Skip to main content
x

ልሂቅ ፕሮፌሰር ዓቢይ ፎርድ  (1927- 2010)

በ1920ዎቹ ዓመታት በማርክስ ጋርቬይ መሪነት ተራማጅ አስተሳሰብ ያራምድ በነበረው የሐርለም ፓን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ራባይ አርኖልድ ጆሹዋ ፎርድ ይጠቀሳሉ፡፡ በማርከስ ጋርቬይ የተመሠረተው ዩኒቨርሳል ኔግሮ ማኅበርም የሙዚቃ ዳይሬክተር ሆነው ከማገልገላቸው ባሻገር ‹‹ወደ አፍሪካ እንመለስ›› በተሰኘው ንቅናቄ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ሲከበር የሙዚቃ ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘንድሮ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ

በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ፈተና መስጠት ከጀመረበት 1938 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ ጊዜው ሁኔታ የሚለዋወጡ የፈተና አስተዳደር ሥራዎች ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ ከዓመት ዓመት እየጨመረ ከሚሄደው የተማሪ ቁጥር አንፃር በየወቅቱ የሚሰጡ ፈተናዎች በሙሉ ተመሳሳይ የፈተና አስተዳደር ሒደትን አይከተሉም፡፡ የኅትመት ሒደቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ያሉ የፈተና ዝግጅት ሒደቶችን ጨምሮ ያሉ ሒደቶች ፈተናው ተጠናቆ የመስጠት ያህል ቀላል እንዳልሆነም መገመት ይቻላል፡፡

በልማዳዊ አሠራሮች የትም መድረስ አይቻልም!

በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች በየዕለቱ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአመርቂ ውጤት ማለፍ የሚቻለው ከልማዳዊ አሠራር በተላቀቁ ሳይንሳዊ ሥነ ዘዴዎች ነው፡፡ ማንኛውም ነገር የሚከናወነውና አፈጻጸሙም የሚለካው በሳይንሳዊ መንገድ በተዘጋጁ መሥፈርቶች ሲሆን ውጤቱ አጥጋቢ ይሆናል፡፡ ይህ ያለንበት ዘመን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ከመራቀቁ የተነሳ፣ በማናቸውም የውድድር መስክ በመፎካከር ማሸነፍ የሚቻለው በቂ ዝግጅት ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የታሪክ ትምህርት ሊከልስ ነው

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጠው የታሪክ ትምህርትና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ አዲስ የመጻሕፍት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን፣ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) ማክሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ባደረገው ፍተሻ መሠረት  የመጻሕፍት ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አገራዊ መግባባት የናፈቀው የሥነ ምግባር ትምህርት 

አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር ባደረገች ማግስት ነበር የትምህርት ፖሊሲ ለውጥ የተደረገው፡፡ ፖሊሲው በትምህርት ሥርዓቱ ልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች እንዲካተቱ አድርጓል፡፡ ከተካተቱም መካከል አንዱ የሥነ ዜጋና የሥነ ምግባር ትምህርት ይገኝበታል፡፡ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ሥራ ላይ ከዋለ የሁለት አሠርታት ዓመታት ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡

ክብር እና ዕውቅና የተቸራቸው አንጋፋዎቹ ፕሮፌሰሮች

ፕሮፌሰር ደምሴ ሀብቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ በአሁኑ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ1972 ዓ.ም. ተባባሪ  ፕሮፌሰር፣ ከሦስት ዓመታት በኋላ ደግሞ ሙሉ ፕሮፌሰር ሆነዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የፔዲያትሪክስና የቻይልድ ኸልዝ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ የፋክልቲው ዲን ሆነው አገልግለዋል፡፡

የማታ ትምህርት ወደ ውድቀት?

ከትውልድ ቀዬዋ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ስምንተኛ ክፍልን አጠናቃ ነበር፡፡ የቀን ተማሪም ነበረች፡፡ አዲስ አበባ ከመጣች ወዲህ ግን የቀን ተማሪ የመሆን ዕድል አላጋጠማትም፡፡ በሰው ቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትምህርቷን የማታ ቀጠለች፡፡

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሁለቱ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየክልሎቻቸው እንዲመደቡ የተደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እንጂ በክልሎች ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ብሔራዊ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ስትራቴጂ በመረቀቅ ላይ ነው

ድርቅ በተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ከአራት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል በግል ተቋማትና በግለሰብ ደረጃ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወነ የሚገኘውን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ብሔራዊ የሚያደርግና መንግሥትንም የሚያሳትፍ ብሔራዊ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ስትራቴጂ በመረቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡