አጫጭር ዜናዎች - Briefs
ከ14 ሺሕ ኩንታል በላይ የቅባትና ጥራጥሬ ምርት ወደ ውጭ ተላከ
በኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን የሰሜን ምሥራቅ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለፉት ሦስት ወራት 14,780 ሺሕ ኩንታል የቅባትና ጥራጥሬ ምርት ጥራቱ ተጠብቆ ወደ ውጭ አገር መላኩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Read more...
የናይጄሪያ ወታደሮች ታጋቾችን አስለቀቁ
የናይጄሪያ ወታደራዊ ኃይሎች በዚህ ወር ብቻ በኒጀር ዴልታ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 19 ታጋቾችን ማስለቀቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ ከታጋቾቹ ውስጥ 12 የሚሆኑት ናይጄሪያውያን ሲሆኑ ሁለቱ አሜሪካውያን፣ ሁለቱ ፈረንሳውያን፣ ሁለቱ ኢንዶኔዥያውያንና አንድ ካናዳዊ ነበሩ፡፡
Read more...
ኮርፖሬሽኑ አነስተኛ ትራክተሮችን ሊያመርት ነው
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በአርሶ አደር ደረጃ በተበጣጠሰ መሬት ላይ የሚሠሩ አነስተኛ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራንክተሮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያመርት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Read more...
ደቡብ አፍሪካ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ሕክምና መገልገያነት ለወጠች
ደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ዘመን የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ካንሰርንና የልብ በሽታን ለመመርመር ወደሚያስችሉ መሣሪያዎች መለወጧን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
Read more...
የጣሊያን መንግሥት የ8.2 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ ሰጠ
የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከጣሊያን መንግሥት ጋር አገሪቱ በጤናው መስክ ለምታከናውናቸው ተግባራት የሚውል የ8.2 ሚሊዮን ዩሮ የዕርዳታ ስምምነት መፈራረሙን የአዲስ ዘመን ዘገባ ያስረዳል፡፡
Read more...
የደቡብ ኮሪያ የጦር መርከብ ሰጠመች
የደቡብ ኮሪያ የጦር መርከብ ከዓሣ አጥማጅ መርከብ ጋር ተጋጭታ በመስጠሟ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም፡፡
Read more...
ቤተክርስቲያኗ በመቃብር ሥፍራ ለሚኖሩ የኮንዶሚኒየም ቤት ገዛች
በመቃብር ሥፍራ ለሚኖሩ 60 አባወራዎች የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በአምስት ሚሊዮን ብር ወጪ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በመግዛት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረጓን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Read more...
ካስትሮ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፓርቲያቸው አባላት ጥሪ አቀረቡ
የኩባው ፕሬዚዳንት ራኦል ካስትሮ ከ14 ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን የገዢውን ኮሚዩኒስት ፓርቲ ኮንግረንስ መጥራታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
Read more...
ባለሥልጣኑ 11 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ሰበሰበ
በሩብ የበጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ10.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ማስታወቁን ዋልታ ዘገበ፡፡
Read more...
የእሳት ተራራው በተፋው እሳት በርካቶች ሞቱ
በኢንዶኔዢያ ‹‹የእሳት ተራራ›› (ማውንት ሜራፒ) በሚል ስያሜ ከሚጠራው ተራራ በተነሳ እሳተ ገሞራ ከ100 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ፡፡
Read more...
More Articles...
Page 9 of 28


