Skip to main content
x

‹‹አርዘ ሊባኖስ››

አርዝን መዝገበ ቃላት ሐዲስ ዘኪወክ ታላቅ ዛፍ ወፍራም ደንዳና ረዥም ገናና እንደ ጥድና እንደ ዝግባ ያለ ሲል ይፈታዋል፡፡ እስከ 20 ሜትር የሚረዝመው ዝግባ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በደጋማ አካባቢ ይበቅላል፤ ብዙ ቅጠልና ዐጽቅ አለው፡፡ በሊባኖስ ምድር የሚበቅለው ረዥሙ ዛፍ ‹‹አርዘ ሊባኖስ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡

ሰስ

ሰስ በተራራማ አካባቢ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ ከአጥቢ እንስሳ የሚመደቡ ሲሆን፣ ምግባቸውም አበባ፣ ሰፋፊ ቀጠል፣ ፍራፍሬና እፀ ተክል ናቸው፡፡ ሰሶች ሳር አይበሉም፡፡ አንድ ሴት ሰስ ከ11 እስከ 16 ኪሎ ግራም ስትመዝን፣ ወንዶቹ ከዘጠኝ እስከ 12 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ የሁለቱም ቁመት እስከ 82 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡

ልዩዎቹ የዘንባባ ዛፎች

ከብዙ ዓመታት በፊት በውኃ እየተገፋ የመጣ አንድ በጣም ትልቅ ዘር በሞልዳይቪስ እና በኢንዶኔዢያ ደሴቶች ዳርቻ ላይ ሲያርፍ የብዙ ሰዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። የዚህን ዘር መነሻ በሚመለከት የተለያዩ አፈ ታሪኮች ይነገሩ ጀመር። አንዳንዶች በባሕር ውስጥ የሚበቅል ዛፍ ዘር እንደሆነ ስለተሰማቸው ኮኮ ደ ሜር ወይም የባሕር ኮኮናት ብለው ሰየሙት።

ድምፅ አልባ አጥፊው

ምስጦች ድምፅ አልባ አጥፊዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ ስም የተሰጣቸው ዛፎችን፣ የዛፍ ስሮችንና ተክሎችን እንዲሁም የእንጨት ውጤቶችን ከላይ ሳይሆን ከሥር ገብተው ውስጡን ቦጥቡጠው ስለሚበሉና ቅርፊት ብቻ ስለሚያስቀሩ ነው፡፡ ምስጦች ለ24 ሰዓት ሳያቋርጡ የሚመገቡ ሲሆን፣ የተመቻቸ ስፍራ ካገኙ እዚያው መጠለያቸውን ሠርተው ይሰፍራሉ፡፡

ባለ አስገራሚ ድምፁ ወፍ

​​​​​​​‹‹ሉን›› በመባል የሚጠራው ወፍ አስገራሚ ድምፅ አለው ይሉታል፡፡ ይህ ወፍ የሚገኘው በካናዳ፣ በአውሮፓና በሰሜናዊ ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ ሐይቆችና ወንዞች አቅራቢያ ሲሆን፣ ኮሽታ በማይሰማባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ድምፁ ከርቀት ያስተጋባል።

ሾለቅ- አፈ ሹል አሞራ

‹‹አዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› ሾለቅን አፈ ሹል አሞራ ይለዋል፡፡ እሱ ሲጮህ ዝናም ይመጣል ይባላል፡፡ ዶ/ር ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› ላይ እንደገለጹት፣ ጠቆር ያለ ግራጫ መልክ አለው፡፡

ግስላ

ግስላ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና እስያ የሚገኝ የነብር ዓይነት ነው፡፡ አጥቢና ሥጋ በል አውሬ ከመሆኑም እጅግ ቁጡ አውሬና እልከኛም ነው፡፡ የአንድ ጎልማሳ ግስላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪሎ ግራም ሲደርስ፣ ርዝመቱ ከ90 ሴንቲ ሜትር እስከ 1.60 ሜትር ይሆናል፡፡

የድመት ጢም

ድመቶች አብዛኛውን ጊዜ በጨለማ ንቁ ናቸው። ከጨለመ በኋላ በአቅራቢያቸው ያሉ ነገሮችን ለይተው ለማወቅና አድነው የሚበሉትን እንስሳ ለመያዝ የሚረዷቸው ጢሞቻቸው እንደሆኑ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል የሚለው ጄደብሊው ዶትኦርግ ነው።

‹‹አዳኙ ወፍ››

ጭልፊቶች በኢትዮጵያ አብዛኛው አካባቢ ይታያሉ፡፡ እርድ በሚፈፀምባቸው ቦታዎች፣ ዓሣ በሚሠገርባቸው ሐይቆችና ሜዳማ ቦታዎች አይጠፉም፡፡ በየጎዳናው የተጣሉ ጥንቦችን ለማንሳትም የሚቀድማቸው የለም፡፡ ዶሮና ሥጋ ዓሣንም በመንጠቅ የምትታወቀው ጭልፊት  በብሂል ውስጥ ትታወቃለች፡፡ ‹‹አጅሬ ጭልፊት ነውኮ›› እንዲል ምሰላው፡፡ ክረምት በሚበረታበት በሐምሌና በነሐሴ ወራት ከዕይታ ትርቃለች፡፡

ድብ

ድብ ከአጥቢ እንስሳት ይመደባል፡፡ ድቦች በዋነኛነት የሚመገቡት ፍራፍሬና አትክልቶችን ነው፡፡ አንዳንዴ በጎችን እንደሚበሉም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ መኖሪያቸው በዋሻዎች ወይም በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ነው፡፡ በሰዓት እስከ 40 ኪሎ ሜትር ሲጓዙ፣ ክብደታቸው ደግሞ ከ70 ኪሎ ግራም እስከ 120 ኪሎ ግራም ይደርሳል፡፡