አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
  • 51 በመቶ ድርሻውን በ48 ሚሊዮን ብር ሸጧል

በኢትዮጵያ የመነፅር ውጤቶች አምራችነቱና አከፋፋይነት የሚታወቀው ሳን ኦፕቲካል ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለግዙፉ ዓለም አቀፍ የመነፅር አምራች ኩባንያ 51 በመቶ ድርሻውን በመሸጥ ምርቱን በአሥር እጅ ለማሳደግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

የግሉ ዘርፍ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በጋራና በተቀናጀ መንገድ ለመወጣት በማሰብ ‹‹የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ማኅበራዊ ኃላፊነት ፈንድ›› በሚል ስያሜ ለሚመሠረተው ተቋም የመመሥረቻ ቻርተር ይፋ ተደረገ፡፡ ፈንዱን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማቋቋም ስምምነት ተደርጓል፡፡

መንግሥት ለገቢ ንግድ በየዓመቱ የሚፈቅደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ የአዲስ አበባ አስመጪዎች እጅ ውስጥ ለማስለቀቅ፣ 215 የክልል አስመጪዎችን መመልመሉ ተሰማ፡፡

  • ወንጀሉን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቁሟል

ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች በኢትዮ ቴሌኮም ሳተላይት ኔትወርክ በኩል ማለፍ ሲገባቸው፣ ሕገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎች ያስገቡ ግለሰቦች ዓለም አቀፍ ጥሪዎቹን በመጥለፍ በራሳቸው መስመሮች ለደንበኞች እያቀረቡ እንደሆነ ታወቀ፡፡

በነሐሴ 2009 ዓ.ም. በአንድ ወር ውስጥ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ለዓለም ገበያ የሚቀርብ የኢትዮጵያ ቡና ግብይት መጠን በ66 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተገለጸ፡፡ ምርት ገበያው በአንድ ወር 1.7 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶች እንዲያገበያይ በቡና እና በምርት ገበያ ላይ የተደረገው ሪፎርም አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ በነበረው ሕዝባዊ አመፅ ሳቢያ ሁለት ጊዜ ንብረቶቹ የተጎዱበት ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የ2010 ዓ.ም. ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የዋዜማ ድግስ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ዕርቅ አወረደ፡፡

Pages