Skip to main content
x

የቻይና ጎዳናዎችን ያጥለቀለቀው ‹‹ሕገወጥ›› የአትሌቶች ጉዞና ተሳትፎ

ኢትዮጵያ በዓለም የስፖርት መድረክ ከፍ ብላ ከምትታወቅባቸው ኩነቶች ዋነኛው አትሌቲክስ ነው፡፡ ይህ የዘርፍ ምንም እንኳ በበርካታ ወርቃማ ድሎች የታጀበና አገሪቱም ቀና ብላ ከምትታወቅባቸው መድረኮች አንዱ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ውጤታማና ስኬታማ ነው ማለት እንደማይቻል የሚናገሩ አሉ፡፡

ሦስተኛው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተጀመረ

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች የሚያከናወነውንና ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ገንዘቤ ዲባባና ሐጎስ ገብረ ሕይወት በ1,500 ሜትርና በ3,000 ሜትር አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

የክለብ ምሥረታ ጅምር ስኬት እንደማይሆን ከብርሃንና ሰላም በላይ ምስክር ከየት?

በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች በትልቁ ትኩረት ከሚሰጡት እግር ኳስ ጀምሮ ሌሎችም ስፖርቶች በኢትዮጵያ ሲመሠረቱ እንዴትና ለምን እንዲሁም በምን ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ እንደሚቋቋሙ ብቻ ሳይሆን፣ ተጠያቂነትም ስለሌለው የፈረሱ ቡድኖችና ክለቦች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ይታመናል፡፡ እንዲያውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‹‹አፈርሳለሁ›› የሚለው ቃል ክለብ አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት ሳይቀር ማስፈራሪያ እስከመሆን መድረሱ እየታየና እየተሰማ ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ኢትዮጵያን አደነቀ

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም በዚሁ እያስመዘገበች ያለውን ውጤት አደነቀ፡፡ አገሪቱ ለዋዳ ፀረ አበረታች ቅመሞች ዘመቻና ለሦስትዮሽ ፕሮግራሞች ትክክለኛ ማሳያ መሆኗን የዋዳ ምክትል ዳይሬክተር ሮበርት ኮህለር ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ፣ ኢትዮጵያ በተለይ በአትሌቲክሱ ዓለም ላይ ያላትን የበላይነት ግምት ውስጥ በማስገባት አበረታች ቅመኞች በይበልጥ ይመለከታቸዋል በሚል ለይቶ ካስቀመጣቸው አምስት አገሮች አንዷ አድርጎ ሲመለከታት ቆይቷል፡፡ በዚሁ መነሻነት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ችግሩን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ፣ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት በማቋቋም እንቅስቃሴ ስታደርግ መቆየቷ አይዘነጋም፡፡

ሩጫና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዱባይ ማራቶን

ዓርብ ጥር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ዱባይ አውራ ጎዳናዎች በኢትዮጵያውያንና ከፍ ብሎ በተውለበለው ሰንደቃቸው ጎልተው የታዩበት ክስተት ዕውን ሆኗል፡፡ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ዓመታዊ የማራቶን ውድድሮች አንዱ እንደሆነ በሚነገርለት ዱባይ ማራቶን፣ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ለውድድሩ የተዘጋጀውን ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ጠራርገው የግላቸው በማድረግ ብቃታቸውን ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በወንዶች ሙስነት ገረመው፣ በሴቶች ደግሞ ሮዛ ደረጀ የወርቅ ሜዳሊያውን በመውሰድ ቀዳሚዎች ሆነዋል፡፡

ሁለቱ የረዥም ርቀት ባለታሪኮች በለንደን ማራቶን ሊገናኙ ነው

በረዥም ርቀት በማይታመን ብቃትና ፍጥነት በአሸናፊነቱ የሚታወቀው ቀነኒሳ በቀለ ሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚካሄደው ለንደን ማራቶን ከእንግሊዛዊው ሞ ፋራህና ከኬንያዊው ኤሉዱ ኪብቾጌ ጠንካራ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ለበርካታ ጊዜያት ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የከረመችው መሠረት ደፋር የመጀመርያዋን የማራቶን ሩጫ በቶኪዮ እንደምታደርግ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማኅበር (አይኤኤኤፍ) ዘገባ አመልክቷል፡፡

በአትሌቲክስ ዝቅተኛ ውጤት በሚታይባቸው ርቀቶች ሻምፒዮና ሊዘጋጅ ነው

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄድ ዝቅተኛ ተሳትፎና ውጤት የሚታይባቸውን የአትሌቲክስ ተግባራት ለማጠናከር ሻምፒዮና ሊዘጋጅ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ ከጥር 15 እስከ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የአጭር፣ የመካከለኛ፣ የዕርምጃና የሜዳ ተግባራት የሚያጠቃልለውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፌዴሬሽኑ ድረ ገጽ አስታውቋል፡፡

የ2017 የአትሌቲክስ ትውስታዎች

ዓለም ታኅሣሥ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2017 በአትሌቲክሱ አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ የተከናወኑት የረዥም ርቀት ውድድሮች የሁሉንም ቀልብ መግዛት ችለዋል፡፡ በተለይ በ5ሺሕ ሜትር ርቀት ላይ ፉክክሩ ልዩ ነበር፡፡ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ኤይኤኤኤፍ የ2017 የአትሌቲክስ ቅኝት መሠረት በተለይ ረዥም ርቀቱን ይበልጥ ተመልክቶታል፡፡

የታላቁ ሩጫ የክልል ጉዞ ከሐዋሳ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓልን በማስመልከት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በክልሎች ሊያከናውን ካቀዳቸው የጎዳና ውድድሮች ቀዳሚውን በሐዋሳ አከናወነ፡፡ እሑድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ውድድሩን የጀመረው ታላቁ ሩጫ የተለያዩ የክለብ አትሌቶች የከተማዋ ነዋሪና የንግድ ባንኩ ደንበኞችን አሳትፏል፡፡