Skip to main content
x

‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት

በህዳሴ ግድቡ ላይ ስምምነት መፍጠር እንዳልተቻለ ግብፅ ለአሜሪካ ማሳወቋ ተጠቁሟል የግብፅን የዓባይ የውኃ ‹‹ለአገሪቱ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው›› ያሉት የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁ ነው የተባለው የዓሳ ማምረቻ ከቀናት በፊት በተመረቀበትና በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው፣ ‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፤›› ብለዋል፡፡

ለኮንፈረንስና ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት ማግኘት የሚችሉበት አሠራር መመቻቸቱ ተነገረ

ከአፍሪካ አገሮች ለኮንፈረንስ፣ እንዲሁም ከአውሮፓና ከአሜሪካ ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት የሚያገኙበት አሠራር መመቻቸቱን፣ የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ አስታወቀ፡፡

አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ በኢትዮጵያ የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ መነሻ አላቸው አሉ

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለመሸምገል አሜሪካ ቁርጠኛ ናት ብለዋል የቀድሞው የኢትዮጵያና የኤርትራ አምባሳደር፣ የአሁኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ኃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በኢትዮጵያ እየተከሰቱ የሚገኙ የፀጥታ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ መነሻዎች አሉዋቸው አሉ፡፡ አገሪቱ ከሶማሊያ የሚቃጣባት የሽብር አደጋም አሳሳቢ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

ሰሎሞን ዴሬሳ!

በቅርቡ በ80 ዓመቱ ዜና ዕረፍቱ የተሰማው፣ በዘርፈ ብዙ ዕውቀቱ ተጠቃሽ የነበረው ዕውቁ ገጣሚና ጸሐፊ፣ ጋዜጠኛና የፍልስፍና መምህር ሰሎሞን ዴሬሳ ሥርዓተ ቀብሩ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚኔሶታ ከተማ በግብአተ እሳት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ ነፍስ ኄር ሰሎሞን ዴሬሳ ከ19 ዓመታት በፊት (መስከረም 1991 ዓ.ም.) ከሪፖርተር መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር (በወቅቱ) ገዛኸኝ ጌታቸው ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን ዴሬሳ  (1930 - 2010)

‹‹በአንድ በኩል ስታስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ እኔ የትግራይ ሰው ነኝ፣ እኔ አማራ ነኝ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩም አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ በሴት አያቶቻችን በራፍ ላይ ማን እንዳለፈ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? የእኔን ጥሩ ኦሮሞነት እግዚአብሔርና የሴት አያቶቼ ናቸው የሚያውቁት፡፡ የሁሉንም እንዲሁ፡፡ ጦር ባለፈ ቁጥር በመዋለድ፣ በንግድ በመገናኘት፣ ተቸግሮ ከአገር ወጥቶ ሌላ ቦታ በመኖር ይቀላቀላል፡፡››

ለአሜሪካ የኮንግረስ አባላት የቀረበውን የሰብዓዊ መብት የውሳኔ ሐሳብ መንግሥት አጣጣለው

የአሜሪካ ኮንግረንስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት፣ በአሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ያቀረቡትን ጥያቄ መንግሥት አጣጣለው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን ድሪምላይነር አውሮፕላን ተረከበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን ተረከበ፡፡ ለአፍሪካ የመጀመርያው የሆነው ግዙፍና ዘመናዊ አውሮፕላን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ዓርብ ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ሲደርስ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አቀባበል አድርገዋል፡፡

በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ መንግሥት ለሕዝብ ፍላጎት ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ኒኪ ሐሌ ሰኞ ጥቅምት 13 ቀን 2010 ባደረጉት ቆይታ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው ታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሪፖርተር ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ አምባሳደር ሐሌ ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ የሚሰማውን መግለጽ፣ መንግሥትም ለሕዝብ ፍላጎት ምላሽ መስጠት እንዳለበት መጠየቃቸውን አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ እንዲሰጥበት ተጠየቀ

የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት፣ በአሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ጥያቄያቸውን ለኮንግረሱ በደብዳቤ ያቀረቡት፣ ኮንግረሱ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ለመወያየት የያዘውን ቀነ ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት በመቀየሩ መሆኑ ታውቋል፡፡