Skip to main content
x

ጉራማይሌው የክለቦች አደረጃጀትና እየጋለ የመጣው የሙያተኞችና የደጋፊዎች ጥያቄ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተደጋግሞ ሰሞነኛ ወሬ ሆኖ ሲደመጥ የሚስተዋለው ከስፖርቱ አዎንታዊ ጎን ይልቅ አሉታዊ ጎን ነው፡፡ ከአሉታዊ ጎኖቹ መካከል ክለቦች የመኖርና ያለመኖር ሕልውናና በእግር ኳሱ ምክንያት ክቡር የሆነው የሰው ሕይወትና ንብረት ውድመት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ለእግር ኳሱ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን፣ ለኅብረተሰቡ በሚሰጡት ማኅበራዊ ግልጋሎት ጭምር ትልቅ ስምና ዝና ያላቸው ‹‹ውጤት›› ወይም ደግሞ ‹‹ተገቢ ክብር አልተሰጠንም›› በሚል እንዲፈርሱ የተደረጉና ለመፍረስ ከጫፍ የደረሱ ክለቦች ቁጥር እየበረከተ መምጣቱን የሚናገሩ አሉ፡፡ ከነዚህ አስተያየት ሰጪዎች መካከል የኢትዮጵያ ባንኮች ስፖርት ማኅበር ደጋፊዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

የታላቁ ሩጫ የክልል ጉዞ ከሐዋሳ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓልን በማስመልከት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በክልሎች ሊያከናውን ካቀዳቸው የጎዳና ውድድሮች ቀዳሚውን በሐዋሳ አከናወነ፡፡ እሑድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ውድድሩን የጀመረው ታላቁ ሩጫ የተለያዩ የክለብ አትሌቶች የከተማዋ ነዋሪና የንግድ ባንኩ ደንበኞችን አሳትፏል፡፡

የሕንፃ ግንባታ ድንጋጌዎችን የጣሱ ኩባንያዎች በሕግ ሊጠየቁ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንፃ ግንባታ አዋጅ የደነገገውን በመተላለፍ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ 23 ኩባንያዎች ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፣ ባለማረማቸው ምክንያት በሕግ ሊጠየቁ ነው፡፡ ወደ ሕግ ከተወሰዱት መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይገኝበታል፡፡

ካሩቱሪ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ይፋ አደረገ

የኩባንያው ባለቤት ‹‹ተስፋ ቆርጫለሁ ተሸንፌያለሁ›› አሉ ለሰባት ዓመታት ያህል በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ከመቶ ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት የእርሻ ቦታ በመያዝ የሜካናይዝድ ግብርናን ለማካሄድ ሲሞክር የቆየው የህንዱ ካሩቱሪ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱንና ኢንቨስትመንቱን ማቋረጡን ለሪፖርተር ይፋ አደረገ፡፡