Skip to main content
x

የቅዱስ ላሊበላ ውቅር መቅደሶችን የመታደግ ጅምር

‹‹…የምገልጽበት ቋንቋ የለኝም፡፡ የዚህን ክቡር ሰው፣ ከሁሉም መሬታውያን በጥበብም ሆነ በሥነ ጽድቅ የከበረ ላሊበላ ከአንድ ደንጊያ፣ ከአንድ አለት ፈልፍሎ ዐሥር አብያተ ክርስቲያናትን ያነፀው ዐቢይ ሥራ የምገልጽበት ልሳን የለኝም::›› ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በዛጒዬ ሥርወ መንግሥት ዘመን በላስታ ላሊበላ የተሠሩትን ዕፁብ ድንቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ያከናወናቸው የቅዱስ ላሊበላን ገድል በኋላ ዘመን ላይ የጻፈው ደራሲ ውሳጣዊ ስሜቱን የገለጸበት ነበር፡፡

በመስቀል በዓል የዩኔስኮ ምዝገባ የተፈጠረው ‹‹ስህተት›› በጥምቀቱም ላለመድገም

መሰንበቻውን የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ከሳቡ በዓላት አንዱ ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ነው፡፡ በኢትዮጵያ በአደባባይ ከሚከበሩት በአውራነትም ይጠቀሳል፡፡ ሃይማኖት ከባህል ጋር የነበረውና ያለው የሚኖረው ቁርኝት አሳይነቱም ይጎላል፡፡ ድንበርን አልፎ ባሕርን ተሻግሮ ባዕዶችን ጭምር የማረከ መሆኑም ሌላው ገጽታው ነው፡፡

የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ የማስመዝገብ ማመልከቻ ‹‹በመጋቢት›› ይገባል

በወርኃ ጥር የኢትዮጵያ አደባባዮች በበዓላት ደምቀው ይታዩበታል ከሚያሰኘው አንዱ የጥምቀት በዓል የሚከበርበት መሆኑ ነው፡፡ የውጭ ጸሐፍት ‹‹የአፍሪካው ኤጲፋኒያ›› (African Epiphany) በመባል በልዩ ልዩ ድርሳኖች የሚታወቀው የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት) በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity)  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በይፋ እንቅስቃሴ ከጀመረ ከርሟል፡፡

አክሱምን በምልዓት የሚታደጋት ማን ነው?

መሰንበቻውን አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ የአክሱም ሐውልቶችና ቅርሶች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸው ነው፡፡ የሦስት ሺሕ ዓመታት ባለታሪኳ ጥንታዊቷ አክሱም የዛን ዐረፍተ ዘመን የሚያሳዩ፣ በመንበረ መንግሥትም ሆነ በመንበረ ክህነት የልዕልናዋ መገለጫ የሆኑ ግዙፉን ሐውልቶች፣ ቤተ መቅደሶች፣ የቤተ መንግሥት ፍራሾችን በዕቅፏ ይዛለች፡፡ ጽላተ ሙሴ የሚገኝበት የአራተኛው ምታመት ቅድስት ማርያም ጽዮን፣ የድንጊያ ዙፋኖች፣ የሐውልቶች ፓርክ፣ ድንጉር ቤተ መንግሥት፣ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ለቅርሶች ጥበቃ ተስፋ የተጣለበት ዲጂታል የምዝገባ ሥርዓት

‹‹ካልቸራል ሔሪቴጅ ኢንቨንተሪ ማኔጅመንት ሲስተም (CHIMS)›› በመባል የሚታወቀው የባህላዊ ቅርሶች የምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓት፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ያደረገው ዳታቤዝ ነው፡፡ ቅርሶች በዲጂታል መንገድ የሚመዘገቡበት ሲሆን፣ ቀድሞ የነበረውን በእጅ ጽሑፍ የመመዝገብ (ማንዋል) አሠራር ያስቀራል ተብሏል፡፡

ላሊበላን ለመጠበቅ የተዘረጋው የብረት ጥላ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስላመዘነ ሊነሳ ነው

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል በሚል የከባድ የብረት ምሰሶ የተሠራው ጥላ፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስላመዘነ ሊነሳ እንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ጥላው የተዘረጋው ቅርሱን ከዝናብ፣ ከንፋስና ከመሳሰሉት ተፈጥሯዊ ተፅዕኖዎች ለመከላከል በሚል ቢሆንም፣ ቅርሱን እየተጫነው ነው፡፡ በተለይም ከጊዜ ብዛት ጥላው ያረፈበት የቅርሱ ክፍል እየተሰነጠቀ መምጣቱ በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

እንደ ቅርስ ያልተያዙት የጎንደር ድልድዮች

ኤፍሬም ምትኩ በጎንደር ከተማ የባጃጅ ሹፌር ነው፡፡ ተወልዶ ካደገበት አንገርብ ወንዝ አካባቢ ደፈጫ የሚባል ድልድይ ይገኛል፡፡ ልጅ ሳለ ድልድዩን አፄ ፋሲል (1624-1659 ዓ.ም.) እንዳሠሩትና በድልድዩ የሚተላለፉ ሰዎች ‹‹የፋሲልን ነፍስ ይማር›› እያሉ ያልፉ እንደነበር የተነገረውን ያስታውሳል፡፡

እየጠፉ ያሉትን ባህላዊ ቅርሶች የሚታደጋቸው ማን ነው?

ለኢትዮጵያዊ ጥንታዊነት ምስክርነት የሚቆሙ በተለያዩ ሥፍራዎች በርካታ ባህላዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ ለዘመናት ‹‹የሦስት ሺሕ ዓመት›› ታሪክ የሚለውን ብሒል የሚቀይሩ፣ ከአራት ሺሕ ዓመታት በላይ የሚያስቆጥሩ ግኝቶች፣ በሥነ ቁፋሮ ባለሙያዎች መገኘታቸው ከአሠርት ወዲህ ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡