በዮሴፍ ሳህለሥላሴ
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት እና የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በጋራ፣ ሚያዝያ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል ባዘጋጁት የአንድ ቀን ዐውደ ጥናት ..የመረጃ ነፃነት እና የማወቅ መብት.. በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
በዮሴፍ ሳህለሥላሴ
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት እና የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በጋራ፣ ሚያዝያ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል ባዘጋጁት የአንድ ቀን ዐውደ ጥናት ..የመረጃ ነፃነት እና የማወቅ መብት.. በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
ሕጻናት የነገ አገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን የሁሉንም እንክብካቤ እና ድጋፍ ይሻሉ፡፡ የሕጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በዓለም አቀፍ እና በአህጉራዊ ደረጃ የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተዋል፡፡
(በሙላት ገ/ሕይወት ገዛኸኝ)
በአገራችን ውስጥ የሕክምና ውልና አሉታዊ ውጤቶቻቸውን በተመለከተ እንደ ሌሎቹ የውል ዓይነቶች በኅብረተሰባችን (በታካሚው፣ በሐኪሙና በተቋማቱ) ዘንድ እውቅና አግኝቶ ውሉ በተሟላ ሁኔታ አይሠራበትም፤ የውሉ ውጤት አሉታዊ ሆኖ ቢከሠትም፣ በተዋዋዮቹ ዘንድ ትኩረት አይሰጥበትም፤ በሕክምና አገልግሎት ሰጪው (ሐኪሙም ሆነ ተቋሙ) አገልግሎት የሚሰጠው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ልምድ መሠረት ባደረገ አኳኋን እንጂ በፍ/ብ/ሕጉ ስለ ሕክምና ሕግ፣ በሕክምና ሕግ ድርሳናትና በሙያ ሥነ ምግባሩ ደንብ ድንጋጌ መሠረት አይመራም ብሎ መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
በፍርድ ሒደት ውስጥ፣ በቀጠሮ ቀን የከሳሽ፣ ተከሳሽ ወይም ደግሞ ወኪሎቻቸው በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መገኘት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ በተከራካሪዎቹ መካከል አግባብ ያልሆነ መጉላላት እንዳይፈጠር ከፍተኛ እገዛ ያደረጋል፡፡ ከተከራካሪዎቹ አንዱ ያለ በቂ ምክንያት በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቢቀር በሌላኛው ወገን ላይ አላስፈላጊ እንግልት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
የተከሰሱ ሰዎችን በተመለከተ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት የተለያዩ መሠረታዊ መብቶች ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህ መብቶች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 20 በዝርዝር ይገኛሉ፡፡ ይኸውም፡-
- በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመዳኘት መብት፣
- ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሑፍ የማግኘት መብት፣
በጋዜጣው ሪፖርተር
ሕጻናት ልዩ ትኩረትና ከለላ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህም በመኾኑ የሕጻናት መብትን ለማስጠበቅ በዓለም አቀፍ፣ በአኅጉር እና በብሔራዊ ደረጃ የሚገኙ ተቋማት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተቋማቱ በየተዋረዳቸው ልዩ ልዩ ሕግጋትን አውጥተዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ በ1989 የወጣው ዓለም አቀፍ የሕጻናት መብቶች ኮንቬንሽን በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ በአኅጉር ደረጃ እ.ኤ.አ በ1990 የወጣው የአፍሪካ የሕጻናት መብቶች እና ደኅንነት ቻርተርም ተጠቃሽ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትም በአንቀጽ 36 እና በሌሎች ድንጋጌዎች ላይ የሕጻናትን መብቶች የተመለከቱ ድንጋጌዎችን አካትቷል፡፡
በሰለሞን ጎሹ
የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ጉዳይ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው እንዳልሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የሙያ ማኅበራት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ማኅበረሰቡን ሰብአዊ መብቶችን በአምሳለ ፍ/ቤት ውድድር የማስተማር ጥረትም ርእሰ ጉዳዩ ዘርፈ-ብዙ ተዋናዮች እንዳሉት ያሳያል፡፡
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 57 መሠረት አንድ ሰው በወንጀል ጥፋተኛ የሚባለው ድርጊቱን አስቦ ወይም በቸልተኝነት ያደረገ እንደሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የፈጸመው ድርጊት በሕግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ምንም ጥፋት ሳያደርግ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ ነገር የተፈጸመ ወይም የደረሰ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ሕግ ሊፈረድበት እንደማይገባ የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 57(2) ይደነግጋል፡፡
Page 8 of 10