Skip to main content
x

የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ መንግሥት ዕርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

አንድ ሦስተኛ ያህሉ ጎልማሶች ለደባል አጫሽነት ተጋልጠዋል በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ 3.2 ሚሊዮን ትምባሆ አጫሾች እንዳሉ፣ በጎልማሳነት የዕድሜ ክልል ከሚገኘው አንድ ሦስተኛ ያህሉ ደግሞ ለደባል (ለእጅ አዙር) አጫሽነት እንደተጋለጠና ኅብረተሰቡን ከዚህ ዓይነት አደጋ ለመታደግ የሚያስችል አስቸኳይ ዕርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ሲጋራ ማጨስን አስመልክቶ የተሠራውና ሰሞኑን ይፋ የሆነው የዳሰሳ ጥናት አመለከተ፡፡ 

ኢትዮጵያ ከልጅነት ልምሻ ነፃ ሆነች

ቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል ኢትዮጵያ ከልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) በሽታ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ነፃ መሆኗን ለዚህም በአፍሪካ ደረጃ ከተቋቋመው የአፍሪካ አህጉር የፖሊዮ ነፃ ማወጅ ተቋም (አፍሪካ ሪጅናል ሰርቲፊኬሽን ኮሚሽን) ዕውቅናና ተቀባይነትን ማግኘቷን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ቅንጨራን ለመከላከል ባለድርሻዎች ተናበው እንዲሠሩ ተጠየቀ

በሥርዓተ ምግብና በንፅሕና ላይ የሚሠሩ ተቋማት ቅንጨራን ለመከላከል ተናበው መሥራት ካልቻሉ ለውጥ ማምጣት አይቻልም ተባለ፡፡ መቀንጨርንና የሥርዓተ ምግብ ችግርን ለመቅረፍ በሚሠሩ ሥራዎች ላይ ኃላፊነት ወስደው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እርስ በርስ ተረዳድተው መሥራት ካልቻሉም መቀንጨርን ለማጥፋት የተያዘውን የሰቆጣ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2030 እንዳይሳካ ምክንያት እንደሚሆን የሰቆጣ ስምምነት የሴክተር ማጠናከር ኃላፊዋ ወ/ሮ ጽጌረዳ አብርሃም ገልጸዋል፡፡

በርካቶችን የሚቀጥፈው የነርቭ መዋቅር ክፍተት

በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአደጋ፣ በበሽታና በተለያዩ አጋጣሚዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ በየቀኑ 151,600 ሰዎች ሲሞቱ በተቃራኒው ደግሞ በየደቂቃው 250፣ በየሰዓቱ 15,000፣ በየዓመቱም 360,000 ሕፃናት ይወለዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እንደተወለዱ የሚሞቱ፣ አልያም ዕድሜ ልካቸውን አብሯቸው ከሚቆይ የአካል ጉዳት ጋር አብሮ ለመኖር የሚገደዱ አሉ፡፡ ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱ የተለያዩ ሕመሞች መካከል ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የጤና ዕክሎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡

የጀርባ አጥንት መጣመም ችግር ላለባቸው 80 ወጣቶች የማቃናት ሥራ ተከናወነላቸው

‹‹በዓለም ከፍተኛ የጀርባ አጥንት መጣመም የሚታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው›› የአዲስ አበባ ቃጠሎና ድንገተኛ ሆስፒታል (አቤት)፣ በኅብለ ሰረሰር ቀዶ ሕክምና የጀርባቸውን አጥንት የማቃናት አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ከመዘገባቸውና የጀርባ አጥንት መጣመም (ስኮላይሰስ) ችግር ካለባቸው 2,400 ታዳጊ ወጣቶች መካከል ለ80 ያህሉ አገልግሎቱን መስጠቱንና ሕክምናውም ቀጣይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የጨቅላ ሕፃናትን ክትባት በፈለጉት ጤና ተቋማት ማግኘት እስከምን?

የመጀመሪያ ልጇን ብራስ የእናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ለወለደችው እናት፣ ለሕፃኗ የመጀመሪያውን መሠረታዊ ክትባት ለማግኘት ምንም ችግር አልገጠማትም፡፡ የሕፃኗን የክትባት መረጃ የያዘውን ቢጫ ካርድም ከሆስፒታሉ ወስዳለች፡፡ ቀጣዩን ክትባት እዛው ብራስ፣ በኋላ ደግሞ ለመታረስ ከነበረችበት ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኝ ጤና ጣቢያ አስከትባለች፡፡

በ13 ቢሊዮን ብር ወጪ ከ2000 በላይ የጤና ፕሮጀክቶች ተከናውነዋል

በኢትየጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በጤና መሠረተ ልማት አቅርቦት ላይ ያተኮሩ 2,483 ፕሮጀክቶች በ13 ቢሊዮን ብር ወጪ ተከናውነው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አሚር አማን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ላቦራቶሪዎች፣ የጥናትና ምርምር ክፍሎች፣ የደም ባንኮች፣ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖች፣ ወዘተ ከተካተቱባቸው ከእነዚሁ የጤና መሠረተ ልማት አቅርቦት ፕሮጀክቶች መካከል 265ቱ የተከናወኑት በክልል መንግሥታት ሲሆን፣ የቀሩት 2218 የሚሆኑት ፕሮጀክቶች የተሠሩት ደግሞ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነው፡፡

በኤችአይቪ ዙሪያ አገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነው

ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል በተሠሩ ሥራዎች፣ በተገኙ ውጤቶች፣ ተግዳሮቶችና በዘርፉ ባለው መቀዛቀዝ ላይ ያተኮረና አጠቃላይ ሥራውን የሚገመግም አገር አቀፍ ጥናት መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚጀመር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የመኖር ዕድሜ ቢጨምርም ተላላፊ በሽታዎች ሕይወት እየነጠቁ መሆኑ ተመለከተ

ኢትዮጵያውያን በሕይወት የመኖር ዕድሜያቸው ከዚህ ቀደም ከነበረው ቢጨምርም፣ ተላላፊ በሽታዎች ሕይወት እየነጠቁ ነው ሲል እ.ኤ.አ. በ2016 የተከናወነውና ሰሞኑን ይፋ የሆነው ‹‹ግሎባል በርደን ኦፍ ዲዚዝ›› አመለከተ፡፡