Skip to main content
x

ግብፃዊያን በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ ነው

ግብፃዊያን ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው፣ ይህንን አመለካከት ወደ አንድ ሐሳብ ለማምጣትና የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ 30ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመካፈል የመጡና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አብዛኛው የግብፅ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ሁሉም ግብፃውያን የጋራ አቋም እንደሚኖራቸው ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የአገሪቱ ሕዝብ ከመንግሥት አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በሱዳንና ሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው በሱዳንና በሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር፣ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሪፖርተር ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለጉዳዩ በጣም ቅርብ የሆኑ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት ፍርደኛ ኢትዮጵያውያኑን ከሱዳንና ከሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች ለማዘዋወር በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው፣ ሕጋዊ ሥልጣን ያለው የአገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ነው፡፡

ግብፅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የለኝም አለች

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በቀጥታ በቴሌቪዥን ለግብፃውያን ባስተላለፉት መልዕክት፣ አገራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የላትም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ‹‹በቀጣናው ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ጠንቅቀን የምናውቅ በመሆኑ ግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአገሮችን ሉዓላዊነት አትደፍርም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ግብፅ ከወንድሞቿ ጋር ወደ ጦርነት አትገባም፡፡ ምክንያቱም ሰላም አንዱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፤›› ማለታቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ‹‹ከማንኛቸውም ጎረቤቶቻችን ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ዕቅዱም ሆነ ፍላጎቱ የለንም፤›› ሲሉ በቀጥታ በተላለፈው የቴሌቪዥን ሥርጭት መናገራቸውን የዜና አውታሮች ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን››

የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በመገንባት ጫናውን ለብቻቸው እንደተሸከሙ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን መልዕክት ሲያደርስና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በተነጋገረበት ወቅት መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያና የግብፅ አዲሱ አሠላለፍ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴ ግድቡን አሞላልና አለቃቀቅ፣ እንዲሁም አካባቢያዊ ተፅዕኖ በተመለከተ የሦስትዮሽ ውይይት ማድረግ ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ሦስቱ አገሮች የጋራ የአጥኚዎች ቡድን በማቋቋም የሦስትዮሽ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የህዳሴ ግድቡ የሚኖረውን ተፅዕኖ እንዲያጠና የቀጠሩት የፈረንሣዩ ‹‹ቢአርኤል›› የተሰኘው ተቋም የሚሠራበትን የመነሻ ሐሳብ ለማርቀቅ ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ቢሆንም ግን በውይይት መነሻ ሐሳቡ ላይ ግብፅና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ይታወቃል፡፡

የዓለም ባንክ በታላቁ ህዳሴ ግድብ አደራዳሪ እንዲሆን በግብፅ መጠየቁ ሥነ ሥርዓት የጣሰ መሆኑ ተገለጸ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የዓለም ባንክ አደራዳሪ እንዲሆን ግብፅ ያቀረበችው ጥያቄ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የተስማሙበትን የውይይት ሥነ ሥርዓት የጣሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የእንግሊዝ ኩባንያ በኢትዮጵያ የ200 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ሊጀምር ነው

ኢንትሬድ የተሰኘውና ዋና መሥሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ኩባንያ በሱዳን ሰፊ የጥጥ እርሻ እንዳለው ከመግለጹም ባሻገር፣ በኢትዮጵያ ሰፊ የጥጥ እርሻ የማልማት ዕቅድ እንዳለውና በ200 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ሦስት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መነሳቱን አስታወቀ፡፡

ግብፅ ለመጪዎቹ 20 ዓመታት ለምትተገብራቸው የግብርናና የውኃ ሀብት ዕቅዶቿን ይፋ አደረገች

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሻኩሪ በናይል ጉዳይ ለመነጋገር ሰኞ፣ ታኅሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ፣ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አቲ ለግብፅ ፓርላማ የ20 ዓመታት የመንግሥታቸውን የውኃና የመስኖ አጠቃቀም ዕቅድን አሰምተዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ ከግብፅ ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ምክክር አይደረግም አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሲወያዩ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ያልተካተተችበት የሁለትዮሽ ምክክር በህዳሴ ግድቡ ላይ እንደማታደርግ አስታወቁ፡፡

ነዳጅ ድርጅት የአንድ ዓመት ነዳጅ ግዥ ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2010/2011 በጀት ዓመት ፍጆታ የሚውል የነዳጅ አቅርቦት ስምምነት ትራፊጉራ ከተሰኘ የስዊዘርላንድ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌትና ሱዳን መንግሥታት ጋር በገባው ውል መሠረት አብዛኛውን ነዳጅ የሚገዛው ከሁለቱ አገሮች ሲሆን፣ የተቀረውን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በየዓመቱ በሚያወጣው ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ይገዛል፡፡