Skip to main content
x

ታሪካዊ መቀራረብ ላይ ያተኮረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኬንያ ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ዓ.ም. ከጂቡቲና ከሱዳን ቀጥለው ባደረጉት ሦስተኛው የውጭ አገር የሥራ ጉብኝት ከሚያዝያ 28 እስከ 29 ቀን 2010 ወደ ኬንያ በማቅናት፣ በጂቡቲና በሱዳን ከተደረጉት መግባባቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ስምምነቶች ላይ ደርሰው ሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመልሰዋል፡፡

ንግድ ምክር ቤት የዓለም ንግድ ምክር ቤቶችን ጉባዔ ለማስተናገድ ከሦስት አገሮች ፉክክር ይጠብቀዋል 

ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር የተፋጠጠችበትንና የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ለማሳየት ያሰናዳችውን ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነድ ከተጨማሪ ማብራሪያዎች ጋር በማጀብ በቻይና በሚደረገው ስብሰባ እንደምታቀርብ ታወቀ፡፡

የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት መታየቱ ተገለጸ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አቢዮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት እንደታየ አስታወቁ፡፡ ኮሚሽነሩ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ዝውውሩን ለመቆጣጠር ባደረገው ጥረት በርካታ መሳሪያዎችን መያዝ መቻሉን ገልጸው፣ የሕገወጥ የመሳሪያዎች ዝውውር ግን ሙሉ በሙሉ ቆሟል ለማለት እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡

ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከስምንት ሺሕ በላይ ሆነ

ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የገቡ ስደተኞች ቁጥር 8,592 መድረሱን የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ይኼንን አረጋግጧል፡፡

መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በፀጥታ ኃይሎች በዘጠኝ ግለሰቦች ላይ በተፈጸመው ግድያ፣ ነዋሪዎች መፈናቀል መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በስምንት የተለያዩ ማዕከላት ተጠልለው ለሚገኙት ተፈናቃዮች አስፈላጊውን ዕገዛ እያደረገ እንደሆነና የተፈናቃዮቹም ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል፡፡

​​​​​​​ከሞያሌ ስለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን መረጃ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ

 በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹በተሳሳተ መረጃ›› በነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ግድያ ተደናግጠው ወደ ኬንያ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ለመመለስና ዕርዳታ የሚያስፈልግ ከሆነም ለማቅረብ፣ መረጃ እየጠበቀ መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢው የሚገኝ የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ መረጃዎችን በራሱ መንገድ እየተከታተለ ነው፡፡ ዝርዝር መረጃ ከኮማንድ ፖስቱ እየጠበቀ መሆኑንም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኬንያ ንግድ ምክር ቤቶች የዓለም ንግድ ምክር ቤቶችን ጉባዔ ለማስተናገድ ተፋጠዋል

የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች አባል የሆኑበትና በየሁለት ዓመቱ በተለያዩ አባል አገሮች እየተዘዋወረ የሚካሔደውን የዓለም የንግድ ምክር ቤቶች ኮንግረስ በአፍሪካ ደረጃ ለማዘጋጀት የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ከኬንያ አቻው ጋር ተፋጧል፡፡

በቆሎ ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንዲደረግ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

በተያዘው የ2009/2010 ምርት ዘመን ትርፍ በቆሎ በመመረቱ፣ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ለማድረግ የመንግሥት ፈቃድ እየተጠበቀ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ፡፡በ2008/2009 ዓ.ም. በተወሰነ ደረጃ ትርፍ በቆሎ ተገኝቶ ስለነበር 620 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ወደ ጎረቤት ኬንያ መላኩ ይታወቃል፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተያዘው ምርት ዘመን በርካታ በቆሎ በመመረቱ ለመንግሥት ውሳኔ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበር ፕሬዚዳንት ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ማኅበር (አሜሰያ) /Association of Member Episcopal Conferences in Eastern Africa (AMECEA)/፣ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

ከኬንያ ድንበር የተመለሰው ስኳር ለአገር ውስጥ እንዲቀርብ ሊወሰን ይችላል ተባለ

ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ለማድረግ ታስቦ ሞያሌ ድንበር ደርሶ የነበረው 4,400 ቶን ስኳር፣ ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርብ ሊወሰን እንደሚችል ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገለጸውን መጠን ስኳር አግሪኮሞዲቲስ ኤንድ ፋይናንስ ለተባለ ኩባንያ ከሸጠ በኋላ፣ ኩባንያው ወደ ኬንያ የሚገባበትን ሁኔታዎች ባለማመቻቸቱ በሞያሌ ድንበር በእርጥበታማ ሙቀት ለሁለት ወራት በተሽከርካሪዎች ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡