Friday, May 24th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

‹‹ታሪክና ምሳሌ›› ከገላጭ ሥዕሎች ጋር ቀረበ

E-mail Print PDF
User Rating: / 5
PoorBest 

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለሦስተኛ ክፍል የአማርኛ መማርያ የነበረው የደራሲ ከበደ ሚካኤል ‹‹ታሪክና ምሳሌ›› ሦስት ግጥሞች በሥዕላዊ መግለጫ ተቀናብረው በአንድ መጽሐፍ ለገበያ ቀረቡ፡፡ ለሕፃናት እያዝናኑ ትምህርት የሚሰጡ ስቲከሮች ባሉበት መጽሐፍ ላይ የወጡት ግጥሞች፣ ‹‹ፋኖስና ብርጭቆ››፣ ‹‹የሸክላ ድስትና የብረት ድስት››፣ ‹‹የሾላ ፍሬና የዱባ ፍሬ›› የተሰኙት ናቸው፡፡

በሸክላ ስቱዲዮ አማካይነት የታተመው መጽሐፍ ለሕፃናትና ለአዋቂዎች በሚያመች መልኩ በሥዕል ተቀናብሮ መቅረቡን ተቋሙ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የአቶ ከበደ ሚካኤልን (የክብር ዶክተር) ግጥሞች በሥዕል አቀናብሮ ለማሳተም ከከበደ ሚካኤል ፋውንዴሽን ፈቃድ የተሰጠው መሆኑንም አክሎ ገልጿል፡፡