Skip to main content
x

የሪል ስቴትና የአከራይ ተከራይ አዋጅ በድጋሚ እንዲስተካከል ታዘዘ

በሪል ስቴት ቤቶች ግብይት፣ በመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆኑ ሦስት ረቂቅ አዋጆች በጥቅል ተዘጋጅተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከቀረቡ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሦስቱም ረቂቅ አዋጆች ተነጣጥለው እንዲዘጋጁ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የሊዝ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢገባም እስካሁን ውይይት አልተደረገበትም

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 በድጋሚ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ ከወራት በፊት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢቀርብም፣ ምክር ቤቱ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በመጠመዱ እስካሁን እንዳልመከረበት ምንጮች ገለጹ፡፡

የጄኔራሎች ሹመትና አንድምታው

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በርዕሰ ብሔርነት ከተሾሙ አንስቶ ከፈጸሟቸው ተግባራት በጉልህ የሚታወቀው፣ ባለፉት ዓመታት ለከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች በየዓመቱ ሲሰጡ የነበረው የማዕረግ ሹመት ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በ2005 ዓ.ም. ለ35 ጄኔራሎች ሹመት ከሰጡ በኋላ በ2006 ዓ.ም. ለ37፣ በ2008 ዓ.ም. ለስድስት፣ በ2009 ዓ.ም. ደግሞ ለ38 ጄኔራሎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡ ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ደግሞ ለ61 የሠራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች የጄኔራል መኮንነት ማዕረጎችን ሰጥተዋል፡፡

መንግሥት በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ የጣለውን ዕገዳ አነሳ

መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ለዓመታት ጥሎት የነበረውን ዕገዳ ከማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲነሳ ወሰነ። የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዕገዳው እንዲነሳ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥር 22 ቀን ጀምሮ ዕገዳው እንዲነሳ መወሰኑን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

የመንግሥትና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥትን ብቻ የሚመለከት ሆኖ ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥትና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጅ፣ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶችን ብቻ የሚመለከት እንዲሆን ማሻሻያ በማድረግ አፀደቀ። አዋጁ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶችን ብቻ የሚመለከት እንዲሆን ከተደረገው መሠረታዊ ማሻሻያ ውጪ፣ ሌሎች ማሻሻያዎችም በረቂቁ ላይ ተደርገዋል። ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለምክር ቤቱ የቀረበው ይህ አዋጅ የተፈጻሚነት ወሰንን የሚገልጸው አንቀጽ፣ ‹‹ለክልል መንግሥታት በሚሰጥ ልዩ ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች›› በመንግሥትና በግል አጋርነት ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተቱ የሚያደርግ ነበር።

የኦሮሚያ ክልል በአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ላይ ለፓርላማ ያቀረበው የሕጋዊነት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የኦሮሚያ ክልል በፌዴራል መንግሥት ተረቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ሕገ መንግሥታዊ  አለመሆኑን በመጥቀስ እንዳይፀድቅ በተደጋጋሚ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጎ በፓርላማው ፀደቀ። የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ረቂቅ አዋጁ በሕገ መንግሥቱ ለክልሎች የተሰጠውን ሥልጣን ከግምት ያላስገባና ለመተግበር አስቸጋሪ ሆኖ በመዘጋጀቱ ሊፀድቅ እንደማይገባው በመጥቀስ የሕግ ሰነዱን ላመነጨው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር እየተመለከተ ለነበረው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በደብዳቤ በተደጋጋሚ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ለቀረቡ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች የኢሕአዴግ ምላሽ እየተጠበቀ ነው

አሥራ አምስት አገር አቀፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አራተኛ የመደራደሪያ አጀንዳ በሆነው የፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 ላይ ተከታታይ ድርድር ሲያደርጉ፣ ፓርቲዎቹ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ እንዲሰረዙ፣ እንዲሻሻሉና እንዲጨመሩ ብለው ላነሷቸው ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች የኢሕአዴግ ምላሽ እየተጠበቀ ነው፡፡

እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ የአደገኛ ቆሻሻ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

 

 

በዮናስ ዓብይ

የአደገኛ ኬሚካልና ቆሻሻ ወደ አገር ውስጥ አገባብ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ለመቆጣጠር አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቅ ሕጉ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል በተባለለት የቁጥጥር ዕርምጃ፣ ጥፋተኛ በሚባሉ አስገቢዎችና አምራቾች ላይ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ እስራትና እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ በድንጋጌው ውስጥ አስፍሯል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ላይ ድርድር ጀመሩ

በአገሪቱ የምርጫ ማዕቀፍ ሕጎች፣ ተያያዥ ሕጎችና አዋጆች ላይ ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር ድርድር በማድረግ ላይ የሚገኙት 15 አገር አቀፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ላይ የሚያደርጉትን ድርድር ዓርብ ታኅሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ማካሄድ ጀመሩ፡፡