አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ግንኙነት በማንኛውም መሥፈርት እጅግ የተወሳሰበ ነው፡፡ ለዘመናት በእርስ በርስ ጦርነት፣ ግጭትና ፖለቲካ ፍትጊያ ውስጥ  አልፈዋል፡፡ አልፎ አልፎም ሁለት ሆነው በማበር አንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያሴሩበት አጋጣሚም ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

የሙስና ወንጀል ተግባራት ጋር ተያይዞ መንግሥት እየወሰደ ያለው ዕርምጃ የዘገየ አለመሆኑንና የባለሥልጣን ከለላ ያላቸው አይነኩም የሚለውን አመለካከት እንደማይቀበሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ መንግሥት ከአሁን በኋላ በአገሪቱ አለመረጋጋትን የሚያስከትሉ ክስተቶችን እንደማይታገስም አስጠንቅቀዋል፡፡

የተከሰሱበት የሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ ወደ ወንጀል ሕግ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው አቶ በቀለ ገርባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን በመከላከያ ምስክርነት በመቁጠራቸው ባለሥልጣናቱ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የአማራና የቅማንት ሕዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች በማኀበረሰቦቹ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ለማቋቋም ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ በተወሰነው መሠረት፣ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ወሰነ።

  • በሁለት ወራት ከ1.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የዕርዳታ እህል ተከፋፍሏል

በዚህ ዓመት በተካሄደው የበልግ ወቅት ጥናት መሠረት፣ በአሁኑ ወቅት ከ8.5 ሚሊዮን በላይ የድርቅ ተጎጂዎች ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 2010 ዓ.ም. የሚያቆይ የምግብና ሌሎች የዕለት ደራሽ ዕርዳታዎችን ለማቅረብ 487.7 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የፌዴራል ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች በቅርቡ ያሠራጨውን የበጀት ወጪ ቅነሳ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው፣ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንዲያቀርቡ አዘዘ፡፡ በመመርያው መሠረት በርካታ አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዲቀንሱ ጠበቅ ያሉ ክልከላዎች ተደርገዋል፡፡          

Pages