Skip to main content
x

ቅድሚያ ለአገር

ወቅታዊው የአገራችን ፖለቲካዊ ትኩሳት የወለዳቸው ችግሮች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የአገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ እዚህም እዚያም እሳት እያስነሳ ለበርካታ ዜጎች ሕይወት ሕልፈት፣ አካል ጉዳትና ንብረት መውደም ምክንያት ሆኗል፣ እየሆነም ነው፡፡ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችም ጋሬጣ እየሆነ ነው፡፡ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለም ጉዳቱ እየገዘፈ መምጣቱ አይቀርም፡፡

ጎርባጣው ባቡር

በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የአዲስ ጂቡቲ የምድር ባቡር መሳፈር ጀምረናል፡፡ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ድረስ በሚዘልቀው የባቡር መስመር ወደ 19 ከተሞች መጓዝ ቢቻልም፣ በአሁኑ ወቅት መንገደኞች የሚያስተናገዱት በአራት ከተሞች ብቻ ነው፡፡ አዲሱ የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር በቅርቡ ጉዞ የጀመረው 28 ተሳፋሪዎችን ይዞ ነበር፡፡ ከዚያን ወዲህ ያለው የተሳፋሪ ቁጥር ከዚህ በላይ እንደጨመረ ይታመናል፡፡ ብዙ የሚጠበቅበት የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት አጀማመሩ ስንጠብቀው የነበረውን ያህል አልሆነም፡፡ የባቡሩ ጉዞም ቢሆን ከትክክለኛው የፍጥነት ወሰን በግማሽ ቀንሶ የሚጓዝ ነው፡፡ በአራት ሰዓት ‹‹ድሬ›› የመድረስ ጉልበት ያለው ፈጣኑ ባቡራችን፣ አሁን ላይ ድሬ ለመድረስ ሰባት ሰዓታት ይወሰድበታል፡፡

ፍጥነት መንገዱና የፈጠነው ጥገና

ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ አዳማ ተጉዤ ነበር፡፡ ጉዞዬን ያደረኩት ከቃሊቲ መናኸሪያ በአዲሱ የፍጥነት መንገድ ነበር፡፡ ከከተማ ከወጣሁ ቆየት ብያለሁ መሰለኝ የፍጥነት መንገዱ ግራ ቀኝ የማውቀው አልመስልህ አለኝ፡፡ የመንገዱ ግራና ቀኝ በቀደመው ውበት ደረጃ ላይ አልነበረም፡፡ አንድ አዲስ የተመለከትኩት የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች በመንገዱ ግራና ቀኝ በተወሰነ ርቀት መቀመጣቸው ነበር፡፡ ይህ መዘጋጀቱ በጣም ጥሩ ዕርምጃ ነው፡፡

ውዥንብር የፈጠረው የቀረጥ ነፃ መመርያ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ታኅሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. አወጣ የተባለውና ለመንገደኞች የቀረጥ ነፃ መብት የሚሰጠው መመርያ ያልታሰበ ነበር ሊባል የሚችል ነው፡፡ ሹልክ ብሎ ዱብ ያለ የሚመስለው ይህ መመርያ፣ እውነት መሆኑን ለማመን ብዥታ ውስጥ  ገብተው ከነበሩት አንዱ ነኝ፡፡ ግን ትክክል መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ መመርያው እንዲተገበር ከተፈለገበት ምክንያቶች አንዱ ‹‹ላልረባ ቀረጥ›› የመንገደኞችን ሻንጣ እየበረበሩ ላለመጉላላት የሚለው ነጥብ ጎልቶ ወጥቷል፡፡ የረባና ያልረባ ቀረጥ ብሎ ነገር ያለ ባይመስለኝም ስለመመርያው መውጣት በተገቢው መንገድ ሳንሰማ ከመመርያው ጋር ተያይዞ ተፈጠረ ስለተባለው ቀውስ ጎልቶ ሰማን፡፡

ይበል የሚያሰኘው የአየር መንገዱ ዘመናይነት

እንደ ብሔራዊ ኩራት ከምንጠቅሳቸው አገር በቀል ኩባንያዎች ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀድመን እናነሳለን፡፡ ከ75 ዓመታት በላይ በበጎ አገልግሎቱ ስሙ የሚነሳው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከአገር ውስጥ አልፎ በአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪው የአፍሪካ ግንባር ቀደም ለመሆን በቅቷል፡፡ በየጊዜው አዳዲስ አሠራሮችን እያስተዋወቀ በተወዳዳሪነት የዘለቀው አየር መንገዱ፣ በኢንዱስትሪው ትልቃ ስም በማትረፍ በዓለም የሚጠቀስ ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡ በየጊዜው የሚያገኛቸው ሽልማቶችም ለዚህ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አጥር አልባው ባቡር

ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ የወጣበት የአዲስ አበባ ጂቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በይፋ ጀምሯል፡፡ በዓመት ከሁለት ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የማጓጓዝ ዕቅድ የተያዘለት ይህ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ዋነኛ ተግባሩ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ምርቶች ማጓጓዝ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የዋጋ ቅናሽ የሚናፍቀው ሸማች

በዓላት በተቃረቡ ቁጥር ሰውን ሁሉ ራስ ምታት ከሚያሲዙ ጉዳዮች አንዱ የዋጋና የገበያ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከበዓላት አከባበር ልማድ አኳያ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ እንደ በግ፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ እንቁላል ወዘተ. ምርቶች ዋጋቸው ምን ያህል ጨምሮ ይሆን? የሚለው ያሳስባል፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በዓሉን ለማክበር ተለቅቶና ተበድሮ የቋጠራትን ጥሪት በመያዝ ወደ ገበያ ያቀናል፡፡

አገር ታሟል ሐኪም ይሻል

 የአገራችን የፖለቲካ ትኩሳት ብዙ እየተባለለት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ አኳኋን ለተፈጠረው ችግር መንስዔው ምንም ይሁን፣ የሰው ሕይወት እየጠፋበት መሆኑ ከምንም በላይ ያሳዝናል፡፡ እጅግ ያማል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ በግጭቱም የጠፋው የሰው ሕይወት፣ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በብርቱ እንዲታይ የሚያስገድድ ሲሆን፣ ዘግናኙ ግጭት ለምንና እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ማወቅን፣ ዳግም እንዳይከሰት የሚረዳ ዘላቂ መፍትሔንም ይጠይቃል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮቹን ምን አፈዘዛቸው?

የአገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳደግ ብሎም በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፉ ተስፋ ከተጣለባቸው የመንግሥት ውጥኖች ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ይጠቀሳል፡፡ እነዚህ ፓርኮች በልዩ ትኩረትና ክትትል እንደሚገነቡም ሲገለጽ ቆይቷል፡፡