Skip to main content
x

እየቀነሰ የመጣው የገቢ ንግድ

በአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው ወጪ ቅናሽ እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፡፡ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ዓመታዊ ተከታታይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በተለይ ባለፉት አሥር ዓመታት የገቢ ንግዱ በአማካይ ከ20 በመቶ እያደገ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው የውጭ ምንዛሪ በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው፡፡ ሰሞኑን ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የ2009 ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውም፣ በ2009 በጀት ዓመት ለወጪ ንግድ የወጣው ወጪ ከቀደመው በ5.5 በመቶ ቀንሷል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ ለወጪ ንግድ የሰጠው ትኩረት ተጋኗል እየተባለ ነው

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰሞኑ ዕርምጃዎች ውስጥ የአገሪቱ ባንኮች ከወጪ ንግድ ባሻገር ላሉት ዘርፎች የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ገደብ እንደሚያስቀምጥ ማስታወቁ አንዱ ነው፡፡ ይህ አሠራር ባንኮች በዓመት ከምትሰጡት ጠቅላላ ብድር ውስጥ እንደሚወሰነው መጠን ለኢኮኖሚው ዘርፍ እንዲያውሉ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

የብር የምንዛሪ ተመን በ15 በመቶ ቀነሰ

ለባንኮች የብድር ጣሪያ ሊቀመጥላቸው ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብር ከሌሎች የውጭ ገንዘቦች በ15 በመቶ ቀንሶ ግብይት እንደሚፈጸምበትና ባንኮች ለተቀማጭ ገንዘብ የሚከፍሉት የወለድ መጠን ወደ ሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን አስታወቀ፡፡