Friday, May 24th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

‹‹አንዳንድ ቀንማ . . . ››

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

ሰው ተሰበሰበ አንድ ሁለት እያለ
አዳራሹ ሞላ ሞቅ ደመቅ አለ
መድረኩ አሸብርቆ መብራት ብልጭ ድርግም

ሙከራ አንድ ሁለት ማጉያው ድም ድም
ሽር ጉድ እያሉ መድረክ አዘጋጆች
ቦታ ቦታ ያዙ ተጋባዥ እንግዶች፡፡
የመድረኩ መሪ ጉሮሮውን ጠርጎ
ሰላምታ ሰጠና ድምፁን ከፍ አድርጎ
በሳቅ እያዋዛ ገለጸ ዓላማውን
የዝግጅቱን ግብ ጠቅላላ መልዕክቱን
እንድትጨብጡ ነው በቂ ግንዛቤ
ስለኤችአይቪ ኤድስ የአዘጋጁ እሳቤ፡፡
ከዚያም መብራት ጠፋ ሸራው ብቻ በራ
ፊልሙ ተከፈተ ገድሉ ሊዘከዘክ የኤችአይቪ ሥራ
ታየ ብዙ ብዙ
ከመነሻው አንስቶ እስከነመዘዙ
ሙዚቃም ታከለ ‹‹ማለባበስ ይብቃ››
ግንዛቤ አገኘ ሰውም ተነቃቃ፡፡
በባለሙያዎች ተሰጠ ማብራሪያ
ስላለበት እርከን ስለ ቁጥሩ ጣሪያ
መድኃኒት የለውም እያሉ ገለጡ
ወጣቱን መከሩ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡
መታቀብ እያሉ መፈክር አሰሙ
ዝግጅቱ አለቀ ሁሉ አንድነት ቆሙ
የህሊና ፀሎት ተደርጎ ላለፉት
ደግሞ ተቀመጡ ዘና ሊሉ ጥቂት
የመዝጊያውም ዘፈን ሙዚቃ ተሰማ
ዘፋኞቹም ቆሙ መሰንቆውን ይዞ ወገቧን አሽማ
ጭብጨባው ቀለጠ ናኘ ጣዕመ ዜማ
‹‹አንዳንድ ቀንማ አንዳንድ ቀንማ ይሻላል ውሽማ፡፡››
(አይዳ ታደሰ፤ አልረግምሽም፣2003)

*      *         *
‹‹የሚሌኒየሙ ምርጥ አባባሎች››
- ሥራ የፈታ አዕምሮ የሰይጣን ፋብሪካ ነው
(ረቂቅ አሻራ)
- ሕይወት የግዴታዎች ሰንሰለት ናት፡፡ (ኦሮማይ)
-  ቅናት ከፍቅር ጋር አብሮ ይወለዳል፣ ነገር ግን አብሮት አይሞትም፡፡
(የቅናት ዘር)
- አስቀድሞ የበሰለ ፍሬ አስቀድሞ ይጠፋል፡፡
(ጣምራ ጦር)
-   እግዚአብሔር ይመስገን ፍቅርም ሀዘንም በቶሎ ያልፋሉ፡፡
(በርትል)
- አፍንጫ ሥር ያለውን ነገር ለመመልከት ዘላቂ ትግል ያስፈልጋል፡፡
-  ነፃነት ማለት ኃላፊነት ነው፡፡ ስለዚህም ነው ብዙ ሰዎች የሚፈሩት፡፡
(ቤንጃሚን ፍራንክሊን)
-  እያንዳንዱ ትውልድ በአባቶች ላይ ያምፃል ከአያቶች ጋር ያብራል፡፡ ከፈለጉ እሺ ካልፈለጉ አልፈልግም ይበሉ እንጁ ተፈቀርኩ ብለው አይመጻደቁ፡፡
(የንስር ዓይን)
- የሞኝ ሰው ልቡ አፉ ነው፡፡ የብልህ ሰው አፉ ግን ልቡ ነው፡፡
(ፍራንክሊን)
(ምርጥነህ ታምራት፤ጣዝማ፣2000)


*      *         *
እንቆቅልህ

እንቆቅልህ ወይም እንቆቅልሽ ማለት ከቀን ብዛት አነጋገሩ ተለውጦ ነው እንጂ ዕንቁላል አለህ ወይም እንቁላል አለሽ ማለት ነው፡፡ ዕንቁላል ድፍን በመሆኑ በውስጡ ያለው ጫጩት ወንድ ይሁን ወይም ሴት ትሁን ከቅፍቀፋው ወይም ከፍልፈላው በፊት ሊታወቅ ባለመቻሉ የተሰወረና የተደበቀ ምስጢር መጠያየቂያና መፈታተኛ ሆኖ ሲያፋትን ይኖራል፡፡
(ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፤ ከሥራ በኋላ ሥራ ስትፈቱ እንቆቅልሽ ተጫወቱ፣1943)

*      *         *

ስለ ቢልጌትስ አንዳንድ እውነታዎች
•    ቢልጌትስ በየሰከንዱ 250 ዶላር፣ በየቀኑ 2 ሚሊዮን ዶላር፣ በዓመት ደግሞ 7.8 ቢሊዮን ዶላር ያገኛል፡፡
•    አንድ ሺሕ ዶላር በመሬት ላይ ቢወድቅበት ዞር ብሎ እንኳን ለማየት ግድ አይኖረውም ይባላል፡፡ ምክንያቱም የወደቀበትን ገንዘብ ለማንሳት የሚያጎነብስበት አራት ሰከንድ ጊዜ ውስጥ አንድ ሺሕ ዶላር ስለሚያገኝ ነው፡፡
•    የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ 5.62 ትሪሊየን ይደርሳል፡፡ ቢል ጌትስ ይህን እዳ ለብቻዬ ልክፈል ብሎ ቢነሳ ከ10 ዓመት ያነሰ ጊዜ ይፈጅበታል፡፡
•    ቢል ጌትስ በዓለም ላይ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው 15 ዶላር ቢሰጥ በእጁ ላይ 5 ሚሊዮን ዶላር ይቀረዋል፡፡
•    በአሜካ የአትሌት ክፍያ ታሪክ ከፍተኛ ተከፋይ የነበው ማይክል ጆርዳን ሳይበላና ሳይጠጣ በዓመት የሚያገኛትን 30 ሚሊዮን ዶላር እያንዳንዷን ሳንቲም ቢያስቀምጥ የቢል ጌትስን የመሰለ ሀብት ለማጠራቀም 277 ዓመታትን ይፈጅበታል ተብሏል፡፡
•    ቢል ጌትስ አገር ቢሆን ኖሮ የዓለማችን 37ኛ ሀብታም አገር ሊሆን ይችል ነበር፡፡
•    ቢል ጌትስ ያለውን ገንዘብ በሙሉ በባለ 1 ዶላር ኖት ቢመነዝረው፣ ከምድር እስከ ጨረቃ የሚደርስ 14 መስመር የደርሶ መልስ መንገድ መሥራት ይችላል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡን በማመላለስ ይህን መንገድ ለመገንባት 1400 ዓመታትና ቦይንግ 747 የተሰኙ 713 አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ፡፡
•    ቢል ጌትስ እስከ 75 ዓመት ድረስ ለመኖር ቢታደልና ገንዘቡን በሙሉ ከእለተ ሞቱ በፊት ተጠቅሞ ይጨርሰው ቢባል በየቀኑ 6.78 ሚሊዮን ዶላር ማውጣት ይኖርበት ነበር፡፡
•    የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎች በኮምፒውተሮቻቸው ዊንዶውስ ችግር የተነሳ ሥራ በሚያቆሙበት በእያንዳንዱ ወቀት አንድ ዶላር ከማይክሮሶፍት ቢከፈላቸው ኖሮ ቢልጌትስ በሦስት ዓመታት ውስጥ ለኪሳራ ይዳረግ ነበር፡፡
(ሰላምታ መጽሔት)

*      *         *

‹‹‘ማን ፉል አለ’? አላችሁ?››

በኢትዮጵያ የኮሜዲያን ሥራ ትልቅ ሥፍራ የነበረውና ከዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተስፋዬ ካሳ ቀጥሎ ያለችውን ቀልድ አቅርቦ ነበር፡፡

የትምህርት በሬዲዮ አቅራቢው ለተማሪዎች ስለ ኤሌክትሪክ ቻርጆች እያስረዱ ነበር፡፡ እናም ሁለት የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ሲገናኙ ምን እንደሚፈጥሩ ለማስረዳት፣ ‹‹መምህር፣ እባክዎ ሁለቱን ገመዶች አንዱ በግራ፣ ሌላውን ደግሞ በቀኝ እጆችዎ ይያዙ›› ይሉና ለተወሰኑ ሰከንዶች ዝም ይላሉ፡፡ ይህን የታዘዙት መምህር ድርጊቱን ሲፈጽሙ ለካ ኤሌክትሪኩ ጮኾ ጠረጴዛ ስር ወርውሯቸዋል፡፡ ሁኔታውን ደግሞ ሁሉም ተማሪዎች አይተዋል፡፡

የሬዲዮ ትምህርት አቅራቢው ከጥቂት ዝምታቸው በኋላ፣ ‹‹በጣም ጥሩ መምህር! አሁን ደግሞ ተማሪዎች እንደ መምህራችሁ ሞክሩ›› አሉና በድጋሚ ለሰከንዶች ዝም አሉ፡፡ ከዝምታቸው ቀጥለው ‹‹ተማሪዎች ‘ማን ፉል አለ?’ አላችሁ?›› አሏቸው፡፡
(አጋርነት ለልማት ጥር 2003)

*      *         *
ፈተና

በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ አንድ ሰው ለተፈለገበት መደብ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ወጥቶ በርካታ ሥራ ፈላጊዎች ይመዘገባሉ፡፡ ከብዙዎቹ ግን በመጨረሻው ዙር የደረሱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከጥቂቶቹ ደግሞ በተያዩ መስፈርቶች ተጣርተው ሁለት ይቀራሉ፡፡

የመጨረሻዎቹ ተፈታኞች ወንድና ሴት ነበሩና አንድ ላይ ፈታኙ ፊት እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ ፈታኙ ቀድሞውኑም ቀልባቸው ልጅቱ ላይ አርፎ ኖሮ መጀመሪያ ሴቷን፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ስንት ነው›› አሏት፡፡ ልጅቱም ሳትቆይ ‹‹75 ሚሊዮን›› ትላለች፡፡ ቀጠሉና ወንዱን ተፈታኝ ‹‹አንተ ደግሞ ስማቸውን ጥራ›› ብለው ለዩት፡፡
(ዘመን መጽሔት መጋቢት 2001)

*      *         *

ኮሶ በሻኪሶ
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሻኪሶ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባት ቦታ ነበረች፡፡ ቦታዋ ወርቅና የተለያዩ ማዕድናት የሚገኙበት በመሆንዋ ማንም ሰው ያለፈቃድ ወደ ከተማዋ አይገባምና የገባም ዝም ብሎ አይወጣም፡፡ ሻኪሶን ከአዶላ መረዳ ከሚያገኛኘው አዋጣ ወንዝ አጠገብ የተቋቋመው ኬላ ገቢና ወጪው ሕዝብ ይፈተሽበት /ይመረመርበት ነበር፡፡ ዘመዱን ለመጠየቅ ሻኪሶ የመጣ እንግዳ እንኳ ወደ ኬላው ሲደርስ የመጣበትን ዓላማ አስረድቶና መታወቂያውን አስይዞና የርሱንና የዘመዶቹን ስም አስመዝግቦ ፈቃድና የጊዜ ገደብ ከተሰጠው በኋላ ነበር የሚገባው፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከሻኪሶ ሲወጣ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ወርቅ ደብቆ እንዳይወጣ ጥብቅ ፍተሻ ይደረግበታል፡፡ ከዚህም በላይ ወርቁን ሊውጠው ይችላል ተብሎ ስለሚታሰብ ከከተማዋ መውጫ ወደሆነው ኬላ እንዲደርስ ኮሶ እንዲጠጣ ይደረግና የኮሶው ውጤት ከታየ በኋላ ነፃ ከሆነ ይለቀቅ ነበር፡፡
(ሐመር መጽሔት፤2001)

*      *         *
ከበር
የኋላ እግር የሌለው ፍየል በፊት እግሩ መራመድ ቻለ

በቻይና የተወለደውና የኋላ እግር የሌለው ፍየል በፊት እግሩ ብቻ መራመድ በመቻሉ ዝናን እያተረፈ ነው፡፡

የፍየሉ ባለቤት የሆነው የንግ ያንግ የሦስት ወር እድሜ ያለው ፍየል የኋላ እግር ስለሌለው ሁሌም ተኘቶ ያሳልፍ ነበር፡፡ አሁን ግን ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ በፊት እግሮቹ እየዘለለ መራመድ ጀምሯል ብሏል፡፡

አኖኖቫ ድረ ገጽ እንደዘገበው፣ ፍየሉ ለመራመድ በሚያደርገው ጥረት አልሳካ ሲለው መሬት ይመታ፣ ያሳዝንም ነበር፡፡ መራመድ በማይችልበት ጊዜ ጡት እንዲጠባ ሚ/ር ያንግና ሚስቱ ፍየሉን ይረዱት ነበር፡፡ አሁን ግን እናቱ ምግብ ፍለጋ በሔደችበት ሁሉ ይከተላታል፡፡