ሰስ በተራራማ አካባቢ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ ከአጥቢ እንስሳ የሚመደቡ ሲሆን፣ ምግባቸውም አበባ፣ ሰፋፊ ቀጠል፣ ፍራፍሬና እፀ ተክል ናቸው፡፡ ሰሶች ሳር አይበሉም፡፡

 

የአዞ መንጋጋ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ከሚኖሩ አራዊት ሁሉ ይበልጥ ከፍተኛ የመቀርጠፍ ኃይል አለው። ለምሳሌ ያህል፣ አውስትራሊያ አቅራቢያ በጨዋማ ውኃ ውስጥ የሚኖረው አዞ የመንከስ ኃይሉ ከአንበሳ ወይም ከነብር ጋር ሲወዳደር ሦስት እጥፍ ያህል ከፍ ያለ ነው። 

ወርቅ፣  አልማዝ፣ ብር፣ መዳብ፣ ነሐስ፣ የደንጊያ ከሰል፣ ብረት፣ ባዚቃ፣ ታኒካ፣ ቆርቆሮ፣ እርሳስ፣ ደንጊያ፣ ዕብነ በረድ፣ ፕላቲን፣ ቤንዝን፣ ጋዝ፣ በጠቅላላው ዘይታዘይት፣ እንጨት፣ ሣር፣ እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፍ፣ አንሥርት፤ ይህን የመሰለው ሁሉ የምድር ሀብት ነው፡፡  

Pages