Skip to main content
x

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

የቻይናው ሴራሚክ አምራች በአምፑል ምርቶችም ለመሠማራት መዘጋጀቱን አስታወቀ

በቻይናው ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ በ26 ሔክታር (260 ሺሕ ካሬ ሜትር) መሬት ላይ የተንጣለለው የሴራሚክ ውጤቶች ማምረቻ፣ በቻይናው ዲ ዩዋን ሴራሚክስ ኩባንያ የሚመራ ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው ምርት በጀመረ በአንድ ዓመት ውስጥ ገበያው ውስጥ ተሰቅሎ የቆየውን ዋጋ ማረጋጋት እንደቻለም ይነገርለታል።

ቻይና ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ዕቅዶች ድጋፌ ይቀጥላል አለች

የቻይና ሕዝባዊ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና የኮንግረሱ አፈ ጉባዔ ሊ ዣንሹ፣ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ላለው ዲፕሎማሲዊ ግንኙነትና ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የልማት ዕቅዶች ቻይና የምታደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ፡፡

ከመቶ ያላነሱ የአውሮፓና የቻይና ኩባንያዎችን በአንድ ቦታ ያገናኙ ሁለት የንግድ ዓውደ ርዕዮች

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ሁለት የንግድ ዓውደ ርዕዮች በተመሳሳይ ቀናት ተካሂደዋል፡፡ ከመቶ ያላነሱ የውጭ ኩባንያዎችም ተሳትፈዋል፡፡ ከሐሙስ ሚያዝያ 25 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. የተካሄዱት ሁለቱ የንግድ ዓውደ ርዕዮች የየራሳቸው ይዘትና ኩነቶችን የያዙ ቢሆኑም፣ በአንድ ቦታና ተመሳሳይ ቀናት ውስጥ እንዲካሄዱ ተደርገዋል፡፡

የቻይናው ሹራብ አምራች አሥር ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ የሚጠበቀውን ፋብሪካ ሥራ አስጀመረ

በቻይናው ሻንቴክስ ሆልዲንግ ግሩፕ ሥር ከሚተዳደሩ በርካታ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው ሎንቶ ጋርመት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ በዓመት አሥር ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል የሚጠበቀውን ፋብሪካ በዱከም መሥርቷል፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የፋብሪካው የምርቃት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ረዳት ኃላፊ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ይገባሉ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተቀዳሚ ምክትል ኃላፊ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለመምከር፣ ሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት የተጀመረው ፕሮጀክት ቅሬታ እየቀረበበት ነው

በአዲስ አበባ ከተማ እያጋጠመ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በዘላቂነት ለመፍታት፣ በ162 ሚሊዮን ዶላር እየተካሄደ የሚገኘው ግዙፍ ፕሮጀክት ጫና በዝቶበታል፡፡ ፕሮጀክቱ የኤሌክትሪክ ኃይል እየተቋረጠ የሚከናወን በመሆኑ ከኅብረተሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረበበት ነው፡፡

የአሜሪካ የብድር ዕዳ ማስጠንቀቂያና ችላ ያለችው ድጋፍ 

በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከቻይና የሚገኘው ብድር የሚያስከትለውን የብድር ዕዳ መነሻ በማድረግ ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር ለአፍሪካ አገሮች አስተላልፈው ወደ ኬንያ አቅንተዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርና አሳሳቢ ችግሮች ላይ ያተኩራል

ከረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን፣ በጉብኝታቸው ወቅት ትኩረት ከሚያደርጉባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ተተኪውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሰየም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሽግግር ሒደቱን የተመለከተውና ከወቅቱ አሳሳቢ ችግሮች ከዋና ዋና ነጥቦች መሆናቸው ተገለጸ፡፡