እነሆ መንገድ ከኮተቤ ወደ መገናኛ። ጅምር መንገድ ማለቂያ የሌለው ዛሬም እያነሆለለ እያዳፋ ያስጉዘናል። አጥፊና አልሚ ያለ ቀጠሮ ይገናኛል። ሰው ያለ ቢጤው ሊውል ባላሰበው ሊሠለጥን ልራመድ ብሎ መንገድ ያምናል።

እነሆ መንገድ፡፡ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ጎዳናው በባለርስቶቹ ዘመን ብዙ ለምዶ ኖሮ እንደተወረሰ ሰፊ እልፍኝ፣ ‘በስመአብ በስመአብ አልኩኝ ብቻዬን ቀርቼ’ ይባልበት ይዟል። 

እነሆ መንገድ! ከሽሮ ሜዳ - ሜክሲኮ ወደ ጦር ኃይሎች ልንጓዝ ነው። “እዚህ ጋ ጠጋ! ጠጋ! ‘ማዘር’ እዚህ ተጠጉላቸው፤” ተለምዷዊ ቀጭን ትዕዛዝ ናት።

እንሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ኮተቤ ልንጓዝ ነው። እልፍ አዕላፍ ታረኮች በህላዌ መንደር ዛሬም እየተኖሩ ይተረካሉ።

Pages