Skip to main content
x

የንግድ ምክር ቤት አባልነት በውዴታ ወይስ በግዴታ?

የንግድ ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995 ለማሻሻል ከተለያዩ አካላት የመነሻ ሐሳቦች ቀርበው እየተመከረባቸው ናቸው፡፡ ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላቸው ንግድ ምክር ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 314/1995 መሠረት እንደ አዲስ ሲደራጁ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት የሚል መጠሪያ ይዘው እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡ ይሁንና በዚህ አዋጅ መሠረት ከተደራጁ በኋላ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ሲብላሉ ቆይተው አዋጁን ለማሻሻል ወደሚያስችሉ ተግባሮች እየገባ ነው፡፡

የንግድ ምክር ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረቡ ሁለት ሐሳቦች እየተፋጩ ነው

በመላ አገሪቱ የሚገኙትን የንግድ ኅብረተሰብ ይወክላሉ የተባሉ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ አባላትን እንደያዙ ይነገራል፡፡ እነዚህ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ቀድሞ በንግድ ምክር ቤት አሁን ደግሞ በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የሚል መጠሪያ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይሁንና እነዚህን ተቋማት ከ12 ዓመታት በፊት እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያደረገው አዋጅ ቁጥር 341/95 ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አዋጁ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘርፍ ምክር ቤቶች ከታች ጀምሮ በራሳቸው መዋቅር እንዲደራጁና በየደረጃው ከንግድ ምክር ቤቶች ጋር ተጣምረው እንዲደራጁ መደረጉ፣ የንግድ ምክር ቤቶችን እንቅስቃሴ በተፈለገው ደረጃ አላራመደም በሚል የተለያዩ መከራከሪያዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ንግድ ምክር ቤቱ ለአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት የመሠረት ድንጋይ ሊያስቀምጥ ነው

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ለማስገንባት ያቀደውን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ዲዛይን በማሻሻል ወደ ግንባታ ለመግባት ነገ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ ሊያስቀምጥ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዝቅተኛ በሆነ የሊዝ ዋጋ በቦሌ ክፍለ ከተማ ዳያስፖራ አደባባይ (የቀድሞው ዘርፈሽዋል ትምህርት ቤት) አካባቢ በተረከበው ቦታ የሚያስገነባው ሕንፃ፣ ከ300 እስከ 350 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ እንደሆነ ንግድ ምክር ቤቱ የሕንፃ ግንባታውን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡

የዘርፍ ምክር ቤቶች ውጭ ሄደው በቀሩ አመራሮች ምትክ አዲስ ኃላፊዎችን ሰየሙ

የኢትዮጵያ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከአገር ወጥተው በዚያው በቀሩት ፕሬዚዳንቱ ምትክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሰየመ፡፡ የኦሮሚያና የአማራ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችም እንደወጡ በቀሩት ኃላፊዎች ምትክ ነባሮቹን ምክትል ፕሬዚዳንቶች በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት እንዲሠሩ መመደባቸው ታውቋል፡ ከዘርፍ ምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው በምክር ቤቱ ቦርድ አባላት የተሰየሙት የሶማሌ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ዘርፍ ምክር ቤት ቦርድ አባል ሐሰን አብዱላሂ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የኢትዮጵያና የኬንያ ንግድ ምክር ቤቶች የዓለም ንግድ ምክር ቤቶችን ጉባዔ ለማስተናገድ ተፋጠዋል

የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች አባል የሆኑበትና በየሁለት ዓመቱ በተለያዩ አባል አገሮች እየተዘዋወረ የሚካሔደውን የዓለም የንግድ ምክር ቤቶች ኮንግረስ በአፍሪካ ደረጃ ለማዘጋጀት የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ከኬንያ አቻው ጋር ተፋጧል፡፡

የጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት በ110 ዕድሜው የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት አካሔደ

የኢትዮጵያ ኩባንያዎች አለመገኘታቸው አስተችቷል የተመሠረተበትን 110ኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ባሰናዳው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከ250 በላይ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በርካታ የውጭ ኩባንያዎች የተሳታፉበት ይህ የንግድ ትርዒት፣ እ.ኤ.አ. በ1907 ከተመሠረተ ወዲህ ያካሔደው የመጀመሪያው እንደሆነ የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ዮሱፍ ሙሳ ደዋሌህ አስታውቀዋል፡፡ በንግድ ትርዒቱ ለመሳተፍ፣ ከጃፓን፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ፣ ከቱርክ፣ ከፈረንሳይ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድ፣ ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከሞሪሺየስና ከሌሎችም አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎች በጂቡቲው ዓውደ ርዕይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ለንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነት ለመጀመርያ ጊዜ ከሁለት በላይ ዕጩዎች ቀረቡ

አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውና በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነት ለመጀመርያ ጊዜ ከሁለት በላይ ዕጩዎች ቀረቡ፡፡ ሪፖርተር ሕትመት እስከገባት ዓርብ ምሽት ድረስ አራት ዕጩዎች መጠቆማቸው ታውቋል፡፡

ንግድ ምክር ቤቱ ለሚያዘጋጃቸው ንግድ ትርዒቶች በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአገሪቱ ትልቁ የሚባለውን የአዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚያካሂዳቸውን አራት የንግድ ትርዒቶች ከቀደመው ጊዜ በበለጠ ለማሰናዳት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ ይኼን ያስታወቀው ባለፈው ሐሙስ የሦስቱን የንግድ ትርዒቶች መርሐ ግብር ይፋ ባደረገበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡