የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ጥሰዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የቆጠረባቸውን ምስክሮች የማወቅ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለባቸው ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ፣ ‹‹የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል›› በማለት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላከ ቢሆንም ውድቅ ተደረገ፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በታሰሩት፣ በሃዚ አይአይ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤትና በባለሥልጣኑ ዕቃ አቅርቦት ቡድን መሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡  

ከሰሞነኛዎቹ አጀንዳዎች መካከል አንዱ የፀረ ሙስናው ዘመቻ ነው፡፡ በዘመቻውም ከሃምሳ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ባለሥልጣናት፣ ባለሀብትና ደላላዎች ታስረዋል፡፡ ከ200 በላይ የሚሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሀብታቸው በፍርድ ቤት ታግዷል፡፡

መንግሥት ብዙ ነገሮችን በዘመቻ መልክ ማከናወን ይመርጣል፡፡ ልማት በዘመቻ፣ የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል በዘመቻ፣ መልካም አስተዳደር ማስፈን በዘመቻ፣ አዳዲስ አሠራሮችን መተግበር በዘመቻ፣ ሙሰኞችን መክሰስ በዘመቻ አያሌ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ዘመቻ ማድረግ ይቀናዋል፡፡

ቁርጥ ግብር፣ ለማስገበር አስቸጋሪ የሆኑ ገቢ ላይ ይተገበራል፡፡ በቁርጥ የሚጣል ግብር መጠን በተጠና ግምት ይሰላል፡፡ ግብር ተማኙና ሰብሳቢው ባለሥልጣን ትክክል ነው ብሎ የሚያስበውን ግብር በግምትም ቢሆን ለማወቅ የተለያዩ መረጃዎች ላይ ይመሠረታል፡፡ 

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የሚያስችለውን አዋጅ አጽድቆ  ረቂቁን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ 

Pages