የፌዴራል መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር በውክልና የወሰደው የገቢዎች ባለሥልጣን፣ በድጋሚ ወደ ከተማው አስተዳደር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣንን በቢሮ ደረጃ ሊያዋቅር መሆኑ ታውቋል፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ›› በሚባል ስያሜ የሚቋቋመው ተቋም በካቢኔ አባል የሚመራ ይሆናል ተብሏል፡፡

የእስራኤልና የእንግሊዝ ኩባንያዎች በደቡብ ምሥራቅ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች 600 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከጂኦተርማል ዕምቅ  ኃይል በ2.9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ኢንቨስትመንት ለማልማት፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መደራደር ጀመሩ፡፡      

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የፌዴራል ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች በቅርቡ ያሠራጨውን የበጀት ወጪ ቅነሳ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው፣ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንዲያቀርቡ አዘዘ፡፡ በመመርያው መሠረት በርካታ አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዲቀንሱ ጠበቅ ያሉ ክልከላዎች ተደርገዋል፡፡          

በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው 46 የቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎችና ማበጠሪያዎች በ144.95 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት ስለደረሰባቸው ከመንግሥት የካሳ ክፍያ ማግኘት መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡  

ኢትዮጵያ ከወርቅ የወጪ ንግድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያገኘችው በ2004 ዓ.ም.  እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱ ወደ ውጭ ከተላከው የወርቅ መጠን የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ620 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነበር፡፡       

Pages