Skip to main content
x

በምርት ገበያው የሚያዝያ ወር ግብይት አሽቆለቆለ

ባለፉት ተከታታይ ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ከፍተኛ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበሩት የቡና፣ የሰሊጥ፣ የቦሎቄና የማሾ ምርቶች በሚያዝያ ወር ያስመዘገቡት የግብይት መጠን ዝቅተኛ እንደነበር ተገለጸ፡፡ በሚያዝያ ወር የተመዘገበው ዝቅተኛ ግብይት፣ አጠቃላይ የምርት ገበያውን ወርኃዊ የግብይት መጠንና የግብይት ዋጋ ከቀደመው ወር አኳያ ዝቅ እንዲል አስገድዷል፡፡

የምርት ገበያው የመጋቢት ወር ግብይት ከ3.7 ቢሊዮን ብር በላይ ተመዘገበበት

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም. ቡናን ጨምሮ በአንድ ወር ውስጥ ባካሄደው ግብይት 3.7 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው 72,159 ቶን ምርት እንዳገበያየ ተገለጸ፡፡ ካለፈው ወር አኳያ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው የቡና ምርት መገበያየቱም ታውቋል፡፡  

ለምርት ገበያ አባልነት የቀረበ ወንበር በ3.5 ሚሊዮን ብር ተጫረተ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ሥራ በጀመረ ጊዜ የአባልነት ወንበር የያዙ አባላት ድርሻቸውን የገዙት በ50 ሺሕ ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሁለት ዓይነት የአባልነት ሒደትን በመከተል ሲንቀሳቀስ የቆየው ምርት ገበያው፣ በመጀመርያው ዙር አባልነትን በዝቅተኛ ዋጋ ካስገኘው የወንበር ሽያጭ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት በአባላት ጥያቄ፣ ምርት ገበያውም በራሱ ተጨማሪ ወንበሮችን በማካተት  የአባልነት ወንበር የሚያስገኘውን ዕድል በጨረታ ማቅረብ ጀምሮ በዚያው አግባብ ሲሠራ ቆይቷል፡፡

ምርት ገበያና ደቡብ ግሎባል ባንክ ለግብይት አገልግሎት ስምምነት ፈጸሙ

የቀድሞው የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኝ ነገራና የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አዲሱ ሃባ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር በየወሩ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ የሚገናኙበት መድረክ ነበራቸው፡፡

በሰሊጥ ግብይት የ6.7 ቢሊዮን ብር ዋጋ ተመዘገበ

ከአገሪቱ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል አንዱ የሆነው ሰሊጥ፣ ባለፉት ሰባት ወራት ከ205,900 ቶን በላይ ሲገበያይ፣ በዋጋ ረገድም ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ፡፡ በምርት ገበያው በኩል የሚገበያዩ ሌሎች ምርቶችም የተሻለ ግብይት ማሳየታቸው አስታውቋል፡፡  

ምርት ገበያ ከፍተኛ የሰሊጥና የቡና ግብይት ማከናወኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2010 ግማሽ በጀት ዓመት 317,607 ቶን የግብርና ምርቶች ያገበያየ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 133,818 ቶን ቡና በማገበያየት ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ በማስመዝገብ ቀዳሚውን ድርሻ መውሰዱ ተገለጸ፡፡ 

ምርት ገበያ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ወርኃዊ ግብይት አስመዘገበ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወርኃዊ የግብይት ክዋኔዎች፣ በቡና ሰሊጥ ምርቶች ግብይት በመጠንና በዋጋ ረገድ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ጭምሪ እያሳዩ መምጣታቸውን ምርት ገበያው ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ንግድ ምርቶች በመሆን የሚጠቀሱት ቡናና ሰሊጥ ላይ የሚታየው የግብይት መጠን ከወትሮው ይልቅ እየጨመረ በመምጣቱ፣ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል እያመላከተ ነው፡፡

ሰሊጥ ከቡና ብልጫ የወሰደበትን የ1.8 ቢሊዮን ብር ግብይት አስመዘገበ

በኢትዮጵያ የምርት ገበያ በየዕለቱ ግብይታቸው ከሚፈጸሙ የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል አንዱ የሆነው ሰሊጥ ለመጀመርያ ጊዜ ከቡና የበለጠ መጠን ያለው ምርት ለገበያ ቀረበ፡፡ በኅዳር ወር ለግብይት የቀረበው ሰሊጥ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር ከ532 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡

ብርሃንና ቡና ባንክ የምርት ገበያን ሥርዓት ተቀላቀሉ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ክፍያና ርክክብ ለሚያስፈጽሙ ሁለት ባንኮች ተጨማሪ ባንኮች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው ባንኮች ቁጥር 12 ማድረሱንና ለተመሳሳይ ሥራ አምስት ባንኮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

አርትስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን የቀድሞ የምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ሾመ

አርትስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን አክሲዮን ማኅበር የቀድሞ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ኤርሚያስ እሸቱን፣ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾመ፡፡ አቶ ኤርሚያስ የምርት ገበያውን ለሦስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ የሥራ መልቀቂያቸውን በቅርቡ ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡