Skip to main content
x

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዱ ፈተና የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ ነው!

ሐሙስ ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና ሲዘከር የዘንድሮ መሪ ቃሉ ‹‹ሥልጣን ከልኩ እንዳያልፍ መጠበቅና በዓይነ ቁራኛ መቆጣጠር…›› የሚል አንድምታ አለው፡፡ ጋና ይኼንን ዓለም አቀፍ በዓል የምታስተናግደው የፕሬስ ነፃነትን ተቋማዊ ለማድረግ ባሳየችው ግስጋሴ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2017 የዓለም የፕሬስ ነፃነት መመዘኛ ከ180 አገሮች 20ኛ ደረጃ በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆኗ ነው፡፡

የለውጥ ሒደቱን መደገፍ የለውጥ አካል መሆን ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢሕአዴግ ሊቀመንበር እንዲሆኑ ከተመረጡና በፓርላማ ከተሰየሙ ጊዜ ጀምሮ፣ አገሪቱ ላይ አንዣቦ የነበረው የሥጋት ደመና እየተገፈፈ ነው፡፡ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በመገኘት ከሕዝብ ጋር እያደረጉ ባሉት ውይይትም ይህ እውነታ በሚገባ ተንፀባርቋል፡፡ እሳቸው እያስጀመሩ ያሉትን የለውጥ ሒደት በመደገፍ ሕዝብ በግልጽ እየተናገረም ነው፡፡

አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ ጠንክሮ መገኘት የግድ ይላል!

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቁ ችግር የመወዳደሪያ ሜዳው እንደነበር ብዙ ተብሎለታል፡፡ የፖለቲካ ምኅዳር በመባል የሚታወቀው የመወዳደሪያ ሜዳ አባጣና ጎርባጣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ፈታኝ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በተለይ ያለፉት 27 ዓመታት ውጣ ውረዶች ብዙ የሚናገሩት አላቸው፡፡

አገር በመላምት አይመራም!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ከጨበጡ ሦስት ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ ብዙ ጊዜያቸውን በአዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ ክልሎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሲነጋገሩና መልዕክት ሲያስተላልፉ ሰንብተዋል፡፡ በንግግሮቻቸውም የብዙዎችን ቀልብ ስበዋል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ አዲሱን ካቢኔያቸውን በፓርላማ አፀድቀዋል፡፡ ተጨማሪ ሹመቶችንም ሰጥተዋል፡፡

ለበጎ የታሰበው ክፋት እንዳያበላሸው!

በመላ አገሪቷ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ተሞልተው የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እያከናወኑ መሆናቸው፣ አገሩን ለሚወድ ማንኛውም ሰው ዕፎይታ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለጋራ ዓላማ አብረው ለመሠለፍ የሚያስችላቸው ጅማሬ እየታየ በመሆኑ፣ ብዙዎች መጪውን ጊዜ በብሩህ ተስፋ ተሞልተው ቢጠብቁ አይገርምም፡፡

ኢትዮጵያ የምትደምቀው በልጆቿ አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር ናት ሲባል ያለፈችባቸው ዘመናት ውስብስብ እንደነበሩም መዘንጋት አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገሩን ነፃነት ለማስከበር ያደረጋቸው ተጋድሎዎች፣ ለመብቱና ለነፃነቱ ያደረጋቸው ፍልሚያዎች፣ የማንነትና የሐሳብ ብዝኃነት ባለመስተናገዳቸው ሳቢያ የተፈጠሩ ግጭቶች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሥልጣኔዋ ተለያይታ ለድህነትና ለተመፅዋችነት የተጋለጠችበት አሳፋሪ ውርደት የታሪኳ አካል ናቸው፡፡

የአመራር ለውጡ በስኬት እንዲታጀብ የድርሻን ማዋጣት ይገባል!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) መንግሥት ከተመሠረተ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰይመዋል፡፡ የመጀመርያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሞት፣ ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መልቀቂያ በማቅረብ ሲሰናበቱ፣ ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተተክተዋል፡፡ አገሪቱን ነውጥ ውስጥ በመክተት ቀውስ በፈጠረው የሦስት ዓመታት ያህል ተቃውሞ ምክንያት የመጡት የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከፊታቸው ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንዲጀመር ከማደናቀፍ መደጋገፍ ይቅደም!

ኢትዮጵያ ከአንድ የታሪክ ምዕራፍ ወደ ሌላው እየተሸጋገረች ዘመናትን ያስቆጠረች ባለታሪክ አገር ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ከዘመነ መሳፍንት ወደ ማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ፣ ከአሀዳዊ ወደ ፌዴራላዊ ሥርዓት የተሸጋገረችባቸው ታሪካዊ ሒደቶች በበርካታ ውጣ ውረዶች ታጅበው እዚህ ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡

ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታኅሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ለአሥራ ሰባት ቀናት አድርጎት በነበረው ስብሰባ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር እንደነበረበት፣ ይኼም ችግር የሕዝብን መብት በማክበርና ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ መግለጫው አክሎም በአገሪቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርከት ባሉ አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋት እየደፈረሰ፣ ሁከት የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱን አስታውቋል፡፡

መሪ ከመተካት በላይ የተመሪው ሕዝብ ጉዳይ ያሳስባል!

ኢሕአዴግ ሊቀመንበሩን ለመምረጥ አንድ ሳምንት ስብሰባ ላይ ከርሟል፡፡ ተመራጩ ሊቀመንበር በፓርላማ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ይሰየማል፡፡ ይህ የኢሕአዴግ አሠራር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነት የመልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ ከአንድ ወር በላይ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አንዱ አነጋጋሪ ጉዳይ ተተኪውን መሰየም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የተተኪው ማንነት በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ቢያነጋግር አይገርምም፡፡