Wednesday, Jun 19th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

የተመድ አውሮፕላን ተከስክሶ 32 ሰዎች ሞቱ

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ ከነበሩት 33 ሰዎች 32ቱ ሲሞቱ አንዱ ብቻ መትረፉን የዘገበው ሲኤንኤን ነው፡፡ አውሮፕላኑ አደጋው የደረሰበት በወቅቱ በነበረው ከባድ ነፋስ ሳቢያ እንደነበር ታውቋል፡፡ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በምትገኘው ጎይ ከተማ ተነስቶ ኪንሻሳ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ የኪንሻሳ አውሮፕላን ማረፊያ በወቅቱ የነበረው አውሎ ነፋስ 37 ኪሎ ሜትር በሰዓት ይጓዝ እንደነበር ገልጿል፡፡ በአደጋው ሰለባ ከሆኑት መካከል አብዛኛዎቹ የተመድ ሠራተኞች ሲሆኑ፣ አምስቱ ግን ለሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡ አደጋውን በተመለከተ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚካሄድ መገለጹንም ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል፡፡

*     *     *       *
የአፍጋኒስታን ተማሪዎች አሜሪካን ተቃውመው ሠልፍ ወጡ
በመቶዎች የሚቆጠሩ የአፍጋኒስታን ተማሪዎች በቅርቡ በአሜሪካ ቁርአን መቃጠሉን በመቃወም በካቡል ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት ሠልፍ መውጣታቸውን ዥንዋ ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ የሚገኙ አንድ ቄስ ቁርአንን ቅደዳቸውን አስመልክቶ ሰላማዊ ሠልፍ ሲደረግ የአሁኑ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ትናንት በተደረገው ሠልፍ አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች ተማሪዎች ቢሆኑም፣ እነሱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎችም የተቃውሞ ሠልፉን መቀላቀላቸው ታይቷል፡፡ ባለፈው ዓርብ በተመድ ቅጥር አካባቢ የተደረገው ሰላማዊ ሠልፍ ወደ ብጥብጥ ተቀይሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 28 ቆስለዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በደቡባዊ ካንደሃር በተነሳው ብጥብጥ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

*     *     *       *
በታይላንድ የጐርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 51 ደርሷል
በታይላንድ ደቡባዊ ክፍል በተነሳው የጐርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 51 መድረሱን የመንግሥት ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ የአገሪቱ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ እንደገለጸው ከሆነ፣ አደጋው 10 ክልሎችን ያጠቃ ሲሆን፣ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችንም ለጉዳት ዳርጓል፡፡ ጐርፉ ያደረሰው ጉዳት በትክክል ባይታወቅም ለመልሶ ማቋቋም ግን 146 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት የተነሳው ይኼው የጐርፍ አደጋ ወቅታዊ እንዳልነበረ ያመለከተው ዘገባው፣ አሁን ወቅቱ ሞቃታማ በመሆኑ አደጋውን ያልተጠበቀ አድርጐታል፡፡

*     *     *       *
የጋዳፊ ልጆች አባታቸው ከሥልጣን እንዲወርዱ ይፈልጋሉ ተባለ
ከሊቢያው መሪ ሙአመር ጋዳፊ ወንድ ልጆች መካከል ሁለቱ አባታቸው ከሥልጣን ወርደው አገሪቱ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር እንደሚፈልጉ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡ ዘገባው ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈሉጉን የሊቢያ ዲፕሎማቶች ጠቅሶ እንዳመለከተው፣ የተጠቀሰውን የሥልጣን ሽግግር ሐሳብ ያራመዱት ሳይፍ አል ኢስላም የተባሉት ልጃቸው እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ሰዓድ ኤል ጋዳፊ የተባሉት ሌላው ልጃቸውም ይህንኑ ሐሳብ እንደሚደግፉት ተጠቁሟል፡፡ ጋዳፊም የልጆቻቸውን ሐሳብ መቀበላቸውን ባይናገሩም ሐሳቡን ግን ሳይቀበሉ እንዳልቀሩ መጠቆሙን ዘገባው አመልክቷል፡፡