Skip to main content
x

ካሩቱሪ በኢትዮጵያ የነበሩትን እርሻዎች እንደ አዲስ ለማስጀመር መቃረቡን አስታወቀ

የህንድ የግብርና ምርቶች ኩባንያ ካሩቱሪ ግሎባል በኢትዮጵያ ሲንያንቀሳቅሳቸው የነበሩና በመንግሥት የተወረሱበትን እርሻዎች ዳግም እንደ አዲስ ለማስጀመር፣ ከመንግሥት ጋር ዕርቅ ማውረዱን አስታወቀ፡፡ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥም እንደ አዲስ ስምምነት በመፈረም በጋምቤላ እርሻው ሥራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነቷን ለፈረንሣይ አስረከበች

ኢትዮጵያ ከመስከረም ወር ጀምሮ በፀጥታው ምክር ቤት የነበራትን የአንድ ወር የፕሬዚዳንትነት ጊዜ ለፈረንሣይ አስረከበች፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ መስከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም. የአንድ ወር ጊዜው መጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ አገሪቱ በመስከረም ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆና በቆየችበት ጊዜ ስድስት የውሳኔ ሐሳቦችና አንድ ፕሬዚዳንታዊ መግለጫ በምክር ቤቱ ተላልፈዋል፡፡

በ291 ከተሞች የታየው የማህተመ ጋንዲ ቴአትር በአዲስ አበባ

በህንድ መዲና ኒው ደልሒ የሚከናወኑ ጥበባዊ መርሐ ግብሮች የሚዘገቡበት ኦል ኢቨንስት ኢን ኒው ደልሒ ድረ ገጽ፣ በቅርቡ ያስነበበው ዮግፑሩሽ ማህተመ ከማህተመ ስለተባለ ቴአትር ነበር፡፡ ‹‹ዩግፑሩሽ ልብ የሚነካ ቴአትር ነው፡፡ በሽሪማዲ እና በማህተመ ጋንዲ መካከል ያለውን ጥብቅ ትስስር ያንፀባርቃል፡፡

የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በተከበረው የደመራ በዓል ላይ የተገኙት የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፣ በኢትዮጵያ አቻቸው በአቡነ ማትያስ ግብዣ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ከልብ እንዳስደሰታቸው ተናገሩ፡፡