Sunday, May 26th

English Version

Error
  • Error loading feed data.

በህግ አምላክ - Law

በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የሕመም ፈቃድ እንዴት ይታያል?

E-mail Print PDF

(በዮሴፍ ጌታቸው፣ የሕግ ጥናት ማርቀቅ፣
ትምህርት፣ ሥልጠና እና ምክር ባለሙያ)

በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የሕመም ፈቃድ አቆጣጠርን አስመልክቶ ሕጉ ምን ይላል? እንዴትስ ይቆጠራል? በሚል ጽሑፍ በማዘጋጀት የላኩላችሁ ከድሬዳዋ አስተዳደር ፍትሕ፣ ፀጥታና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ ባለሙያ ነኝ፡፡

Read more...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999

E-mail Print PDF

5. የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አጠቃቀም ሁኔታዎች

1.    በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የሚጠቀም ታክስ ከፋይ፤
ሀ. በዚህ ደንብ አንቀጽ 16 መሠረት የሚሰጠውን በመሣሪያው ለመጠቀም     የሚያስችል ፈቃድ በቅድሚያ ማግኘት አለበት፤

Read more...

የውል መሰረዝን የተመለከተ የሰበር ሰሚ ፍርድ

E-mail Print PDF

የውል መሰረዝ ሊከሰት የሚችለው በአፈጻጸሙ ጊዜ ተዋዋዮች በሚፈጥሩት ችግር ነው፡፡ ከተዋዋዮቹ ወገን አንደኛው ግዴታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ለመወጣት ባልቻለ ጊዜ፣ ውሉን ያከበረው ወገን ውሉን የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ውልን መሰረዝ የውሉ ግዴታ ባለመፈጸሙ ምክንያት ውሉን ያከበረው ወገን በሕግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት መሠረት ውሉን ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግበት አጋጣሚ ነው፡፡

Read more...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999

E-mail Print PDF

ክፍል ሁለት
የግብር ከፋይ ግዴታዎች


3. በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች የመጠቀም ግዴታ
በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ ዝርዝራቸው የሚወሰን ታክስ ከፋዮች በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት ዕውቅና የተሰጣቸውን የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች በመጠቀም በዚህ ደንብ አንቀጽ 4 መሠረት የሽያጭ ደረሰኞችን አዘጋጅተው የማውጣት ግዴታ አለባቸው፡፡

Read more...

“ሃይማኖታዊ ፕሬሶች ብዙ ትኩረት የማይሰጣቸው ነገር ግን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የሚካሄድባቸው ናቸው”

E-mail Print PDF

በሔኖክ ያሬድ

ሃይማኖታዊ (መንፈሳዊ) ፕሬሶች ወይም በእምነት ሥር የሚሰጡ መግለጫዎች ብዙ ትኩረት የማይሰጣቸው ነገር ግን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የሚካሄድባቸው ቦታዎች ሆነው መገኘታቸውን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

Read more...

በምርጫ ሒደት የሚነሱ አቤቱታዎች እና ክርክሮች

E-mail Print PDF

በዮሴፍ ሳህለሥላሴ

የምርጫ ሒደት የተራራቁና የተለያዩ ሀሳቦች የሚስተናገዱበት መድረክ በመሆኑ፣ የተለያዩ አለመግባባቶች እንደሚፈጠር መገመት አያዳግትም፡፡ የተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 በምርጫ ሒደት የሚነሱ አቤቱታዎችንና ክርክሮችን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡ የምርጫ ሕጉ በመራጮች ምዝገባ ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎች፣ በዕጩዎች ምዝገባ ሒደት የሚነሱ ቅሬታዎች፣ በድምፅ አሰጣጥ ሒደት የሚነሱ ቅሬታዎች እና በቆጠራ ሒደት እና ውጤት የሚነሱ ክርክሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችን አስቀምጧል፡፡

Read more...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999

E-mail Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች ስለመጠቀም ግዴታ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ፡-

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 471/1998 አንቀጽ 5፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 84 እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 117 መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ


1. አጭር ርዕስ


ይህ ደንብ "በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች ስለ መጠቀም ግዴታ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፣
1. "የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ" ማለት የጥሬ ገንዘብ መመዝገቢያ መሣሪያ ወይም የሽያጭ ነቁጣ መሣሪያ ነው፣
2. "የጥሬ ገንዘብ መመዝገቢያ መሣሪያ" ማለት በሽያጭ መደበኛ ደረሰኝ ፋንታ የሸቀጦችን ወይም የአገልግሎቶችን ሽያጭ የሚመዘግብና ለማንበብ ብቻ የሚቻል ማስታወሻን የሚያከማች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ፕሮግራም የሚደረግ ቺፕ የተገጠመበት በሰርክዩት የተጋገረ ፕሮግራም የሚጠቀም መሣሪያ ነው፤
3. "ደረሰኝ" ማለት የጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ደረሰኝ ሲሆን፣ የዱቤ ሽያጭ ኢንቮይስንና ያለ ክፍያ የሚሰጥ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ማስተላለፊያ ደረሰኝን ይጨምራል፤
4. "በሰርክዩት የተጋገረ ፕሮግራም" ማለት በማይቀያየር ማስታወሻ ላይ የሚጫን በትክክል ተለይቶ የተቀመጠን ሥራ ለማደራጀት እንዲያገለግል የተዘጋጀ ፕሮግራም ነው፤
5. "የማይቀያየር ማስታወሻ" ማለት ኃይል ቢቋረጥም ተይዞ የቆየው መረጃ ተጠብቆ የሚቆይበት ማስታወሻ ነው፤
6. "የሽያጭ ነቁጣ መሣሪያ" ማለት የጥሬ ገንዘብ መመዝገቢያ መሣሪያን የሚተካ ኮምፒውተራይዝድ የሆነ መሣሪያ ሲሆን፣ የደንበኞችን ትዕዛዝ፣ የትዕዛዙን አፈፃፀም ሂደትና የዴቢትና የክሬዲት ካርድ ሂሣብን የመመዝገብና የመከታተል፣ በክምችት ያለን ዕቃ የመቆጣጠርና የመሳሰሉትን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችል ተጨማሪ አቅም ያለው መሣሪያ ነው፤
7. "ታክስ" ማለት የተጨማሪ እሴት ታክስንና የገቢ ግብርን ያጠቃልላል፤
8. "ሚኒስቴር " እና "ሚኒስትር" ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ሚኒስትር ነው፤
9. "ባለሥልጣን" ማለት የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ነው፤
10. "የታክስ ባለሥልጣን" ማለት ባለሥልጣኑ ወይም በባለሥልጣኑ የሥልጣን ውክልና የተሰጠው የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር የግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ነው፤
11. "አቅራቢ" ማለት የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎችን ለታክስ ከፋዮች በሽያጭ የሚያቀርብ ሰው ነው፤
12. "ሰው" ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
13. "ፊሲካል ፕሪንተር" ማለት የፊሲካል ማስታወሻ ያለው ሆኖ በሥራ ላይ ያለውን የውስጥ መገናኛ በመጠቀም ብቻ በማናቸውም የአሠራር ፕሮግራም ሊያገለግል የሚችል ፕሪንተር ነው፤

ሙስናን የተመለከተ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ውሳኔ

E-mail Print PDF

የፌዴራል ሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ "የፀረ ሙስና ልዩ የስነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 239/1993." አንቀጽ 51/2/ "ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረን ስለሆነ ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረን መሆኑን በማረጋገጥ" ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ እንዲያስወስንልን በማለት የቀረበለትን አቤቱታ ተመልክቶ፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 84/2/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለውን የሕገ-መንግሥት ትርጉም ሃሣብ አቅርቧል፡፡

Read more...

የጋብቻ መፍረስ በንብረት ክፍፍል ላይ የሚያስከትለውን ውጤት የተመለከተ ውሳኔ

E-mail Print PDF

የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ የጋብቻ መፍረስን ተከትሎ ንብረት በምን ዓይነት መልኩ መጣራት እንዳበት የተለያዩ ድንጋጌዎችን ከአንቀጽ 85 እስከ 93 አስቀምጧል፡፡

Read more...

የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ሚና

E-mail Print PDF

(በዮሴፍ ሣህለሥላሴ)

ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የሚካሄደን አገራዊ ምርጫ ተከትሎ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች አገራችን ገብተዋል፡፡ እንዲሁም በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለመሆኑ የምርጫ ታዛቢ ማለት ምን ማለት ነው? ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በምን ሕግ ይመራሉ? ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የሚመሩበት የሥነ ምግባር ደንብ አለን? የሚሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

Read more...

Page 7 of 10