Skip to main content
x

የትግራይ ክልል ለወጣቶች ከተመደበለት 562 ሚሊዮን ብር ውስጥ 105 ሚሊዮን ብር ብቻ መጠቀሙን አስታወቀ

የፌዴራል መንግሥት ያለውን የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የአሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ በጅቶ ለክልሎች እያከፋፈለ ቢሆንም፣ ከዚህ ውስጥ የትግራይ ክልል 562 ሚሊዮን ብር እንደተመደበለት ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውስጥ ክልሉ እስካሁን ድረስ 105 ሚሊዮን ብር ብቻ መጠቀሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የትግራይ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረሚካኤል መለስ ዓርብ ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የተበጀተው ገንዘብ የሚለቀቀው በሁለት ዓመት በመሆኑ ባለፈው ዓመት 205 ሚሊዮን ብር የፌዴራሉ መንግሥት እንዳላከና መጠቀም የተቻለው 105 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ተገለጸ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) በዚህኛው በጀት ዓመት ምንም ዓይነት ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ተናገሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራም በጀት አሠራርን በደንብ እንዲተገብሩም ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ቅኝት የተካሄደባቸው የአዲስ አበባ ተቋማት መንግሥትን ለአላስፈላጊ ወጪ መዳረጋቸው ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት በጀትና ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በ26 ባለበጀት የከተማው አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ግምገማ አስተዳደሩን ለአላስፈላጊ ወጪዎች የዳረጉ ክስተቶች መታዘቡን አመለከተ፡፡