Skip to main content
x

ሆሄ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ጸሐፊዎችን ያወዳድራል

ሆሄ ዓመታዊ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ግጥምና ወግ የሚያስነብቡ ጀማሪ ጸሐፊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም አስታውቋል፡፡ ዓምና የመጀመሪያው ዙር ውድድር የተካሄደው በረዥም ልቦለድ፣ በልጆች መጻሕፍትና በግጥም ዘርፍ ሲሆን፣ ዘንድሮ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ታክሎበታል፡፡ በ2009 ዓ.ም. በማኅበራዊ ድረ ገጽ (በዋነኛነት በፌስቡክ) ከቀረቡ ግጥሞችና ወጎች በተጨማሪ ታትመው ለንባብ የቀረቡ የወግ መጻሕፍትም በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡

ለአዳዲስ ፈጠራ ስንቅ የሆነው ይበልታ

ዳጉሳ የተለያየ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች የሚመረት ድርቅና በሽታን መቋቋም የሚችል ሰብል ነው፡፡ በተለይም በቆላማና ደጋማ ቦታዎች በስፋት መመረት ይችላል፡፡ ነገር ግን ተፈላጊነቱ ከሌሎች ሰብሎች አንፃር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተመረተ የሚገኘውም በ454,662 ሔክታር መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡