Skip to main content
x

ለነዳጅ ታሪፍ ጭማሪ የዘገየው የመንግሥት ምላሽ አንድምታ

የነዳጅ ትርፍ ህዳግ (ታሪፍ) ለዓመታት ባለመስተካከሉና የዘርፉ ቢሮክራሲ ከመቃናት ይልቅ እየተወሳሰበ በመቀጠሉ፣ በርካታ የነዳጅ ማመላለሻ ትራንስፖርት ባለቤቶች እንዲሁም የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ሥራ ማቆምን አማራጭ አድርገው ማሰብ ጀምረዋል፡፡ ነዳጅ ለኢትዮጵያ ዋነኛው ስትራቴጂክ ሸቀጥ ቢሆንም፣ መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመንፈጉ የነዳጅ ዘርፍ ነጋዴዎች ለኪሳራ በመዳረጋቸው ኪሳራውን መሸከም የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አበክረው እያሳወቁ ነው፡፡ በመንግሥት ቸልተኝነት እያዘኑ ከሚገኙ ዋነኛ የነዳጅ ዘርፍ ተዋናዮች መካከል አቶ ፀጋ አሳመረ ይገኙበታል፡፡ የ77 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው አቶ ፀጋ፣ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማመላለሻ ትራንስፖርት፣ በነዳጅ ማደያ ዘርፍ እንዲሁም በነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ ውስጥ ለ56 ዓመታት ጉልህ ሥፍራ ይዘው ቆይተዋል፡፡

በአራት ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት ታስቧል

ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው የኢንቨስትመንት ኩባንያ ፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ከተለያዩ የእስያ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአራት ቢሊዮን ዶላር ወጪ የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ ታወቀ፡፡

በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ለመሰማራት አራት ኩባንያዎች ፈቃድ ወሰዱ

በአገሪቱ የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ የሚሰማሩ ኩባንያዎችን ቁጥር ወደ 22 የሚያሳድጉ አራት አዳዲስ አገር በቀል የነዳጅ ኩባንያዎች፣ ወደ ገበያ ሊያስገባቸው የሚችል ፈቃድ መውሰዳቸው ተገለጸ፡፡ በተመሳሳይ ሥራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ሌሎች ኩባንያዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡

ጎመጁ ኦይል ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች አስገባ

የነዳጅ ማከፋፈል ኢንዱስትሪን በቅርቡ የተቀላቀለው ጎመጁ ኦይል የተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ፣ አገሪቱ ውስጥ ያለውን የነዳጅ ማደያ እጥረት ለመቅረፍ እንደሚረዱ የታመነባቸውን ስድስት ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ገዝቶ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ አስገባ፡፡

የኢትዮጵያን መርኮቦች በባህር ላይ ነዳጅ የሚሞላው አዲሱ የጂቡቲ ኩባንያ

‹‹ሬድ ሲ ባንከሪንግ›› በሚል ሥያሜ ከተቋቋመ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረው ኩባንያ፣ በራሱ መርከብ አዲስ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ ኩባንያው በጂቡቲ መንግሥት የ55 በመቶ ድርሻ እንዲሁም በዱባዩ ዩናይትድ ካፒታል ኢንቨስትመንትስ ግሩፕ የ45 በመቶ ድርሻ የተቋቋመ ነው፡፡

ከጂቡቲ ኢትዮጵያ ሊዘረጋ የታሰበው የነዳጅ መስመር ፕሮጀክት ታጠፈ

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከጂቡቲ ወደብ ወደ መሀል አገር የምታስገባው የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት እንደታጠፈ ታወቀ፡፡ ተቀማጭነቱ በደቡብ አፍሪካ የሆነው ብላክ ራይኖ የተባለ ኩባንያ ከጂቡቲ ወደብ አዋሽ አርባ የሚገኘው የነዳጅ ዴፖ የሚደርስ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመዘርጋት የሚያስችል ዕቅድ፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ነዳጅ ድርጅት የአንድ ዓመት ነዳጅ ግዥ ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2010/2011 በጀት ዓመት ፍጆታ የሚውል የነዳጅ አቅርቦት ስምምነት ትራፊጉራ ከተሰኘ የስዊዘርላንድ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌትና ሱዳን መንግሥታት ጋር በገባው ውል መሠረት አብዛኛውን ነዳጅ የሚገዛው ከሁለቱ አገሮች ሲሆን፣ የተቀረውን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በየዓመቱ በሚያወጣው ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ይገዛል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የተንሰራፋውን ሕገወጥ ንግድ ለመግታት አዳዲስ ሥልቶች እንደቀየሰና በተለይ በሰባት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በንግድ ቢሮ ላይ ባካሄደው ጥናት፣ በተለይ በሦስት ዘርፎች የሚገኙ ሰባት ችግሮችን ነቅሶ አውጥቷል፡፡

‹‹የዓለም የነዳጅ ዋጋ ካልጨመረ በስተቀር በምንዛሪ ለውጥ ምክንያት ዋጋ አይጨምርም››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ካልጨመረ በስተቀር የአገር ውስጥ የነዳጅ መቸርቸሪያ ዋጋ በብር የዶላር ምንዛሪ ለውጥ ምክንያት ጭማሪ እንደማይደረግበት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

አዲስ የነዳጅ ኩባንያ በነዳጅ ማከፋፈል ሥራ እንዲሰማራ ፈቃድ ተሰጠው

ኢትዮጵያ ነዳጅ ንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች 18 መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡ ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በአገሪቱ የነዳጅ ችርቻሮ ሥራና ተያያዥ ተግባራት ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ 18ኛውን አዲስ ኩባንያ ወደ ሥራ ሊያስገባ የሚያስችለው ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡