Skip to main content
x

የወልዲያ ስታዲየም ለአንድ ዓመት ውድድር እንዳያስተናግድ መታገዱን ክለቡ ተቃወመ

  • አሠልጣኙና ተጫዋቾች ዕግድና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የተመልካቾች አምባጓሮ በአብዛኞቹ ክልሎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየታየ ነው፡፡ በክልሎች በሚካሄዱ ውድድሮች ወቅት የተጫዋቾችንና የደጋፊዎችን ስም እየጠሩ መሳደብና ማንቋሸሽ፣ ብሽሽቁን ወደ ብሔር በመውሰድ ግጭት ማስነሳትና ድንጋይ መወራወር፣ ተጫዋቾችንና አሠልጣኞች ማስፈራራት በስታዲየሞች አካባቢ እየተለመደ መጥቷል፡፡ የአካል ላይ ጉዳት ማድረስና የንግድ ቤቶችን ማጥቃት እየተለመደ በመምጣቱ፣ ረብሻውን ለማረጋጋት አስለቃሽ ጋዝ እስከ መጠቀም ደረጃ ተደርሷል፡፡

የወላይታ ዲቻ የኮንፌዴሬሽን ተሳትፎ ዛሬ ይለይለታል

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አማካይነት በየዓመቱ በሚዘጋጀውና ዘንድሮም እየተካሔደ በሚገኝ የኮንፌደሬሽን ዋንጫ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ወላይታ ዲቻ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐዋሳ ስታዲየም በሚያደርገው ጨዋታ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ ዕድሉ ይለይለታል፡፡

ከጨዋነት የራቀው ስፖርታዊ ጨዋነት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሜዳዎች በስፖርታዊ ጥበብና ክህሎት፣ በታክቲክና ቴክኒክ ብቃታቸው የሚያስደምሙ፣ የእግር ኳስ ጠቢባን የሚታዩባቸው፣ ሕዝቡ በኳስ ፍቅር የሚጎርፍባቸው ከመሆን ይልቅ፣ የደጋፊዎች እርግጫና ጡጫ አስቀያሚ ቃላት መሰናዘሪያ አለፍ ሲልም ብሔር ቀመስ መሻኮቻዎች ከሆኑ ውለው አድረዋል፡፡

ዋሊያዎቹ በፊፋ ደረጃ ወደ 145ኛ ወረዱ

አሠልጣኝ አልባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በፊፋ ወርኃዊ ደረጃ ስምንት ደረጃዎችን በመጣል ከ137ኛ ወደ 145ኛ ዝቅ ማለቱ ባለፈው ሐሙስ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ግጥሚያ የወዳጅነትን ጨምሮ ያላደረጉት ዋሊያዎቹ ለደረጃቸው ማሽቆልቆል በምክንያትነት ይነሳል፡፡

ትንሣኤን በሩጫ

በርካታ ዓለም አቀፍ የጎዳና የሩጫ ውድድሮች በበዓለ ትንሣኤው ዋዜማና በዕለቱ ተከናውነዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶችም ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ከተከናወኑት የማራቶንና ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድሮች በተለያ የአውሮፓ ከተሞች የተደረጉት ይጠቀሳሉ፡፡

ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ቡሩንዲ ያቀናል

በአፍሪካ ደካማ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ከሚስተዋልባቸው ዞኖች የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) ይጠቀሳል፡፡ ዞኑ ከእግር ኳሳዊ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ከፋይናንስ እስከ ወጥ የሆነ ዓመታዊ መርሐ ግብር አወጣጥ ድረስ ችግር ያለበት በመሆኑ ጭምር ይታወቃል፡፡ በዚሁ ችግር ምክንያት የዞኑ አገሮች ብሔራዊ ቡድኖች ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረም ይገኛል፡፡

ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ለአራተኛ ጊዜ ተሳትፎ የሚያበቃቸውን ግስጋሴ በድል ጀመሩ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሚቀጥለው ዓመት በጋና አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሮችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በግብፅ ካይሮ የሊቢያ አቻውን የገጠመው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) 8 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ከጉባዔው የሚጠበቀው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀጣይ አመራርን ለመምረጥ እየተደረገ የነበረው የተንዛዛ አካሄድ ምንም እንኳ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) መፍትሔ ያለውን የውሳኔ ሐሳብ ቢያሳልፍም፣ አሁንም መቋጫውን አላገኘም፡፡ በተለያዩ ግለሰባዊ ፍላጎቶች ፍትጊያዎችን ያስተናገደው ይህ ምርጫ ከበርካታ ባለሙያዎችና አስተያየት ሰጪዎች የሰላ ትችት ሲያስተናግድ ከርሟል፡፡

ፊፋ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲመረጥ አዘዘ

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አካል ፊፋ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫን የሚያስፈጽም አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንደገና እንዲያዋቅር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ፊፋ በፌዴሬሽኑ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ላይ የነበረውን ውዝግብ ለመፍታት ውሳኔ እንደሚያተላለፍ ከሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ፊፋ በደብዳቤው አዲሱ የአስመራጭ ኮሚቴ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ልየታ እንደገና እንዲሠራና ወደ ምርጫ ሒደት እንዲገባም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡