Skip to main content
x

የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት 20 ወራት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌታሁን ናና፣ ከኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ጌታሁን ናና ኃላፊነታቸውን የለቀቁት በፈቃዳቸው ነው፡፡ ሆኖም ባንኩን ለመምራት በተመደቡ በአጭር ጊዜ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የተገደዱት፣ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከፍተኛ ጭቀጭቅ ያስነሳ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት መልቀቂያ አስገቡ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና ከፍተኛ ወቀሳዎች ከተሰነዘሩበት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በኋላ፣ ዓርብ ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማስገባታቸው ታወቀ፡፡

አይኤምኤፍ የልማት ባንክ የተዛባ ብድር አሰጣጥን ለማስተካከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥል አለ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክን የተዛባ ብድር አሰጣጥን ለማስተካከል፣ በመንግሥት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት አለ፡፡ አይኤምኤፍ ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከገመገመ በኋላ ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የልማት ባንክን ለማስተካከል የጀመረውን ጥረት በመደገፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የልማት ባንክን የተበላሸ ብድር ለማስተካከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ 25.3 በመቶ የሚሆነው የተበላሸ ብድር በመሆኑ፣ ይኼንን የተበላሸ ብድር ምጣኔ ወደ ገደቡ ለመመለስ በባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቋመ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ገደብ ያስቀመጠ ቢሆንም፣ የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር መጠን 25.3 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

ልማት ባንክ አዳዲስ የእርሻ ፕሮጀክቶች የብድር ጥያቄዎችን መቀበል አቆመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአዳዲስ በዝናብ የሚለሙ እርሻ ፕሮጀክቶች የሚመጡ የብድር ጥያቄዎች መቀበል ማቆሙን አስታወቀ፡፡ ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና ለሁሉም የባንኩ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤቶች ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ፣ ተለዋጭ መመርያ እስከሚስጥ ድረስ አዳዲስ በዝናብ የሚለሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች የብድር ጥያቄ ለጊዜው ማስተናገድ ማቆሙ ተገልጿል፡፡

ከሦስት ሺሕ በላይ ተጠቃሚዎች የሚሳትፉት የ276 ሚሊዮን ዶላር የሊዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ምንም እንኳ ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት በፊት ቢጀመርም የዓለም ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ባቀረቡት የ276 ሚሊዮን ዶላር ብድር አማካይነት ከ3,000 በላይ ተጠቃሚዎችን በማሽነሪ ኪራይ ብድር በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ መሰማራት የሚችሉበትን ዕድል ይዞ ብቅ ማለቱ ይፋ ተደርጓል፡፡

ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ብድር መስጠት የሚያስችል ዝግጅት እንዲደረግ ለሁሉም ቅርንጫፎች ትዕዛዝ ሰጠ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ ቅርንጫፎቹ ባስተላለፈው የውስጥ ማስታወሻ፣ ጥሩ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክቶች ለሚቀጥለው ምርት ዘመን ብድር ለማቅረብ ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ላቀረቡት ምርት ክፍያ ያጡ አገር በቀል ኩባንያዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቀረቡ

ለቱርክ ኩባንያ ኤልሲ አዲስ ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ጥጥ በብድር ሲያቀርቡ የቆዩ 12 አገር በቀል ኩባንያዎች ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን በመግለጽ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) መፍትሔ እንዲሰጧቸው ጠየቁ፡፡

ለጋምቤላ እርሻዎች የተሰጠው ብድር የልማት ባንክን መመለስ ያልቻሉ ብድሮች ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር አድርሷል ተባለ

በመንግሥት ድጋፍ የግል አልሚዎች በጋምቤላ ክልል ለጀመሯቸው ሰፋፊ እርሻዎች የተለቀቀው ብር የኢትዮጵያ ልማት ባንክን የማይመለስና መመለሳቸው አጠራጣሪ የሆኑ ብድሮች መጠን፣ 8.6 ቢሊዮን ብር እንዲደርስ ምክንያት ሆነዋል ተባለ፡፡ ይኼንን ያሉት የአገሪቱ የገንዘብ ተቋማትን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ናቸው፡፡

በሰፋፊ እርሻዎች የተንሰራፋውን ችግር ለመፍታት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ተጠየቀ

በተለያዩ ክልሎች በሰፋፊ እርሻ ሥራ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያወጣው የብድር ፖሊሲ ሊያሠሯቸው እንዳልቻለ በተደጋጋሚ ቢገልጹም፣ ልማት ባንክ ጉዳዩ የፋይናንስ አቅርቦት ብቻ ስላልሆነ ችግሩን ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት መሳተፍ ይኖርባቸዋል አለ፡፡