መንግሥት ያዘጋጀውን የግል ድርጅቶች የጡረታ ፈንድ ረቂቅ አዋጅ ሰሞኑን ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ረቂቅ አዋጁ ከሰኔ 2002 ዓ.ም. በፊት ፕሮቪደንት ፈንድ ያቋቋሙ የግል ድርጅቶች ከፈለጉ ብቻ በጡረታ ፈንድ እንደሚታቀፉ ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ ከአሥር ዓመት ያነሰ ጊዜ ያገለገለ ሠራተኛ ድርጅቱን ሲለቅ ያዋጣው ገንዘብ አይመለስለትም ይላል፡፡ ከሃያ ዓመት በታች ያገለገለ ሠራተኛ እንዲሁ ሲለቅ ራሱ ያዋጣው ገንዘብ ብቻ እንደሚመለስለት ረቂቅ አዋጁ ያትታል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ የፈጠረውን ብዥታ የሚያሳየውን ዘገባ በቢዝነስ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡


