Skip to main content
x

የስድስት ዓመት ሕፃን በምትማርበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ተደፈረች

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቁሟል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ገላን ቁጥር ሁለት ትምህርት ቤት ውስጥ የምትማር የስድስት ዓመት ሕፃን፣ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በሁለት ወጣቶች መደፈሯ ተሰማ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የተንሰራፋውን ሕገወጥ ንግድ ለመግታት አዳዲስ ሥልቶች እንደቀየሰና በተለይ በሰባት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በንግድ ቢሮ ላይ ባካሄደው ጥናት፣ በተለይ በሦስት ዘርፎች የሚገኙ ሰባት ችግሮችን ነቅሶ አውጥቷል፡፡

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት የማዕድን ሚኒስቴር አምስት ሠራተኞች ዋስትና ተፈቀደላቸው

ለአፋር ክልል ከተገዛ የሮለር ፕላስቲክ ፖሊሺት ግዥ ጨረታ ጋር በተገናኘ፣ ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሠራተኞች ዋስትና ተፈቀደላቸው፡፡

የሚኒስቴሩ ሠራተኞች የግዥ ኮሚቴ አባልና ጸሐፊ አቶ የሰውዘር ንጋቱ፣ አባል አቶ ፈቃዱ ራሱና አቶ ዳኛቸው ክንዴ፣ የግዥ ክፍል ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ እማኝና አካውንታንት አቶ ፈለቀ ገብረ ማርያም ናቸው፡፡

የሙስና ክስ በተመሠረተባቸው ባለሀብቶች ላይ የቀረበው ንብረት አስተዳዳሪ ይሾም አቤቱታ ተቀባይነት አጣ

ዓቃቤ ሕግና መርማሪ ቡድን በጋራ እንዲቆጣጠሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ባለሀብቶች ንብረትና ተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ታግዶ ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾም፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አጣ፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት፣ በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የሶማሌላንድ ጉዳይ ፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን በማቃጠል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የሶማሌላንድ መንግሥት ጉዳይ ፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን በማቃጠል ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡ ተጠርጣሪው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለውና በቅርቡ ከሶማሌላንድ ዋና ከተማ ሐርጌሳ ተፈናቅሎ እንደመጣ ለፖሊስ ማስረዳቱን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የፖሊስ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉት ሁለት የጉምሩክ ሠራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በ2004 እና በ2005 በጀት ዓመት መከፈል የነበረበትን ግብር ሳይከፍሉ በመቅረታቸው አራት ሚሊዮን ብር ይከፍላሉ ከተባሉ ግብር ከፋይ 400 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ፣ ሁለት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኃላፊዎች ላይ የክስ መመሥረቻ የመጨረሻ ጊዜ ተሰጠ

ሁለት ተጠርጣሪዎች ከፖሊስ ጣቢያ ተለቀ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት ሁለት ወራት በምርመራ ላይ በነበሩት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎች ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠረት የመጨረሻ 15 ቀናት ተሰጠው፡፡ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ጎን ለጎን ቀረኝ የሚለውን ምርመራ እንዲያካሂድም ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በሙስና የተከሰሱት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተቀጠሩ በሙስናና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ፣ 13 ተከሳሾች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡