Skip to main content
x

በአቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ የተካተቱት የኬኬ ድርጅት ባለቤት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተው አጠናቀቁ

ከግንቦት ወር መጀመርያ ጀምሮ በቁጥጥር ሥር በዋሉትና በመዝገብ ቁጥር 141356 ነሐሴ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ የተካተቱት፣ የሙስና ተግባር ወንጀል ክስ የተመሠረተበት የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ከበደ፣ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተው አጠናቀቁ፡፡

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከ280 በላይ ተጠርጣሪዎችን በታክስና በንግድ ማጭበርበር መያዙን ይፋ አደረገ

ከጥቅምት 1 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኙ 12 የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች አማካይነት በተካሄደ ኦፕሬሽን፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ አራት ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ጨምሮ 281 ተጠርጣሪዎች በፍትሐ ብሔርና በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጓቸውን የታክስና የንግድ ማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ መያዙን አስታወቀ፡፡ 

አቶ መላኩ ፈንታ አፋጣኝ ውሳኔ ለማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ አልጠብቅም አሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ አራት ዓመት ከሰባት ወራት ሲታሰሩ የፍትሕ ፍንጭ ስላላሳያቸው ፈጣሪያቸውንም እንደሚጠራጠሩ ገልጸው፣ የተፋጠነ ውሳኔ ማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ እንደማይጠብቁ ተናገሩ፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ መምርያ ኃላፊና ሦስት ሠራተኞች ክስ ተመሠረተባቸው

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ የቀረጥ ነፃ ማስፋፊያ መምርያ ኃላፊ፣ የቀረጥ ነፃ ማስፈጸሚያ መምርያ ቡድን መሪ፣ የቀረጥ ነፃ ጉዳዮች ቡድን አስተባባሪና የቀረጥ ነፃ ኦፊሰር የነበሩ ሠራተኞች በከባድ ሁኔታ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል በድምሩ ከ21.2 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በድንበር የሚካሄድ ኮንትሮባንድ የአገር ፈተና ሆኗል

ሕገወጥ የመድኃኒት ዝውውር የጤና ዋስትና ሥጋት መሆኑ ተገለጸ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር በምትዋሰንባቸው የድንበር ንግድ ቀጣናዎች የሚካሄደው ሕገወጥ ንግድ፣ አገሪቱን ለውጭ ምንዛሪ ኪሳራና ለማኅበራዊ ደኅንነት ችግር እየዳረገ መሆኑ ተመለከተ፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ የሥራ ኃላፊ በተፈቀደላቸው የዋስትና መብት ላይ የቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተፈቀዱ ከቀረጥ ነፃ መብቶች ማስፈጸሚያ መምርያ ኃላፊ ዓለም ፀሐይ ግርማይ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ሲመረመሩ ከቆዩ በኋላ፣ ጉዳዩን እያየው የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት የ50,000 ብር የዋስትና መብት ቢፈቅድላቸውም ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡