Skip to main content
x

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ የሚታየው ግጭት አሳስቦኛል አለ

የአሜሪካ ኤምባሲ በጨለንቆና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተነሱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት በመጥፋቱና የአካል ጉዳት በመድረሱ እጅግ እንዳሳሰበውና እንዳዘነ ገለጸ፡፡ ኤምባሲው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

ምሁራን አገራዊ ግዴታቸውን እንዳልተወጡ የተብራራበት ኮንፈረንስ

ሐረግ ጥበቡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ እንደሆነች ትናገራለች፡፡ ከምዕራብ ጎጃም ዞን እንደመጣች ታስረዳለች፡፡ ቤተሰቦቿ አርሶ አደሮች እንደሆኑና ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ እንደሚገፉ ትገልጻለች፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሰቲዎች እየተሰሙ ያሉ ዜናዎች እያሳሰባት መሆኑን ትናገራለች፡፡ ትምህርቷን አጠናቅቃ አስተምረው ለዚህ ያደረሷትን ቤተሰቦቿን ለመርዳትና ለማስደሰት ህልም ቢኖራትም፣ በአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚታዩ ነውጠኛ ድርጊት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም እንዳይከሰት ትሠጋለች፡፡

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተዛምቷል

የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ20 በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል በትግራይ ክልል በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መዛመቱ ተገለጸ፡፡ በሕይወትና በአካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ተማሪ ሲሞት፣ ከ20 በላይ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ተማሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አውስትራሊያ ከሄዱ በኋላ ሪፖርት አለማድረጋቸው ጥያቄ አስነሳ

ከኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ጋር ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው የነበሩት የኢትዮጵያ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አውስትራሊያ ከሄዱ በኋላ ሪፖርት ሳያደርጉ አንድ ወር ማስቆጠራቸው ጥያቄ አስነሳ፡፡ በዚህም ምክንያት ቼክ ላይ የሚፈርም በመጥፋቱ ችግር መፈጠሩን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞችን እመነጥራለሁ አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጭበርብረው የተቀጠሩ ሠራተኞችን ለመመንጠር አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሁሉም መሥሪያ ቤቶች ይህንን የሚሠራ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን፣ በማዕከል ደረጃ ፖሊስና ፍትሕ ቢሮ ያሉበት ግብረ ኃይል አቋቁሟል፡፡ ቢሮው ሒደቱ የሚመራበትን መመርያ በማዘጋጀት በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ መዋቅሮች ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ቆይቷል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሠራው የእንቦጭ መንቀያ ማሽን አጥጋቢ ሙከራ ማድረጉ ተገለጸ

በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመንቀል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካይነት የተሠራው ማሽን አጥጋቢ ሙከራ ማድረጉ ታወቀ፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ማሽኑን ለመሥራት ሙከራ ሲደረግ ቆይቶ፣ ሰሞኑን በተደረገው ጥረት ማሽኑ አረሙን መንቀል እንደቻለ ታውቋል፡፡

በአማራ ክልል የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ቱለፋ ከተማ የተቋቋመው የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡ በቻይና ባለሀብቶች የተቋቋመውና ሒዩማን ዌል ፋርማሲዩቲካል በተሰኘው ድርጅት አማካይነት በአማራ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው ‹‹ሒዩማን ዌል›› የተሰኘውና የመጀመርያ የሆነው የመድኃኒት ፋብሪካ፣ እሑድ ኅዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይኼነው ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹መንግሥት እንኳን የሰው ሕይወት ይቅርና የውሻ ደም መፍሰስ የለበትም ብሎ ነው እየሠራ ያለው›› ነገሪ  ሌንጮ (ዶ/ር)፣  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ስለህዳሴ ግድቡና አገሪቱ ስላለችበት የፀጥታ ሁኔታ የመግለጫቸው የትኩረት ነጥቦች ነበሩ፡፡

በኢትዮጵያ ግብርና ቀዳሚ የሆነው የጤፍ እርሻ በሜካናይዜሽን ሊደገፍ ነው

የግብርና ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ይጠበቃል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ለአርሶ አደሩ አድካሚ ሆኖ የቆየውን የጤፍ እርሻ ሥራ በሜካናይዜሽን እንዲታገዝ ለማድረግ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ጤፍ የሚያጭዱና የሚወቁ ማሽኖችን ከቻይና አስገባ፡፡

በወ/ሮ አዜብ መስፍን ዕግድ ላይ የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚወስን  ተጠቆመ

ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና አቶ ዓለም ገብረዋህድ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በማዕከላዊ ኮሚቴ እያካሄደ በሚገኘው ጥልቅ ግምገማ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ለጊዜው ታግደው እንዲቆዩ በተደረጉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጉዳይ ላይ፣ የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ምንጮች ገለጹ፡፡