Skip to main content
x

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ ተጠቆመ

ላለፉት በርካታ ዓመታት የፌዴራል መንግሥት ካቢኔ አባልና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የክልሉ ፓርቲ ሕወሓት መወሰኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ። 

በኤሌክትሪክ ማመንጨት ለሚሰማሩ የግል ኩባንያዎች የተቀመጠው የማመንጫ ጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው

ታዳሽ የኃይል ማመንጫዎችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ለሚሳተፉ የግል ኩባንያዎች ይሰጥ የነበረው የጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው፡፡ የጊዜ ገደቡን ለማራዘም የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 ማሻሻል የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅም ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ብሮድካስት ባለሥልጣን በአዋጅ መጓተት ተልዕኮዬን መወጣት አልቻልኩም አለ

አንድ ክልል በማዕከላዊ ዲጂታል ኔትወርኩ ለመታቀፍ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሏል አራት በሳተላይት የሚሠራጩ ጣቢያዎች የባለቤትነት ይዞታቸውን እንዲያዛውሩ ታዘዘ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የአገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሥርጭት ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለመቀየርና ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን የቴሌቪዥን ሥርጭቶች ለመቆጣጠር የሚያስችል የሕግ ረቂቅ ባለመፅዱቁና ለዓመታት በመጓተቱ፣ የፕሮጀክት ሥራዎቹ ለማከናወን እንቅፋት እንደገጠመው አስታወቀ፡፡

ፓርላማው በ13 ድምፀ ተአቅቦ የደን ልማት ጥበቃ አዋጅን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢሕገ መንግሥታዊ ነው የሚል ክርክር የቀረበበትን የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ በ13 ድምፀ ተአቅቦ አፀደቀ፡፡ ኢሕአዴግ በሚመራበት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ መሠረት የፓርላማ አባላት ከፓርቲው የበላይ አካል የተሰጡ ውሳኔዎችን መቃወም እንደ ዲስፕሊን ጥሰት የሚቆጠር በመሆኑ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቃውሞ ክርክር ያቀረቡ አባላትና ሌሎችም በተቃውሞ ድምፅ ከመስጠት ይልቅ ድምፅ ተአቅቦ ማድረግን መርጠዋል፡፡ አንድ ረቂቅ አዋጅ በ13 የኢሕአዴግ አባላት ድምፅ ተአቅቦ ሲፀድቅም የመጀመርያው ሊሆን እንደሚችል ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅትን የሚተካ ጂኦ ስፓሻል ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው

ለኢንሳ የተሰጠው ተመሳሳይ ኃላፊነት አልተነሳም የክልል ወሰኖችን የማመልከት ኃላፊነት ይኖረዋል ላለፉት 74 ዓመታት የተለያዩ መንግሥታትን እያገለገለ የቆየው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅትን የሚተካ፣ የኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው፡፡ ኤጀንሲውን የሚያቋቁመው ረቂቅ የሕግ ሰነድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ኅዳር 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራን ከመሀል ከተማ ለማንሳት ብድር ተገኘ

የአዲስ አበባ ቄራን ከመሀል ከተማ ወደ ፉሪ ሐና ለማዘዋወር ከፈረንሣይ ልማት ድርጅት ብድር መገኘቱ ታወቀ፡፡ ሰሞኑን ለሕዝብ ተካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሰነድ እንደሚያመለክተው፣ መሀል ከተማ የነበረውን የቄራ ድርጅት ወደ ፉሪ ሐና ለማዘዋወር 70 ሚሊዮን ዩሮ ከፈረንሣይ ልማት ድርጅት በብድር መልክ ተገኝቷል፡፡

ከ57 ዓመታት በኋላ የንግድ ሕግ ረቂቅ ማሻሻያ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ

በተደጋጋሚ ውድቅ የተደረገው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ረቂቅ ሕግ በድጋሚ ቀርቧል ከ1952 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘውን የንግድ ሕግ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን፣ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በተጨማሪም ከ1954 ዓ.ም. ጀምሮ በተግባር ላይ የቆየውንና ተሞክሮ በተደጋጋሚ ውድቅ ተደርጎ የነበረው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉንም ለማሻሻል፣ ድጋሚ ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ መቅረቡንም ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ረቡዕ ኅዳር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት የመሥሪያ ቤታቸውን የሩብ ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ አይኖርም

ኢትዮጵያ ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከአዋሽ-ወልዲያ-መቀሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ እያካሄደች ቢሆንም፣ ዘንድሮ አዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደማይጀመር ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አገሪቱ ሁለት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ቢሆንም ዘንድሮ የሚጀመር ፕሮጀክት የለም፡፡ ከመቼ ጀምሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደሚጀመር አይታወቅም ብለዋል፡፡

ምልዓተ ጉባዔ ለጥቂት ተሟልቶ የተካሄደው የፓርላማ ውሎ

የከተማ ፕላን ረቂቅ አዋጅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተመርቷል ፓርላማው ሐሙስ ኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የነበረውን መደበኛ ስብሰባ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን ምልዓተ ጉባዔ ለጥቂት በማሟላት፣ ለዕለቱ በያዛቸው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡