አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

በዳዊት እንደሻው

ሦስት መቶ ሃምሳ ያህል የሰፋፊ እርሻ ልማት ባለሀብቶችን እንወክላለን ያሉ አራት ማኅበራት፣ እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ምክንያት ዘርፉ አደጋ ላይ እየወደቀ ስለሆነ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ጠየቁ፡፡

በዳዊት እንደሻው

ከዚህ ቀደም በፓስታ አስመጪና ላኪነት ብቻ ተሰማርቶ የነበረው አልቪማ አስመጭና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በአገር ውስጥ ፓስታ ለማምረት የሚያስችለውን ፋብሪካ በአዳማ ከተማ ገነባ፡፡

  • ከታክስ ግርግር እስከ መንግሥት ጣልቃገብነት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች አቶ ኃይለ ማርያም የሰጧቸው ምላሾች

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ከተቋቋመ ሰባት ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል በተደረሰ ስምምነት መሠረት፣ በሚኒስትሮች የተመሩ 15 ያህል የምክክር መድረኮች በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

የኅብረቱ ልዑክ ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም ብሏል

የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን ወደ አውሮፓ የሚልኩ ነጋዴዎች፣ በመንግሥት አሠራር ሳቢያ ምርታቸውን መላክ እንዳልቻሉ በመጥቀስ በቀረበው ዘገባ ላይ ምላሽ የሰጠው የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተገቢውን እየሠራ እንደሚገኝ በማስታወቅ ይልቁንም በአፍላቶክሲን ጉዳይ መጠየቅ የሚገባው የአውሮፓ ኅበረት ነው በማለት ወቀሳውን አሰምቷል፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ከሌላቸው አገሮች መካከል አንዷ ነች፡፡ አገሪቱ ያለ ባህር መኖር ከጀመረች ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ተቆጥሯል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ስትሄድ የአሰብንና የምፅዋን ወደቦች ይዛ በመሄዷ ወደብ አልባ አገር ሆናለች፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር በውክልና የወሰደው የገቢዎች ባለሥልጣን፣ በድጋሚ ወደ ከተማው አስተዳደር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣንን በቢሮ ደረጃ ሊያዋቅር መሆኑ ታውቋል፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ›› በሚባል ስያሜ የሚቋቋመው ተቋም በካቢኔ አባል የሚመራ ይሆናል ተብሏል፡፡

የእስራኤልና የእንግሊዝ ኩባንያዎች በደቡብ ምሥራቅ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች 600 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከጂኦተርማል ዕምቅ  ኃይል በ2.9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ኢንቨስትመንት ለማልማት፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መደራደር ጀመሩ፡፡      

Pages