Skip to main content
x

መረን የወጡ የኳስ ሜዳ አምባጓሮዎች እስከ መቼ?

የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ በክልል ከተሞች በስታዲየሞች መረን የወጡና ምክንያታዊ ያልሆኑ አምቧጓሮዎችና ውርጅብኞች በርካቶችን ‹‹እግሬን በሰበረው›› ማሰኘት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ደጋፊዎች ችግሮች እንኳ ቢኖሩ ሰከን ብለው መፍትሔውን ከመሻት ይልቅ ክቡር ለሆነው የሰው ልጆች ሕይወትና ንብረት ውድመት ምክንያት እየሆኑ ይገኛል፡፡

126 ሺሕ ኪሎ ሜትር የሚጓዘው የዓለም ዋንጫ የካቲት 17 አዲስ አበባ ይገባል

ብዙዎች የሚመኙት፣ ነገር ግን ጥቂቶች በአራት ዓመት አንድ ጊዜ የሚታደሙበት የዓለም ዋንጫ ዝግጅት በብዙ ውጣ ውረድ የአዘጋጅነቱን ዕድል ባገኘችው ሩሲያ በመጪው ክረምት ይካሄዳል፡፡ በእግር ኳሱ 32 የዓለም ኃያላን የሚፎካከሩበት የዓለም ዋንጫ፣ ከዚያ በፊት ከ50 በላይ አገሮች እንዲጎበኝ በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት ቅዳሜ የካቲት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል፡፡ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ጉብኝት፣ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአሥር አገሮች የጉብኝት ፕሮግራም ተይዞለታል፡፡ የአዘጋጇ ሩሲያ 35 ከተሞችን ጨምሮ ከ50 በላይ በተመረጡ የዓለም አገሮች ይንቀሳቀሳል ተብሏል፡፡

ፊፋ የአስመራጭ ኮሚቴውን ክስ ውድቅ አደረገው

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ)፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያላፀደቀው የፊፋ የምርጫ ሕግ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል በማረጋገጥ፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ ያቀረቡለትን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ጥር 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴሬሽኑ በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ምርጫውንም ፌዴሬሽኑ በራሱ ደንብ እንዲያከናውን አሳስቧል፡፡

ሕጋዊ  አመራር በሌለው ተቋም ስለፍትሕ ማውራት ለማን?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበላይነት ከሚመራቸው ሊጎች መካከል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፤ ከፍተኛ (ሱፐር) ሊግ  እና ብሔራዊ ሊግ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በሁሉም ሊጎች  በጨዋታ ዳኞች ሊሆን ይችላል፣ በሚከሰቱ ስህተቶች ምክንያት የሚደመጡ አስተያየቶችና ትችቶች ከሙያ ሥነ ምግባር ያፈነገጡ እየሆኑ ቀላል የማይባል ጥፋት እያስከተለ ይገኛል፡፡ የክለብ አመራሮችና አሠልጣኞች በተለይ ውጤት ሲርቃቸው ከሙያ ሥነ ምግባር ያፈነገጡ ከፋፋይ አስተያየቶችን ጊዜያዊ መሸሸጊያ ካደረጉት ሰነባብተዋል፡፡

ጉራማይሌው የክለቦች አደረጃጀትና እየጋለ የመጣው የሙያተኞችና የደጋፊዎች ጥያቄ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተደጋግሞ ሰሞነኛ ወሬ ሆኖ ሲደመጥ የሚስተዋለው ከስፖርቱ አዎንታዊ ጎን ይልቅ አሉታዊ ጎን ነው፡፡ ከአሉታዊ ጎኖቹ መካከል ክለቦች የመኖርና ያለመኖር ሕልውናና በእግር ኳሱ ምክንያት ክቡር የሆነው የሰው ሕይወትና ንብረት ውድመት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ለእግር ኳሱ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን፣ ለኅብረተሰቡ በሚሰጡት ማኅበራዊ ግልጋሎት ጭምር ትልቅ ስምና ዝና ያላቸው ‹‹ውጤት›› ወይም ደግሞ ‹‹ተገቢ ክብር አልተሰጠንም›› በሚል እንዲፈርሱ የተደረጉና ለመፍረስ ከጫፍ የደረሱ ክለቦች ቁጥር እየበረከተ መምጣቱን የሚናገሩ አሉ፡፡ ከነዚህ አስተያየት ሰጪዎች መካከል የኢትዮጵያ ባንኮች ስፖርት ማኅበር ደጋፊዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

መራጭ ተመራጭና አስመራጭ ሆድና ጀርባ የሆኑበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮችን ለመምረጥ የሚደረገው ሽኩቻ ከፖለቲካዊ ቅስቀሳና እንቅስቃሴ ባልተናነሰ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ይገኛል፡፡ በአንድም ሆነ በሌላ ይህ ተጋግሎ የቀጠለው ሽኩቻ፣ በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙት የአህጉራዊም ሆነ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ አስተዳዳሪዎች፣ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2020 እንደምታስተናግደው የሚጠበቀውን የቻን ውድድር አገሪቱ በገባችበት የምርጫ አተካሮ ምክንያት፣ ለሌላ አገር አሳልፈው ሊሰጡ የሚችሉበት ዕድል ሊፈጠር የሚችልበት ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡

ወጥነት ያጣው የፕሪሚየር ሊግ ጉዞ

የኢትዮጵያ ፕሪሚያር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት 11 ሳምንታት ውስጥ የተመዘገቡት ነጥቦችና መረብ ላይ ያረፉት ቁጥሮች እያሸቆለቆለ መጥቷል፡፡ በተለይ ጨዋታዎቹ ያለምንም ግብ ማጠናቀቃቸውና እኩል ግብ ሲጠናቀቅ ማየት እየተለመደ በመምጣቱ የስፖርት ተመልካቹን ያሰለቸ ይመስላል፡፡ ባለፉት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመናት በበላይነት ያጠናቅቃሉ ተብለው ግምት የሚሰጣቸው የነበሩ ክለቦች፣ ዘንድሮም በተመሳሳይ መንገድ እየሄዱ ነው፡፡ በአንፃሩ ፕሪሚየር ሊጉ ሁሌም በበላይነት የሚያጠናቅቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀላሉ ጨዋታን አሸንፎ መውጣት ሲቸገር ቢስተዋልም፣ የደደቢት ወቅታዊ የድል ጉዞ ከወዲሁ ትልቅ ግምት እንዲቸረው አስችሎታል፡፡