "ይመለከተኛል" የሚል አካል ካለ ማስረጃውን እንዲያቀርብና፤ በንብረቱ ላይ የመጨረሻ የቃል ክርክር ለማድረግ ቢሆንም፤ የዶ/ር ብርሃኑ ባለቤት (ዶ/ር ናርዶስ ምናሴ) ጠበቃ "ዶ/ር ብርሃኑ የብቻቸው የሚባል ንብረት የላቸውም፤ የሳቸው ንብረት የሚስታቸውም ነው፡፡ ስለዚህ አቃቤ ህግ አጣርቼ ያቀረብኩት የዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ንብረት ብቻ ነው" የሚለው ትክክል አለመሆኑን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ በማመልከታቸው ነው፡፡

በወንጀል የከሰሰው፣ ጥፋተኛ ያሰኘው ዶ/ር ብርሃኑን መሆኑን፣ ህጉም እንዲወረስ የሚያዘው የእርሳቸውን ንብረት በመሆኑ፣ "ጠበቃ ነኝ" ብለው የቀረቡት ሰው ሊከራከሩ ወይም ማንሳት የሚገባቸውን ነገር ማንሳት የሚችሉት በአፈፃፀም ጊዜ እንጅ በስረ ነገር ክርክር ላይ መቅረብ እንደማይችሉ በመግለፅ ዐቃቤ ሕግ ተቃውሞውን ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

መታየት ያለበት የዶ/ር ብርሃኑ ባለቤት በመሆኗ እንዲወረስ ጥያቄ በቀረበበት ንብረት ላይ እንደሚገባት ጥያቄ ያቀረበችውን ሰው "ባለቤት ናት አይደለችም?፣ ንብረት አላት ወይስ የላትም?" የሚለውን ገና አለማየቱን ፍርድ ቤቱ ተናግሮ፤ ጠበቃው "ሕጋዊ አይደሉም" የሚል ከሆነ ዐቃቤ ሕግ እንዲያስረዳ ጠይቋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ "የይገባኛል ጥያቄ መስተናገድ ያለበት በአፈፃፀም ወቅት ነው" ሲል፤ ፍርድ ቤቱ "ለዚህ ለዚህማ በደፈናው የግል ንብረት ይወረስ ቢባል ሌላ ክርክር ሊመጣ ነው" ካለ በኋላ፣ በንብረቱ ላይ ያገባኛል የሚል ካለ ተጣርቶ ይቅረብ ያለው ሌላ ውዝግብና ክርክር እንዳይፈጠር መሆኑን አስረድቷል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ጠበቃው ያቀረቡትን የመከራከሪያ ሀሳብ እንደማይቀበል ገልፆ፣ "ማንም ጣልቃ ገብቶ መከራከር አይችልም፡፡ እኛም አንቀበልም ፍርድ ቤቱ ያለውን ይበል፡፡ ቀድመን በሰጠነው ሀሳብ ላይ ብይን ይሰጠን" ሲል ጠይቋል፡፡

የዶ/ር ብርሃኑ ባለቤት ጠበቃ በበኩላቸው፤ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ 213/92 አንቀፅ 62 እና 63 ላይ እንደተመለከተው ንብረቱ የግል ቢባልም የባልና ሚስቶቹ የጋራ ንብረት መሆኑና ዐቃቤ ሕግ ባመለከተው መሠረት ፍፃሜ ቢያገኝ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ዶ/ር ናርዶስ ምናሴ በጋራ የወለዷቸው ልጆች መኖራቸውን ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ አስረድተው፣ ለልጆቹ ማሳደጊያ አስፈላጊ በመሆኑ ንብረቱ እንደሚመለከታቸው አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ ሰዎች ባልና ሚስት ስለመሆናቸው ካቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ጋር የጋብቻ ሰርተፍኬታቸውን አያይዘው ማቅረባቸውን ጠበቃው ሲናገሩ፤ ፍርድ ቤቱ በመሀል፣ ሚስትየዋ አገር ውስጥ እንደሌሉ በመጥቀስ፣ እንዴት ሊወክሏቸው እንደቻሉ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል፡፡

ዶ/ር ናርዶስ በውልና ማስረጃ ሙሉ ውክልና የሰጧቸው ተወካይ እርሳቸውን (ጠበቃውን) እንደወከሏቸው ሲናገሩ፣ ዐቃቤ ሕግ በመሀል "ጠበቃው ሊከራከሩ የሚያስችላቸው ቢሆን እንኳን መከራከር የሚችሉት ሙሉ ውክልና ሲኖራቸው ነው" በማለት የዶ/ር ናርዶስ ጉዳይ መታየት ያለበት በአፈፃፀም ጊዜ መሆኑን በማስረዳት ተቃውሟል፡፡

"አፈፃፀም ማለት ምን ማለት ነው?" በማለት ፍርድ ቤቱ ጠይቆ፤ ለጥያቄው ራሱ ምላሽ ከሰጠ በኋላ፤ አንድ ነገር የሚፈፀመው ፍርድ ቤት በወሰነው ነገር ላይ መሆኑንና ይኸም ሕግ መሆኑን በመግለፅ ሚስት በባል ንብረት ላይ መብት እንዳላት አስረድቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ "በዶ/ር ብርሃኑ ስም የተመዘገበ ንብረት አንፈልግም ከሆነ ደብዳቤ ፃፍልን" ሲል፤ "እያልን ያለነው ቀደም ብለን ባቀረብነው ላይ ብይን ይሰጠን ነው፡፡ ይመለከተናል ካለ (ከብይን በኋላ" መጥቶ መከራከር ይችላል በማለት ዐቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ተወካይ ቀረበም አልቀረበም፣ ሚስትን፣ ልጆችንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች ፍርድ ቤቱ ሰነዶችን በሚመረምርበት ወቅት ሊያልፈው እንደማይችል በመናገር፣ ከዛ በፊት ግን ነገሮች ግልፅ ሆነውና ጠርተው መቅረብ ስለሚያስፈልጋቸው መሆኑንም ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

የተወካይ ተወካይ (የዶ/ር ናርዶስ ተወካይ ነኝ ያሉትን ጠበቃ) ጣልቃ ገብቶ ሊከራከራቸው እንደማይችል ዐቃቤ ሕግ ተናግሮ "መጀመሪያ ቀደም ብለን ባስያዝነው ላይ ብይን ይሰጠን" ሲል፤ ፍርድ ቤቱ "ብይን ማለት ምን ማለት ነው?፣ ብይን የሚሰጠው በየትኛው ጭብጥ ላይ ነው?" በማለት ከጠየቀ በኋላ "ንብረቱ ይወረስ አይወረስ ገና አልተወሰነም" በማለት ተናግሯል፡፡

ዐቃቤ ሕግ እያስከበረ ያለው የሕዝብ ጥቅም መሆኑን በመግለፅ፣ የሚቃወም ከሆነ እንዲቃወም የሚስማማ ከሆነ እንዲስማማ፤ ለማስረጃነት የቀረቡት (በስምንቱም ተከሳሾች ላይ) ዋና ሰነድ (ኦርጂናል) ተሰጥቶት ለማመሳከር ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ሌላው በዕለቱ"ትናንትና) ከደረሱት የ36ኛ ተከሳሽ (አቶ ጌቱ ወርቁ) የንብረት መቃወሚያ ላይ መልስ መስጠት እንደሚችል ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ የተቃውሞ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሕዳር 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ዐቃቤ ሕግ የአቶ ጌቱ ወርቁን ንብረት በተመለከተ ባቀረበው ማስረጃ ላይ "ዐቃቤ ሕግ ጥቅምት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. እንዲታገድለት አቅርቦት ከነበረው ንብረት በተጨማሪ ሌላ ንብረት ማቅረብ አይችልም" በሚል በቀረበው መቃወሚያ ላይ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

አቶ ጌቱ ያላቸው ንብረት ለጊዜው እንዲታገድለት እንጂ በዝርዝር ያላቀረበ በመሆኑ (በመጀመሪያው ይታገድልኝ አቤቱታው) በድጋሚ ሲያቀርብ በዝርዝር ማቅረቡን፣ በማህበር የሰሩት አይደለም የተባለውን ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ማስረጃ ማግኘቱንና በወንጀል ሕግ አንቀፅ 98"3) መሠረት፣ የልጆችንና የሚስትን የሚመለከት ንብረት ስላልነካ የቀረበበት መቃወሚያ ውድቅ እንዲደረግለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የተከሳሽ ጠበቃ (የ36ኛ) በበኩላቸው፣ "ዐቃቤ ሕግ ያቀረብነውን መቃወሚያ ተረድቶት ከሆነ ያነሳነው የእግድ ጉዳይ አይደለም" በማለት፤ ህዳር 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ያቀረበው ንብረት ቀደም ብሎ ጥቅምት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. እንዲታገድለት ከጠየቀው ውጭ ያቀረበውን ንብረት ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ "በፅሁፍ ያቀረባችሁትን መቃወሚያ እንመለከተዋለን፤ ሌላውን በቃል ክርክር ወቅት ታደርጋላችሁ" በማለት ሰነዶቹን አመሳክሮና ትክክለኛነቱን አጣርቶ (ዐቃቤ ሕግ) ለማቅረብ ተለዋጭ አጭር ቀጠሮ እንያዝ ሲል የዶ/ር ናርዶስ ጠበቃና የአቶ ጌቱ ጠበቃ ረዘም ያለ ጊዜ ጠይቀዋል፡፡

የዶ/ር ናርዶስ ጠበቃ፣ ደንበኛቸው አሜሪካን አገር እንደሚኖሩና (አሜሪካዊም ናቸው) ኦርጂናል ዶክመንት እስከሚመጣ ረዘም ያለ ጊዜእንዲሰጣቸው ሲጠይቁ፣ የ36ኛ ጠበቃም፤ የተከሳሹ ባለቤት በቅርቡ ወደ ውጭ ስለሄዱ በማለት ተመሳሳይ አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከውጭ ይመጣል ስለተባለው ማስረጃና፣ የዶ/ር ናርዶስ ጠበቃ "ህጋዊ ናቸው አይደሉም፤ ውክልና የሰጣቸው አካል ሥልጣን አለው ወይስ የለውም" የሚለውን ዐቃቤ ሕግ በቀረቡት "ይመለከተኛል" ሰነዶች ላይ ኀሳብ ከሰጠ በኋላ እንደሚታዩ በመግለፅ፣ ዐቃቤ ሕግ ሰነዶችን አመሳክሮ ሀሳብ እንዲሰጥ ሁሉም "ይመለከተኛል" በሚል ሰነድ ያስገባ ትናንትና፣ ዛሬና ነገ ኦርጂናሉን ይዞ በመቅረብ ሬጅስትራር ቢሮ እንዲያመሳክርና ዐቃቤ ሕግ ሁሉንም ሰነዶች መረጋገጣቸውን በማየት ሀሳቡን ለታህሳስ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. ይዞ እንዲቀርብ የመጨረሻ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡