Friday, May 24th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

የኤፍሬም እንዳለ ሦስተኛው የ‹‹እንጨዋወት›› መድበል

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

 

በጋዜጣው ሪፖርተር

የጋዜጠኛ፣ ደራሲና ተርጓሚ ኤፍሬም እንዳለ ሦስተኛው የእንጨዋወት መድበል ለአንባብያን ቀረበ፡፡ ይህ ባለፈው ሐሙስ በይፋ በገበያ ላይ የዋለው መድበል በ47 የተለያዩ ርእሶች ሥር የተሰናዱ አዝናኝ መጣጥፎችን ይዟል፡፡

‹‹ጽሑፎቹ በተለያዩ ወቅቶች የተዘጋጁ እንደመሆናቸው በአብዛኛው በተጻፉበት ጊዜ የነበሩ ክሥተቶችን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከጥቃቅን ማስተካከያዎች በስተቀር እምብዛም ለውጦች አልተደረጉባቸውም፡፡ አንባብያንም የተጻፉባቸውን ወቅቶች እያሰባችሁ አንብቡልኝማ፤›› ሲል ኤፍሬም ማሳሰቢያውን በመድበሉ ላይ አስተላልፏል፡፡

በ195 ገጾች የተዘጋጀው እንጨዋወት ቅጽ 3፣ ‹‹ቢያንስ ቢያንስ፣ እልል በሉለት፣ የአምናን ቀን ረገምኩት፣ የማንቼን ለበስኩ እንጂ...በልቤ የቼልሲ ነኝ፣ ከመከካት ወደ ‘መፍጨት' የዕውቀት ሽግግር፣ ኳሷን ካጣህ እግሩን፣ ሰበበኛ ከንፈር ከማማሩ የማበጡ፣ አናውቅሽምና ነው፣ ወዘተ.›› በሚሉ ርእሶች የተዘጋጁ በርካታ አዝናኝ ጽሑፎችን አጭቋል፡፡

ከዚህ ቀደም እንጨዋወትን በሁለት መድበሎች ያዘጋጀው ኤፍሬም፣ ሁለት የልብ ወለድ ሥራዎችን፣ ስድስት ትርጉሞችንና አምስት ሌሎች ሥራዎችን (ቀልድና የእንግሊዝኛ ማስተማሪያ መጻሕፍትን) ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡