Skip to main content
x

የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምርታማነትን እየጎዳ ነው

የውጭ ምንዛሪ እጥረት የአምራች ኢንዱስትሪውን እግር ከወርች ይዞ አላላውስ እንዳለ የተለያዩ ፋብሪካዎች ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተፈጠሩ ችግሮች ለከፍተኛ ችግር እንደዳረጓቸው አምራቾች ለፌዴራል መንግሥት አስታውቀዋል፡፡ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ፣ የተለያዩ ፋብሪካዎች ባለቤቶችና ተወካዮች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ምርታማነታቸው እንዳሽቆለቆለና ህልውናቸው አደጋ ውስጥ እንደገባ ገልጸዋል፡፡

የንግድ ምክር ቤት አባልነት በውዴታ ወይስ በግዴታ?

የንግድ ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995 ለማሻሻል ከተለያዩ አካላት የመነሻ ሐሳቦች ቀርበው እየተመከረባቸው ናቸው፡፡ ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላቸው ንግድ ምክር ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 314/1995 መሠረት እንደ አዲስ ሲደራጁ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት የሚል መጠሪያ ይዘው እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡ ይሁንና በዚህ አዋጅ መሠረት ከተደራጁ በኋላ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ሲብላሉ ቆይተው አዋጁን ለማሻሻል ወደሚያስችሉ ተግባሮች እየገባ ነው፡፡

የንግድ ምክር ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረቡ ሁለት ሐሳቦች እየተፋጩ ነው

በመላ አገሪቱ የሚገኙትን የንግድ ኅብረተሰብ ይወክላሉ የተባሉ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ አባላትን እንደያዙ ይነገራል፡፡ እነዚህ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ቀድሞ በንግድ ምክር ቤት አሁን ደግሞ በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የሚል መጠሪያ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይሁንና እነዚህን ተቋማት ከ12 ዓመታት በፊት እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያደረገው አዋጅ ቁጥር 341/95 ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አዋጁ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘርፍ ምክር ቤቶች ከታች ጀምሮ በራሳቸው መዋቅር እንዲደራጁና በየደረጃው ከንግድ ምክር ቤቶች ጋር ተጣምረው እንዲደራጁ መደረጉ፣ የንግድ ምክር ቤቶችን እንቅስቃሴ በተፈለገው ደረጃ አላራመደም በሚል የተለያዩ መከራከሪያዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡

እንደወጡ የቀሩት የዘርፍ ምክር ቤት ኃላፊዎች በተቀመጠላቸው ቀነ ገደብ ምላሽ ሳይሰጡ ቀሩ

በቅርቡ ከኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ጋር ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው ሳይመለሱ እንደቀሩ የሚነገርላቸው የኢትዮጵያ የዘርፍ ማኅበራት ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው፣ በሰባት ቀናት ውስጥ ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የዘርፍ ምክር ቤት ቦርድ ያስተላለፈው ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ ተገለጸ፡፡

ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች የሚቀርቡበት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ

በአራት ክልሎች በ5.7 ቢሊዮን ብር እየተገነቡ ለሚገኙት አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች ማቅረብ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የተመረተ የአሉሚንየም ምርት ለውጭ ገበያ ቀረበ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ፋብሪካ በመትከልም ሆነ ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ቀዳሚ የሆነው ቢኤንድሲ የተባለው የአሉሚንየም አምራችና አከፋፋይ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ስም ያመረታቸውን የአሉሚንየም ምርቶች ወደ ውጭ መላክ ጀመረ፡፡