Skip to main content
x

በካፋ ዞን ጎጀብ በተነሳ ተቃውሞ ንብረት መውደሙ ተሰማ

በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ አካባቢ ሐሙስ ሚያዚያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተቀሰቀሰ ግጭት፣ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ በርካታ ንብረት መውደሙን የሪፖርተር ምንጮች አስታወቁ፡፡ የግጭቱ መነሻ የሆነው ጉዳይ በጎጀብ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች፣ የጎጀብ እርሻ ልማት ይዞታ ተከፋፍሎ ይሰጠን በማለት ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሳይገኝ በመቆየቱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ቆይታ ገደብ የተወሳበት የሐዋሳው ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተሰየሙ በኋላ፣ እጅግ በጣም የተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳ ይዘው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በአዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተጓዙ ሲያወያዩና ንግግሮችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡

በሸካ ደን በተነሳ ሰደድ እሳት በ200 ሔክታር ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት ወደመ

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ዓርብ መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. የተነሳ ሰደድ እሳት፣ 200 ሔክታር በሚገመት መሬት ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ደን አወደመ፡፡ በሳምንቱ ዓርብ መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ሰደድ እሳቱ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱ የተገታ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ግን አለመጥፋቱ ታውቋል፡፡ በምዕራብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቦራ ዞን ጎሬ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ሸካ ዞን ማሻ ከተማ በሚወስደው መንገድ 14 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኝ ተፈጥሯዊ ደንና ውኃ አዘል መሬት ላይ ሰደድ እሳቱ ተከስቷል፡፡

በካፋ ዞን በተከሰተ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ታወቀ

በደቡብ ክልል ካፋ ዞን በዴቻና በጨታ ወረዳዎች ጠረፍ አካባቢ በመኤኒት አርብቶ አደሮችና በወረዳዎቹ ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት፣ የሰዎች ሕይወት እንደጠፋና በርካታ ከብቶች እንደተዘረፉ ምንጮች ከሥፍራው ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ወደ ውጭ በቀጥታ መላክ የሚችሉበትን ስምምነት ፈጸሙ

​​​​​​​በአዲሱ የቡና ንግድ አዋጅ መሠረት አቅራቢና ላኪዎች በጋራ እንዲሠሩ ባስቀመጠው ሥርዓት በመጠቀም፣ የደቡብ ቡና አቅራቢዎች ዘርፍ ማኅበር ከመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ቡናን በቀጥታ መላክ የሚችልበትን ዕድል አስጠብቋል፡፡

ደኢሕዴን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ባጠናቀቀው ስብሰባው አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡

በጉራፈርዳ 55 ሰዎች መግደላቸው የተረጋገጠባቸው ተከሳሾች የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወሰነባቸው

በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ መለያ፣ ኮመታ፣ ጋቢቃ፣ ኩኪ፣ ኡይቃ፣ ቢቢታ፣ ስመርታና ከነዓን ቀበሌዎች በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆችና በፌዴራል ፖሊሶች ላይ በድምሩ የ55 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋታቸው የተረጋገጠባቸው 18 ተከሳሾች፣ በዕድሜ ልክና ከሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት እስከ 22 ዓመታት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጠ፡፡

በሐዋሳ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ውዝግብ አስነሳ

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ፕሮጀክት የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ተነሳበት፡፡ ሆቴሉ ሊገነባበት በታሰበበት ቦታ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳው የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑም ታውቋል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር የሆነን ሆቴል በሐዋሳ ለመገንባት  የይሁንታ ደብዳቤ በከተማ አስተዳደሩ ተሰጥቶኛል የሚሉት ባለሀብቱ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው፣ ሆቴሉን ለማስገንባት ዲዛይን ለማሠራት ያደረጉት እንቅስቃሴ መደናቀፉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ፍርደኞችና ክሳቸው የተቋረጠ እስረኞች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው እንዲፈቱ ተወሰነ

በተከሰሱበት ወንጀል የተፈረደባቸውና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ በመንግሥት የተወሰነላቸው 746 እስረኞች የሚፈቱት፣ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቦ ከፀና በኋላ የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 417 ፍርደኞች ይቅርታ እንዲደረግላቸው በፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ተወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቧል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረትም ጉዳያቸው በመታየት ላይ የነበረ የ329 ተጠርጣሪዎችን ክስ ይቋረጣል፡፡

በአማራ ክልል የተፈረደባቸውና ጉዳያቸው በመታየት ላይ ያሉ 2,905 ግለሰቦች እንዲለቀቁ ተወሰነ

መንግሥት የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና አገራዊ ስምምነት ለማምጣት በማለት፣ ጉዳያቸው በመታየት ላይ ያሉና በተከሰሱበት ወንጀል የተፈረደባቸውን እንደሚለቅ በተናገረው መሠረት፣ ከአማራ ክልል በአጠቃላይ 2,905 ግለሰቦች እንዲለቀቁ ተወሰነ፡፡